Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ትህትናና ገርነት

    እግዚአብሔር ወንዶችንና ሴቶችን ለአገልግሎት ሲርጥ ትምህርት፣ የአነጋገር ብቃት ወይም ምድራዊ ሐብት እንዲኖራቸው አይጠይቅም፡፡ ይልቁንም“እኔ ላስተምራቸው በምችለው የትህትናና ገርነት መንገድ ይመላለሳሉ? ቃሌን በከንፈሮቻቸው ማኖር እችላለሁ? በሄዱበት ሁሉ እኔን ይወክላሉ?” በማለት ይጠይቃቸዋል፡፡Testimonies, vol. 7, p. 144.ChSAmh 341.2

    ክብርዎንና የበላይነትዎን እያሳዩ ድኾችን፣ የተናቁትንና የተተዉትን ለመርዳት የሚሞክሩ ከሆነ ይህ አካሄድ አንዳችም hንውን አያገኝሎትም፡፡- Testimonies, vol. 6, p. 277. ChSAmh 341.3

    ቤተ ክርስቲያኖቻችንን በጥረቶቻቸው ሁሉ ብርቱና ስኬታማ ሊያደርግ የሚችለው ጉድ ጉድ ማለታቸው ብቻ ሳይሆን የተረጋጋና ትሁት ሥራ መሥራታቸው—በታይታና ጉራ ሳይሆን በትዕግሥትና በጸሎት ጽኑ ጥረት ማድረጋቸው ነው፡፡Testimonies, vol. 5, p. 130.ChSAmh 341.4

    በተደጋጋሚ የሚደርስብን ሽንፈትና ውርደት ያለ እርሱ ድጋፍና እርዳታ አምላካዊውን ፈቃድ መፈጸም እንደማንችል _ ያሳየናል፡፡ Patriarchs and Prophets, p. 633.ChSAmh 342.1

    የደሳሳ ጎጆ ነዋሪው ትሁት ነፍስ መክሊቶች ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው እየተዘዋወርን ለምንሰጠው አገልግሎት ከሌሎች የከበሩ ስጦታዎች ይልቅ የበለጠ ውጤት እንድናስመዘግብ ያስችለናል፡፡-Testimonies, vol 9, Pp. 37, 38.ChSAmh 342.2

    የእግዚአብሔር መልእክተኞች በናዝሬቱ የሱስ ስም ወደ ዓለም ይዘው በሚሄዱት ሥራ መላው የሰማይ ሠራዊት ደስተኛ ነው፡፡ ይህ ሥራ ታላቅ እንደመሆኑ ወንድሞችና እህቶች በየቀኑ ራሳችንን በእግዚአብሔር ፊት ትሑት እያደረግን የሰብዓዊው ጥበብ ፍጹም አለመሆን ሊሰማን ይገባል፡፡ ሥራውን በጽናት መያዝ ይጠበቅብናል፡፡ እግዚአብሔር ትሁት እንዲያደርገን መጸለይ የለብንም፡፡ ምክንያቱም ማንነታችን በእርሱ ቁጥጥር ስር ሲውል እኛን ደስ እንደሚያሰኝ ሳይሆን እንደ እርሱ ፈቃድ ትሁት ያደርገናል፡፡ ይህም ቢሆን በኃያሉ አምላh እጆች ስር ራሳችንን በየቀኑ ትሁት እያደረግን የግል ደኅንነታችንን በፍርሐትና በመንቀጥቀጥ መለማመድ ይኖርብናል፡፡ ፈቃዱን የሚፈጽመውም ሆነ እርሱን ደስ የሚያሰኘውን ነገር በእኛ ውስጥ የሚሠራው ራሱ እግዚአብሔር እንደመሆኑ በእኛ ውሰጥ በሚሠራው ሥራ ልንተባበረው ይገባል፡፡Review and Herald, July 12, 1887.ChSAmh 342.3

    ከጠባቡ መንገድ በስተመጨረሻ ከሚገኘው በር ዘልቀን ለመግባት ብርቱ ትግል ማድረግ ይኖርብናል፡፡ ሆኖም ይህ በር የላሉ ማጠፊያዎች ስለሌሉት በጥርጣሬ የተሞሉ ባህሪያት እንዲገቡ ሊፈቅድ አይችልም፡፡ ከፊታችን ከተቀመጠው የከበረ ዋጋ ያለው ሽልማት ጋር ተመጣጣኝ ተጋድሎ እያደረግን የዘላለም ህይወት ባለቤት ለመሆን ከወዲሁ መጣር ይኖርብናል፡፡ የመንግሥተ ሰማይን በሮች የሚከፍትልን ገንዘባችን፣ ርስታችን ወይም ምድራዊ ሥልጣናችን ሳይሆን የክርስቶስ ዓይነት ጸባይ ባለቤት መሆናችን ነው፡፡ የህያውነትን ዘውድ እንድንደፋ የሚያስችለን የዚህ ዓለም ክብራችን ወይም የከፍተኛ ትምህርት ምሑራዊ ስኬታችን አይደም፡፡ እግዚአብሔርን የብቃታቸው መለኪያ ያደረጉ ትሁታን፣ ገሮችና ራሳቸውን ዝቅ ያደረጉ ብቻ ይህን ስጦታ ይቀበላሉ፡፡-Southern Watchman, April 16, 1903.ChSAmh 342.4

    የወንጌል አገልግሎት ሰጥተው ወደ ቤትዎ ሲመለሱ የክርስቶስን የቀራኒዮ መስቀል ከፍ ያድርጉለራስዎ ሳይሆን ለየሱስ ክብር ይስጡ፡፡Testimonies, vol. 5, p. 596.ChSAmh 343.1

    ትvትና ከክብር ይቀድማል፡፡ ከሰዎች መካከል ከፍተኛውን ቦታ እንዲይዝ እግዚአብሔር የሚመርጠው እንደ መጥምቁ ዮሐንስ በእርሱ ፊት ራሱን ዝቅ የሚያደርገውን ሠራተኛ ነው፡፡ ለእግዚአብሔር ቀልጣፋ ሠራተኛ የሚሆነው እንደ ህፃን ገር ልብ ያለው ደቀ መዝሙር ነው፡፡ የሰማይ ተወካዮች ሊተባበሩ የሚችሉትም ራሱን ከፍ ከፍ ለማድረግ ሳይሆን ነፍሳትን ለማዳን ከሚጥረው ሰው ጋር ነው፡፡The Desire of Ages, p. 436. ChSAmh 343.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents