Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መሥጋታችንን እናቁም

    የአገልጋዮች ራሳቸውን ለሥራው ቀድሰው አለመስጠት በአገልግሎት ላይ ስህተት እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል፡፡ ይህን ተከትሎ የሚከሰተው ውጤት ከዐይኖችዎ የዕንባ ዘለላ እንዲወርድ መንስዔ ሊሆን ቢችልም ነገር ግን ሥጋት አይግባዎ፡፡ ከአጥናፍ እስh አጥናፍ የተዘረጋው የቡሩኩ ጌታ ሥራ በእርሱ ተቆጣጣሪነት እየተመራ ነው፡፡ እርሱ የሚጠይቀው ነገር ቢኖር ሠራተኞቹ አምላካዊውን ትዕዛዝ ለመቀበል ወደ እርሱ መጥተው መመሪያዎቹን እንዲታዘዙ ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያኖቻችን፣ የሰንበት ትምህርት አገልግሎታችን፣ የሰበካ ጽሕፈት ቤቶቻችን እንዲሁም ተቋሞቻችን ከመለኮታዊው ልብ በሚመነጭ አመራር ተግባራቸውን ያከናውናሉ፡፡ ለምን እንሰጋለን? ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር ባነጻት መሰረት ሕያውና አንጸባራቂ ሆና ለመመልከት የኖረው መናፈቅ ሙሉ ለሙሉ በእግዚአብሔር ላይ በመታመን እንደ ብረት የጠነከረ ሊሆን ይገባል፡፡-Review and Herald, Nov. 14, 1893.ChSAmh 336.3

    የተረጋጋ ባህሪን እያጎለበቱና እየተንከባከቡ የነፍስዎን መጠበቅ እንደ ታማኝ ፈጣሪ ለእግዚአብሔር ያስረክቡ፡፡ ለአምላካዊው አመኔታ የተተወውን ሁሉ እርሱ ጠብቆ ያቆያል፡፡ አምላካዊውን መሠዊያ በእንባና በምሬት በመሸፈናችን ደስተኛ አይደለም፡፡ ምናልባት ሌላው ነፍስ ሲለወጥ ማየት ባይችሉ እንኳ ነገር ግን ስለ ሆነው ሁሉ ለእግዚአብሔር ምስጋና የሚያቀርቡበት በቂ ምክንያት አሎት፡፡ _ ማንኛውንም ነገር ከገዛ አስተሳሰብዎ ጋር ተስማሚ እንዲሆን ለማስተካከል የማይሞክሩና ወደ ፊት መራመድዎን ብቻ የሚቀጥሉ ከሆነ ልካሙ ሥራ ቀጣይነት ይኖረዋል፡፡ ዘወትር አመስጋኝ ይሆኑ ዘንድ የእግዚአብሔር ሰላም የልብዎን ማህደር ይግዛ፡፡ ጌታ በእርስዎ ውስጥ ፈቃዱን ለመፈጸም የሚችልበት ዕድል ይኑረው እንጂ መንገዱን አይዝጉበት፡፡ በእርግጥ ከፈቀድንለት መሥራት ይችላል—ይሠራልም! Testimonies, vol. 9, p. 136.ChSAmh 337.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents