Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መለኮታዊው ተልዕኮ

    ደቀ መዛሙርቱ የሠሩትን ሥራ እኛም እንሥራእያንዳንዱ ክርስቲያን ወንጌላዊ መሆን ይጠበቅበታልና፡፡ የሌሎችን ስሜት በመካፈልና ተገቢውን ርኅራኄ በማሳየት እርዳታ የሚያሻቸውን እናገልግል፣ ከራስ ወዳድነት በጸዳ ቅንነት በሰብዓዊው ወዮታ ላይ የማብራት ምኞት ይደርብን፡፡--The Min istry of Healing, p. 104. ChSAmh 28.4

    ክርስቶስ ወደ ሰማይ ከማረጉ አስቀድሞ እርሱ የተወላቸውን የከበረ ዋጋ ያለውን ዘላማዊ ሕይወት የሚያስገኘውን አምላካዊ ፈቃድ በሥራ ላይ 28ለአገልግሎት የቀረበልን አምላካዊ ጥሪ የሚያውሉበትን ተልዕኮ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፡፡ --The Acts of the Apostles, p. 27.ChSAmh 29.1

    ለመጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት የተተወላቸው አደራ በዘመናት ያሉ አማኞች የሚጋሩት እውነታ ነው፡፡ ወንጌልን የተቀበለ ማንኛውም ሰው ለዓለም የሚያደርሰው የተቀደሰ እውነት ተሰጥቶታል፡፡ የእግዚአብሔር ታማኝ ሕዝቦች ያላቸውን ንብረት፣ ዕውቀትም ሆነ መክሊት በጥበብ ለአገልግሎት እያዋሉ ሁል ጊዜም ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ የማያፈገፍጉ መልእክተኞቹ ናቸው፡፡ --The Acts of the Apostles, p. 109. የወንጌል ተልዕኮ ከክርስቶስ መንግሥት ጋር የሚደረግ ታላቅ ውል ነው፡፡ ደቀ መዛሙርት መላውን የምኅረት ግብዣ እያቀረቡ በቅንነት ለነፍሳት እንዲሠሩ ተጠርተዋል፡፡ ሰዎች እንዲመጡ በመጠባበቅ ፋንታ መልእክቶቻቸውን ይዘው ወደ እነርሱ ይሂዱ፡፡The Acts of the Apos tles, p. 28. ChSAmh 29.2

    የእግዚአብሔር መልእክተኞች ክርስቶስ በዚህ ምድር የሠራውን ሥራ አጥብቀው የሚይዙበት ተልዕኮ ተሰጥቶአቸዋል፡፡ በእርሱ ለተጀመረው ለእያንዳንዱ የአገልግሎት ዘርፍ ራሳቸውን አሳልፈው እንዲሰጡ ተጠርተዋል፡፡ ሊደረስበት ስለማይችለው ባለጸግነቱና ሕያው ስለሆነው ሰማያዊ ሀብት ቅንና ታማኝ በሆነ ልብ ይመስክሩ፡፡-- Testimonies, vol 9, p. 130.ChSAmh 29.3

    ለደቀ መዛሙርቱ የተሰጠው ተልዕኮ እነሆ ለእኛም ተሰጥቶናል፡፡ በመስቀል ላይ የተሰቀለውና ከመቃብር የተነሳው አዳኝ ዛሬም እንደ ቀድሞው ያለ እግዚአብሔርና ያለ ተስፋ በተቀመጡት ፊት ከፍ ከፍ ሊልና ሊከብር ይገባል፡፡ ጌታ ለመጋቢዎች፣ ለመምህራንና ለወንጌላውያን ጥሪውን ያቀርባል፡፡መልእክተኞች የደኅንነትን መልእክት በየደጃፉ ያውጁ፡፡ በክርስቶስ የተገኘው የይቅርታ የምስራች ለእያንዳንዱ መንግሥት፣ ብሔር፣ ልሳንና ሕዝብ ይነገር፡፡ መልእክቱ በለዘዘና ህይወት በሌለው ለሆሳስ ድምፅ ሳይሆን ግልጽ በሆነ፣ በማያጠራጥርና በሚያነሳሳ አነጋገር ይቅረብ፡፡ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖች ከጥፋት ለማምለጥ የሚያስችላቸውን ማስጠንቀቂያ እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡ ዓለም የክርስትናን ኃይል በክርስቲያኖች ህይወት በማስረጃ መመልከት ይሻል፡፡ የምኅረት ልእክቶች በጥቂት ስፍራዎች ብቻ ሳይሆን በመላው ዓለም ይፈለጋሉ፡፡ - Gospel Workers, p. 29. ChSAmh 29.4

    የሱስ ምድራዊ ሥራውን የወንጌልን _ ብርሃን ለተቀበሉ ወገኖች በመስጠት ወደ ሰማይ አረገ፡፡ አገልግሎቱን የተረከቡ ሥራውን ወደፊት በማስኬድ ከፍጻሜ ማድረስ ነበረባቸው፡፡ የእርሱን እውነት የሚያሰራጭ አንድም ሌላ ወኪል አልደነገገም “ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ፡፡” “እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፡፡” ይህ የተከበረ ተልዕኮ በዚህ ዘመን ለምንገኝ ለእኛ ደርሶአል፡፡ እግዚአብሔር ይህን የመቀበል ወይም የመቃወም ኃላፊነት ለቤተ ክርስቲያኑ ተቶአል፡፡ --Historical Sketches, p. 288. ChSAmh 30.1

    የተቀደሰ ኃላፊነት ወድቆብናል፡፡ “ስለዚህ _ ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው፤ እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁል ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ” (ማቴ. 28፡19-20)፡፡ የሰማይን ፍጽምና ኃይልና _ ብርታትዎ አድርገው የደኅንነትን ወንጌል ለሌሎች በማሳወቁ ሥራ ራስዎን አሳልፈው እንዲሰጡ ተጠርተዋል፡፡-Testimonies, vol. 9, pp. 20, 21. ChSAmh 30.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents