Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 3—በእግዚአብሔር ሕዝቦች መሃል የሚስተዋሉ ሁናቴዎች

    የወንጌላዊነት መንፈስ እጦት

    በሰንበት ጠባቂ አድቬንቲስቶች መሃል አነስተኛ የወንጌላዊነት መንፈስ ይስተዋላል፡፡ እግዚአብሔር ሕጉን በአእምሮአቸው አትሞና በልባቸው ማህደር ጽፎ የትእዛዛቱ ማኖሪያ አድርጎ በተለይ ያከበራቸው አገልጋዮችና ምዕመኑ በበቂ ደረጃ መነሳሳት ቢችሉ ኖሮ እንዲህ ምላሽ የማይሰጡ ሆነው ተደላድለው ባልተቀመጡ ነበር፡፡--Testimonies, vol. 3, p. 202. ChSAmh 46.1

    እውነተኛ የወንጌላዊነት መንፈስ የከበረ ሥራ መሥራት የምትችለውን ቤተ ክርስቲያን ትቶአታል፡፡ ምእመናን ልባቸው በፍቅር ተሞልቶ በነፍሳት ላይ ማብራት አቁሞአል--ወደ ክርስቶስ እቅፍ እንዲያመሩ የሚያደርገው ምኞታቸውም ደብዝዞአል፡፡ ቅን ሠራተኞች ያስፈልጉናል፡፡ ከእያንዳንዱ አጥቢያ ለሚደጠው የድረሱልን ጩኸት ምላሸ የሚሰጥ የለ ይሆን?--Testimonies, vol. 4, p. 156. ChSAmh 46.2

    እኛ እንደ ሕዝብ በቂ አገልግሎት እየሰጠን እንዳልሆነ ተመልክቼአለሁ፡፡ ሠራተኞቻችን ከእምነታችን ጋር ስምሙ አገልግሎት እየሰጡ አይደለም፡፡ ሟች ለሆነው ፍጡር ያልተሰጠ እጅግ የተከበረ ድንጋጌና አስፈላጊ መልእክት ሥር እየኖርን ለመሆናችን እምነታችን ይመሰክራል፡፡ ሆኖም ይvን ተጨባጭ እውነታ ጠቅለል አድርገንበእግዚአብሔር ሕዝቦች መሃል የሚስተዋሉ ሁናቴዎች ስንመለከተው በእኛ ውስጥ የሚስተዋለው ጥረት፣ ቅንአትም ሆነ ራስን ሥዋዕት አድርጎ የመስጠት መንፈስ ከሥራው ጸባይ ጋር የሚነጻጸር አይደለም፡፡ ከሙታን እንንቃ--ክርስቶስም ሕይወት ይሰጠናል-Testimonies, vol. 2, p. 114. ChSAmh 46.3

    ቤተ ክርስቲያኖቻችን ለእግዚአብሔር ተጠሪ የሆኑበትን እጅግ የተከበረ ኃላፊነት ሳስብ ልቤ ይደማል፡፡ የክርስቶስ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮች ብቻ አይደሉም፡፡ ይልቁንም እያንዳንዱ ምልምል ወንድና ሴት የክርስቶስ ሠራዊት የእርሱ ወታደር ነው፡፡ ክርስቶስ ራሱን በመካድና ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጎ በመስጠት ምሳሌ እንደሆነ ወታደሮች - የወታደርን ደሞዝ ለመቀበል _ ፈቃደኞች ናቸውን? በአጠቃላይ በቤተ ክርስቲያኖቻችን እየታየ ያለው ራስን መካድ ምን ይመስላል? ምእመናን የገንዘብ ልግስና ሲያደርጉ እንጂ ራሳቸውን ለአገልግሎት ሲሰጡ አይታዩም፡፡--General Conference Bulletin, 1893, p. 131.ChSAmh 47.1

    የክርስቶስ ተከታዮች ነን ከሚሉ ክርስቲያኖች ውስጥ አብዛኞቹ ለዓለም የሚሠሩትን ያህል የነፍሳት ሸክም አይሰማቸውም፡፡ የዐይን ምንዝር፣ የታበየ ሕይወት፣ የታይታ ፍቅር፣ የምቾት ፍቅር--እነዚህ ሁሉ ክርስቲያኖችን ከእግዚአብሔር _ ስለሚነጥሉ ተጨባጩ የወንጌላዊነት መንፈስ በጥቂቶ ውስጥ ብቻ ይኖራል፡፡ በጽዮን ያሉ የእነዚህን ኃጢአተኞች ዐይን በመክፈት ግብዞችን ወደ ትህትና ለማምጣት ምን መደረግ ይኖርበታል?--General Conference Bulletin, 1893, p. 132. ChSAmh 47.2

    በሜሮዝ የሚወከሉ የሕብረተሰብ ክፍሎች አሉ፡፡ የወንጌላዊነት መንፈስ ፈጽሞ ነፍሳቸውን አልተቆጣጠረውም፡፡ የባዕድ አገር ወንጌላውያን ጥሪ ወደ ተግባር እንዲገቡ አላነሳሳቸውም፡፡ በአምላካዊው ሥራ አንዳችም ተሳትፎ ያልኖራቸውነፍሳትን ለክርስቶስ ለመማረክ አንዳች ያላደረጉ እነዚv ሰዎች ለእግዚአብሔር ምን ዓይነት ምላሽ ይሰጣሉ? “አንተ ክፉሰነፍ አገልጋይ” --Historical Sketches, p. 290. ChSAmh 47.3

    የተሰጠውን ልዩ መብትና ጥቅም ገሸሽ አድርጎ በእግዚአብሔር ሥራ ተሳታፊ ከመሆን ስላፈገፈገው የሚከተሉት ቃላት በማጣቀሻነት ተሰጥተውኝ ነበር “የእግዚአብሔር ልአh ሜሮዝን ርገሙ፤ ሕዝቧንም አብራችሁ ርገሙ፤ ከኃያላን ሰልፍ እግዚአብሔርን ለመርዳት በእግዚአብሔርም ጎን ለመቆም አልመጡምና’ “ Testimonies, vol. 2, p. 247.ChSAmh 48.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents