Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 10—የወንጌል አገልግሎት የምንሰጥባቸው ዘዴዎች

    የቤት ለቤት አገልግሎት

    የቤት ለቤት አገልግሎት ብዙ ሕዝብ ከሚያካትት የወንጌል ጥረት መርጎ ግብር ጋር እኩል ዋጋ አለው፡፡ በታላላቅ ከተሞች የወንጌል ጥረት በማድረግ ሊደረስባቸው የማይችሉ ከፍ ባለ እርከን የሚኖሩ አንዳንድ የሕብረተሰብ ክፍሎች አሉ፡፡ እረኛው ከመንጋው ተነጥሎ የጠፋውን በግ ለማግኘት እንደሚያስስ እነዚህም ወገኖች ሊፈለጉ ይገባል፡፡ ስለ እነርሱ በትጋት የተሞላ የግል ጥረት ሊደረግ ይገባል፡፡ እያንዳንዱ በግል የሚሠራውን ሥራ ችላ ሲል በአገልግሎት መጎልበት ቢችሉ ወሳኝ ግስጋሴ ማስገኘት ይቸሉ የነበሩ አያሌ የከበሩ ዕድሎችም ይጠፋሉ፡፡-Testimonies, vol. 9, p. III.ChSAmh 156.1

    ከርኅራኄ ቃላት ጋር ጥምረት ያለው አገልግሎት ያስፈልገናል፡፡ ፍቅርና ርኅራኄ የክርስቶስ መልእክት መግቢዎች ነበሩ፡፡ አገልጋዮች ከአንዱ ቤት ወደ ሌላው እያመሩ፣ እርዳታ ለሚያሻው የእርዳታ እጆቻቸውን እየዘረጉ መልካም _ እድል ሲያኙ የመስቀሉን ታሪክ ይንገሩ፡፡ ከአንደበታቸው የሚወጣው ቃል ክርስቶስ ሊሆን ይገባል፡፡ ጽድቁን ጨብጠው የያዙ፣ ሕይወታቸውም ንጽሕናውን ገልጦ የሚያሳይ ይሁን፡፡-Testimonies, vol. 7, p. 228.ChSAmh 156.2

    እግዚአብሔር የሥነ መለኮት ትምህርት ባይኖራቸውም እንኳ ትሑትና ለክርስትና እምነት ቀናኢ የሆኑ ሰዎችን ይጠቀማል፡፡ እንዲህ ዓይነቶቹ ወገኖች የቤት ለቤት አገልግሎት የሚሰጡ ሠራተኞቹ ይሁኑ፡፡ በእሳት ዳር በቤተሰቦች መሃል ተሰባበው በተጨባ ለሚስፈልጋቸው ነገር ተደራሽነታቸውን እያሳዩና የተቀባው አገልጋይ ሊሰጥ ከሚችለው በላይ አገልግሎት እየሰጡ በትህትና፣ በብልሃትና በጥንቃቄ ወደ አምላካዊው አገልግሎት ይግቡ፡፡--Testimonies, vol. 7, p. 21. ChSAmh 156.3

    ከቤተ ክርስቲያን አባላቶቻችን መሃል አብዛኞቹ በቤተ ለቤት አገልግሎት፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ንባብና በራሪ መንፈሳዊ ጽሑፎችን በማደል ሥራ ተሳታፊ ይሁኑ፡፡-Testimonies, vol. 9, p. 127. ChSAmh 157.1

    በቤት ለቤት አገልግሎት ተሳታፊ የሚሆኑ ሰፊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሏቸውን ዘርፎች የመመልከት ዕድል ያገኛሉ፡፡ ለታመሙት እየጸለዩ የወገኖችን ሥቃይ ለማስታገስ አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ ያድርጉ፡፡ ከዝቅተኞቹ የሕብረተሰብ ክፍሎች፣ ከምስኪኖቹና ከተጨቆኑት ጋር አብረው ይሥሩ፡፡ መሻታቸውን መግዛትና መቆጣጠር ተስኖአቸው በአዘቅት ውስጥ ከሚገኙ ረዳት አልባዎች ጋር በግልም ሆነ በሕብረት ይጸልዩ፡፡ ልቦቻቸውን ለመቀስቀስ ፍላጎት የሚያሳዩትን ለማዳን ጽኑና በትጋት የተሞላ ጥረት ያድርጉ፡፡ በቅድሚያ ለሥጋ የሚያስፈልጓቸውን አንገብጋቢ ችግሮች ሊፈቱ የሚያስችሉ ሥራዎችን በመሥራትና ከአድሎ የጸዳ አገልግሎት በመስጠት ወደ ብዙዎች መድረስ ይቻላል፡፡ ፍቅራችን ራስ ወዳድ አለመሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን በተግባር መመልከት በቻሉ ቁጥር በክርስቶስ ፍቅር ለማመን ይቀላቸዋል፡፡Testimonies, vol. 6, pp. 83, 84.ChSAmh 157.2

    የወንጌል ሠራተኞች የቤት ለቤት አገልግሎት እየሰጡ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ለሕዝቦች እያበሰሩና መንፈሳዊ ጽሑፎችን እያደሉ የእነርሱ ነፍስ የተባረhበትን ብርሃን ለሌሎች ያጋሩ፡፡Testimonies, vol. 9, p. 123. ChSAmh 157.3

    አዳኛችን በየቤቱ እየተዘዋወረ የታመሙትን እየፈወሰ፣ ያዘኑትን እያጽናና፣ ጉዳት የደረሰባቸውን እያረጋጋና እያረካ ሰላም የሚሰጡ ቃላትንያካፍል ነበር፡፡ ሕጻናትን በክንዶቹ እያቀፈና እየባረከ ለእናቶች ተስፋ የሚሰጡና የሚያጽናኑ ቃላትን ይናገር ነበር፡፡ የሁሉም አገልጋይ የነበረው እርሱ የእያንዳንዱን የሰብዓዊ ፍጡር ዋይታና ሥቃይ ማብቂያ በሌለው ርኅራኄና ጨዋነት ተጋርቶአል፡፡ ወደዚህ ምድር መጥቶ ለሚገናኛቸው ሁሉ የእርሱ ሥጋና ደም ተስፋና ብርታት ማምጣት ነበረበት፡፡Gospel Workers, p. 188. ChSAmh 158.1

    በፍቅርና ቀለል ባለ መልኩ የሚሰጠው የቤት ለቤት አገልግሎት ክርስቶስ ለመጀመሪያ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን ለአገልግሎት ሲያሰማራ ከሰጣቸው ትእዛዛት ጋር ህብር ሊፈጥር ይገባል፡፡ የምስጋና መዝሙሮችን በመዘመር፣ ትሕትና በማሳየትና ከልብ የመነጨ ጸሎት በማድረግ ወደ ብዙዎች መድረስ ይቻላል፡፡ መለኮታዊው ሠራተኛው ጽኑውን እምነት ለልቦች ለማስተላለፍ በስፍራው ይገኛል፡፡ ክርስቶስ “ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ” ሲል ተስፋ ሰጥቶናል፡፡ እንዲህ ያለው ረዳት የሰጠንን የአብሮነት ማረጋረጫ ይዘን በእምነት፣ በተስፋና በብርታት መሥራት እንችላለን፡፡ Testimonies, vol. 9, p. 34. ChSAmh 158.2

    የቤት ለቤት አገልግሎት የሚሰጡ ሠራተኞች ይፈለጋሉ፡፡ ስለ መጽሐፍ ቅዱሳዊው እውነት አንዳችም ለማያውቁ ሰዎች ወሳኝ ጥረት እንዲደረግ ጌታ ጥሪ ያቀርባል፡፡ በእነዚv ወገኖች መኖሪያ የመዝሙር፣ የጸሎትና የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ መርኅ ግብሮች ሊካሄዱ ይገባል፡፡ ታላቁን ተልዕኮ በመታዘዝ አገልግሎት የምንሰጥበት ጊዜ አሁን ነው “ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ አስተምሯቸው”፡፡ ይህን ሥራ የሚሠሩ በማንኛውም ሰዓት አገልግሎት ላይ መዋል የሚችል የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ “ተጽፏል” _ የተሰኘው አምላካዊ ቃል የመከላከያ መሣሪያቸው ሊሆን የግድ ነው፡፡Counsels to Teachers, p. 540. ChSAmh 158.3

    ወንድቼና እህቶቼበአቅራቢያችሁ የሚገኙ ወገኖችን በመጎብኘትየወንጌል አገልግሎት የምንሰጥባቸው ዘዴዎች በርኅራኄና ደግነት ወደ ልቦቻቸው የመድረስ ምኞት ይደርባችሁ፡፡ አገልግሎታችሁ ጠባብ አስተሳሰብንም ሆነ ፍረጃን የሚቀርፍ እንጂ የሚፈጥር እንዳይሆን ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጉ፡፡ ለዚህ ዘመን የሚበጀውን እውነት እያወቁ ለገዛ ቤተ ክርስቲያኖቻቸው ከማካፈል ወደ ኋላ የሚሉና ላልተለወጡት ጎረቤቶቻቸው አገልግሎታቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ የማይሆኑ-ክንዋኔ ማግኘት ላልቻሉት ተግባሮቻቸው ተጠያቂነቱን ይወስዳሉ፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 34.ChSAmh 159.1

    ደቀ መዛሙርቱ በመጀመሪያው የወንጌል ጉዞአቸው እንዲሄዱ የታዘዙት ቀደም ሲል የሱስ ወደ ጎበኛቸውና ወዳጆች ወዳፈራበት ቦታዎች ብቻ ነበር፡፡ ለጉዞአቸው ማድረግ የነበረባቸው ዝግጅት በጣም አነስተኛ መሆን ነበረበት፡፡ አእምሮአቸው በታላቁ ተልዕኮአቸው ላይ እንዳያተኩር ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲዞር የሚያደርግ፣ ወይም ተቃውሞ በማስነሳት ለወደፊት ሥራቸው ዕንቅፋት የሚፈጥር ነገር መኖር አልነበረበትም፡፡ ካኅናት የሚለብሱትን እንዲለብሱ ወይም ከምስኪኑ ተራ ገበሬ የተለዩ የሚያደርጋቸው አለባበስ እንዲኖራቸው አላስፈለገም፡፡ ጥረት እንዲያደርጉ የተፈለገው ከቤት ወደ ቤት እየተዘዋወሩ የጉብኝት ሥራ ለመሥራት እንጂ ወደ ምኩራቦች ገብተው ሕዝብን በመሰብሰብ የጉባዔ ስብከት እንዲያደርጉ አልነበረም፡፡ አስፈላz ባልሆነ ሰላምታ ወይም በየቤቱ እየዞሩ በመብላትና መጠጣት ጊዜ ማባከን አልነበረባቸውም፡፡ ነገር ግን በሚደርሱበት ቦታ ሁሉ አግባብ ያላቸውን ማለትም ራሱን የሱስን እንደጋበዙ በመቁጠር ከልብ የሚቀበሏቸውን ሰዎች ግብዣ መቀበል ይችሉ ነበር፡፡ ወደ ሰዎች መኖሪያ ሲያመሩ “ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን” በሚለው አስደሳች የሰላምታ ቃል መገናኘት ነበራቸው:፡ ያ ቤተሰብ በጸሎታቸው፣ በውዳሴ መዝሙራቸውና ለቤተሰቡ በሚቀርበው የቅዱሳት መጻሕፍት ንባብ ይባረካል፡፡The Desire of Ages, pp. 351, 352.ChSAmh 159.2

    ጎረቤቶቻችሁን ወዳጃዊ በሆነ ስሜት እየጎበኛችሁ መልካም ጉርብትናየሚያስገኘውን ትውውቅ ፍጠሩ. . . በጥቂቶች እንደተስተዋለው ይህን ኃላፊነት ለመውሰድ ችላ የሚሉና ግዴሽነት የሚያሳዩ ብዙም ሳይቆዩ የመጀመሪያውን ፍቅራቸውን የሚያጡ፣ የገዛ ወንድሞቻቸውን የሚገስጹ፣ የሚተቹና የሚኮንኑ ይሆናሉ፡፡-Review and Herald, May 13, 1902.ChSAmh 160.1

    የሐዋርያው ጥረቶች በሕዝብ ፊት ንግግር በማድረግ ብቻ የተወሱ አልነበሩም፡፡ እንዲህ ዓይነቱን አገልግሎት ብቻ በመስጠት ሊደረስባቸው የማይችሉ ብዙዎች አሉ፡፡ ጳውሎስ በቤተሰብ መሃል እየተገኘ ለረጅም ጊዜ የቤት ለቤት አገልግሎት ሰጥቶአል፡፡ የታመሙትን፣ ያዘኑትን፣ የተጎዱትንና የተጨቆኑትን በመጎብኘት ያጽናናቸውና ተስፋቸውን ያለመልም ነበር፡፡ ሐዋርያው እነዚህን ተግባራት ሲያከናውን ከአንደቱ ይወጡ የነበሩ ቃላቶችም ሆኑ ድርጊቶቹ የየሱስን ስም አጉልተው የሚያሳዩ ነበሩ፡፡ ጳውሎስ “በድካምና በፍርሐት፤ እንዲሁም በከባድ መንቀጥቀጥ” አገለገለ፡፡ --The Acts of the Apostles, p. 250.ChSAmh 160.2

    የወገኖች ልብ ከራስ ወዳድነት ተጽእኖ ነጻ በሆነው ፍላጎታችሁና ፍቅራችሁ እስኪሟሟቅ እንድ በአንድ ወደ ጎረቤቶቻችሁ በመሄድ ቅረቧቸው፡፡ አብራችኋቸው እየጸለያችሁ፣ መልካም ልታደርጉላቸው የምትችሉባቸውን ጋጣሚዎችና ዕድሎች እየፈለጋችሁ የድጋፍ ስሜት አሳዩአቸው፡፡ በተቻለ መጠን ጥቂት እየሆናችሁ በመሰባሰብ በጨለማ በተሞላው አእምሮ ውስጥ አምላካዊውን ቃል ክፈቱ፡፡ ስለ ሰዎች ነፍስ ምላሽ የመስጠት ግዴታ ያለበት አማኝበሥነ ምግባራዊው የወይን ተhል ዙሪያ ከእርሱ ጋር የማገልገል ከፍ ያለ ልዩ መብትና ጥቅም ተሰጥቶታል፡፡ “በሚቻለን ሁሉ አንዳንዶችን እናድን ዘንድ” ለጎረቤቶቻችሁከመንገርም ሆነ አቅማችሁ በፈቀደ መጠን ለእነርሱ መልካም ከድረግ ችላ አትበሉ፡፡ ሐዋርያው የቤት ለቤት አገልግሎት እንዲሰጥ የገፋፋውን መንፈስ እኛም አጥብቀን በእንባ በመሻት “በንስሐ ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱና በጌታችን በየሱስ እንዲያምኑ” ልናስተምራቸው ይገባል፡፡Review and Herald March 13, 1888.ChSAmh 160.3

    ጌታ በከተሞቻችን መሠራት የሚኖርባቸውን ሥራዎች አሳይቶኛል፡፡ በእነዚv ከተሞች ውስጥ የሚኖሩ አማኞች በቤቶቻቸው አቅራቢያ የሚገኙ ጎረቤቶቻቸውን እያገለገሉ ለእግዚአብሔር መሥራት ይኖርባቸዋል፡፡ በጸጥታ፣ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው የሚያገለግሉ ይሁኑ፡፡ በሄዱበት ሁሉ ሰማያዊው ድባብ አይለያቸው፡፡-Testimonies, vol. 9, p. 128.ChSAmh 161.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents