Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የመንፈሳዊ መነቃቃትና የግል አገልግሎት ጥምረት

    አባላት ከልብ በመነጨ ስሜት በየግላቸው አምላካዊውን በረከት ያለማቋረጥ ሲሹ በቤተ ክርስቲያን መነቃቃት ይመጣል፡፡ እግዚአብሔርን ሲራቡ፣ ሲጠሙና በእምነት ሲጠይቁ በዚያው መሰረት ይቀበላሉ፡፡ በጽናት ወደ አገልግሎት ስንሄድና በጌታ ላይ ብርቱ የመተማመን ስሜት ሲኖረን-ነፍሳት እንዲህ ያለውን በረከት ለማግኘት ይነሳሳሉ--በዚህም በሰዎች ልብ መነቃቃት እውን የሚሆንበት ወቅት ይመጣል፡፡ ሰፊ የሆነው ሥራ ችላ የመባል አደጋ አይገጥመውም፡፡ ግዙፎቹ እቅዶች ለትክክለኛው ጊዜና ሰዓት ሲተዉ ነገር ግን በወዳጅዎችዎና በዘመዶችዎ ዙሪያ በግል የሚከናወኑ ጥረቶች መገመት ከሚቻለው በላይ ውጤት ያስገኛሉ፡፡ ክርስቶስ የሞተላቸው ነፍሳት እየጠፉ የሚገኙት እንዲህ ዓይነቱን አገልግሎት በመሻት ነው፡፡ ChSAmh 167.1

    ቀራኒዮ አንድ ነፍስ ዘላለማዊ ዋጋ እንዳለው ይነግረናል፡፡ አንድን ነፍስ ለእውነት ማሸነፍ ሌሎችን ለማሸነፍ የሚያስችል መሣሪያና በየጊዜው እየጨመረና እያደገ የሚሄድ የበረከትና የደኅንነት ውጤት ማስገኛ ነው፡፡ አያሌዎች የሚታደሙበት ስብሰባና ጉባዔ ሰዎችን በግል ለመገናኘት ከተሳነው የእርስዎ ሥራ የላቀ፣ ተጨባጭና አመርቂ ውጤት ማምጣት ይችላል፡፡ ነገር ግን ጉባዔ መር መርኅ ግብር ነፍሳትን በግል መገናኘት ችሎ ሁለቱ ኅብረት መፍጠር ከቻሉ የእግዚአብሔር በረከት ታክሎበት ይበልጥ ፍጹምና ብልሃት የታከለበት የሥራ ዕቅድ ማውጣት ይቻላል፡፡ በአንደኛው ክፍል ብቻ የምንገደብ ከሆነ ግን አማኙ በግሉ በቤት ለቤት አıልግሎት መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ፣ ክርስቶስን እንዲቀበሉ ጥሪ በማቅረብና ከየቤተሰቡ አባላት ጋር የቀረበ ትስስር በመፍጠር ከንቱ ስለሆኑት ዓለማዊ ጉዮች ሳይሆን ነገር ግን ስለ ታላላቆቹ የመዋጀታችን ርዕሰ ጉዳዮች ሊነጋገር ይገባል፡፡ ልብዎ ስለ ነፍሳት ደኅንነት ብርቱ ሸክም የሚሰማው የመሆኑን እውነታ ሌሎች መመልከት የሚችሉ ይሁኑ፡፡-Review and Herald, March 13, 1888.ChSAmh 167.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents