Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 25—መንፈስ ቅዱስ የመንፈh ቅዱስ ተስፋ

    የመንፈስ ቅዱስ ተስፋ

    እንደ መጀመሪያዎቹ ደቀ መዛሙርት ሁሉ ለእኛ ለዛሬዎቹም ተሰጥቶአል፡፡ በጴንጤቆስጤ ቀን ሰዎች የመዳንን ቃል እንደሰሙ ሁሉ እግዚአብሔር የዚህን ዘመን ወንዶችና ሴቶች ከላይ በሚላክ ኃይል ይሞላቸዋል፡፡ በዚህ ሰዓትና ጊዜ የእግዚአብሔርን መንፈስና ጸጋ ለሚሹ ሁሉ እነሆ በቃሉ መሰረት ተሰጥቶአቸዋል፡፡Testimonies, vol. 8, p. 20.ChSAmh 347.1

    የመንፈስ ቅዱስ ተስፋ ለተወሰነ ዘመን ወይም ዘር ተወስኖ የተሰጠ አይደለም፡፡ የመንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ ተጽእኖ እስከ መጨረሻው ድረስ ከተከታዮቹ ጋር እንደሚኖር ክርስቶስ አጽንኦት ሰጥቶ ተናግሮአል፡፡ አጽናኙ ከጴንጤቆስጤ ዕለት አንስቶ እስከ ዛሬ ድረስ ራሳቸውን ሙሉ ለሙሉ ለጌታና ለአገልግሎቱ ለሚያስገዙ ሁሉ ተልኮአል፡፡--The Acts of the Apostles, p. 40.ChSAmh 347.2

    እግዚአብሔር ሕዝቡን በመንፈስ ቅዱስ ስጦታ እንደ አዲስ በፍቅሩ እያጠመቀ ሊያድሳቸው ይመኛል፡፡ በቤተ ክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ እጦት ሊኖር አይገባም፡፡ ክርስቶስ ካረገ በኋላ መንፈስ ቅዱስ ተግተው ይጠባበቁ በነበሩ፣ በሚጸልዩ አማኝ ደቀ መዛሙርት ላይ በሙላትና በኃይል በመውረድ ወደ እያንዳንዱ ልብ ደረሰ፡፡ ወደፊት ምድር ከእግዚአብሔር ክብር የተነሳ ታበራለች፡፡ መለኮታዊው ተጽእኖ ራሳቸውን በእውነት በቀደሱ ወገኖች አማካይነት ለዓለም ይሰራጫል፡፡ምድር በአምላካዊው ጸጋ ሙላት ትከበባለች፡: መንፈስ ቅዱስ በሰዎች ልብ ውስጥ በመሥራት የእግዚአብሔር የሆኑትን ነገሮች እየወሰደ ለሰዎች ያሳያል፡፡ Southern Watchman, Sept. 5, 1905.ChSAmh 347.3

    የምድር መጨረሻ እውን ሆኖ የእግዚአብሔር ሥራ ሲደመደም በልዩ ልዩ ድንቃድንቆችና ምልክቶች የታጀቡ ጽኑ ጥረቶች በመንፈስ ቅዱስ ምሪት ራሳቸውን ለአገልግሎት ቀድሰው በሰጡ ሰዎች ይፋ ይሆናሉ፡፡ በምሥራቁ ዓለም የእርሻ ወቅት በዘር መዝሪያና በምርት መዳረሻ ላይ የመጀመሪያውና ሁለተኛው ዝናብ ይዘንባል፡፡ የዕብራውያን ነቢያት ይህን ተጨባጭ ሁኔታ በእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ላይ ከሚወርደው መጠነ ሰፊ መንፈሳዊ ስጦታ ጋር በማያያዝ በተምሳሌታዊ አነጋገር በትንቢት አቅርበዋል፡፡ በታላቅ ክብር የተሞላው _ በሐዋርያት ዘመን የወረደው የመጀመሪው የመንፈስ ቅዱስ ዝናብ መፍሰስ—የአምላካዊው ድንቅ ስጦታ ጅማሮ ነበር፡፡ መንፈስ ቅዱስ የምድር ታሪክ እስከሚደመደም በእውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን ይኖራል፡፡The Acts of the Apostles, pp. 54, 55. ChSAmh 348.1

    “የፊተኛው ዝናብ በመባል የሚታወቀው በሐዋርያት ዘመን የተስተዋለው የመንፈስ ቅዱስ መፍሰስ ውጤቱ እጹብ ድንቅ ነበር፡፡ ሆኖም የኋለኛው ዝናብ ምድሪቱን እጅግ አትረፍርፎ የሚያረሰርስ ይሆናል፡፡ ለመሆኑ ለመጨረሻው ዘመን የእግዚአብሔር ሕዝቦች ምን ዓይነት ተስፋ ተሰጥቶአል? “እናንተ በተስፋ የምትኖሩ እስረኞች፤ ወደ ምሽጎቻችሁ ተመለሱ፤ አሁንም ቢሆን ሁለት እጥፍ አድርጌ እንደምመልሳችሁ እናገራለሁ፡፡” “በኋለኛው ዝናብ ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ ዝናቡን ለምኑ፤ እግዚአብሔር መብረቅ ያደርጋል፤ እርሱም የበልግ ዝናብን፤ ለእያንዳንዱም በሜዳ ውስጥ ሣርን ይሰጣል” (ከ1962 ትርጉም የተወሰደ) Testimonies, vol. 8, p. 21. ChSAmh 348.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents