Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ከጉባዔው መቅረት ለብርቱ እጦት ይዳርጋል

    የወንጌል ጉባዔዎቻችን ከፍ ባለ ወጪ የሚዘጋጁና የሚቀርቡ ናቸው፡፡ የተጠላውን እውነት የሚሞግቱ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የምኅረትን መልእክት ከተሰቀለው አዳኝ ወደ ምስኪኑ ሰብዓዊ ፍጡር ለማፍሰስ በታላላቆቹ ጉባዔዎች ከመጠን በላይ ይሠራሉ፡፡ እነዚህን መልእክቶች ችላ ማለት ወይም ለመልእክቶቹ ግዴለሽ መሆን የእግዚአብሔርን ምኅረት፣ የማስጠንቀቂያ ድምጹንና ተማጽኖውን አሳንሶ መመልከት ነው፡፡ እነዚህን ጉባዔዎች አለመካፈል በመንፈሳዊው ማንነት ላይ ጎጂ ተጽእኖ አለው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ሲሰበክ በጉባዔው ይገኝ የነበረ መንፈሳዊ ብርታት ከመታጣቱ በተጨማሪ ከእውነት አማኞች ጋር ሊኖር ይገባ የነበረ ኅብረት ይጠፋል፡፡Testimonies, vol. 4, p. 115.ChSAmh 273.2

    አንድ ቤተሰብ በማያምን ማኅበረሰብ መሃል የእግዚአብሔርን ትእዛዛት እየጠበቀ የየሱስ ተወካይ ሆኖ መቆሙ በዋዛ የሚታይ አይደለም፡፡ እኛ ለሰዎች ሁሉ የሚታወቅና የሚነበብ ሕያው ቃል እንድንሆን እንጠየቃለን፡፡ ይህ ሥልጣን አስፈሪ ኃላፊነቶችን ይዞአል፡፡ በብርሐን ውስጥ ለመኖር ብርሐኑ ወዳለበት ስፍራ መምጣት የግድ ይሆናል፡፡ ማንም ቢሆን ተገቢውን መሥዋዕትነት ከፍሎ በዓመት አንድ ጊዜ እውነትን በሚወዱ ወገኖች በሚካሄደው ጉባዔ ላይ ከቤተሰቡ ጋር የመገኘት የተከበረ ግዴታ ሊሰማው ይገባል፡፡ በጉባዔው መገኘት ብርታት ከማምጣቱ በተጨማሪ በፈተና እንድንዘልቅና ኃላፊነታችንን እንድንወጣ ይረዳናል፡፡ ከአማኞች ጋር በአንድነት የማምለክ ልዩ መብትና ጥቅም ማጣት ብርቱ ጉዳት አለው፡፡ እውነት በአእምሮ ውስጥ ይዞ የነበረውን አስፈላጊ ስፍራ ሲያጣ ልብ በሚቀድስ ተጽእኖው ያገኝ የነበረውን ስርጸትና ሕያው መነቃቃት ያጣል፣ መንፈሳዊ ሕይወትም ከግለሰቡ ይርቃል፡፡ በሰባኪው ከሚቀርበው አምላካዊ ቃል ብርታት ማግኘት አይችልም፡፡ አእምሮ ባለማቋረጥ የሚለማመደው ከመንፈሳዊው ርዕሰ ጉዳይ የተነጠለውን ዓለማዊ አስተሳሰብና እንቅስቃሴ ብቻ ይሆናል፡፡Testimonies, vol. 4, p. 106.ChSAmh 273.3

    ሁሉም ሰው በተቻለው መጠን ከዓመታዊ ጉባዔዎች አይቅር፡፡ በጉባዔው ላይ ይገኙ ዘንድ እግዚአብሔር እንደሚጠይቃቸው ይሰማቸው፡፡ እግዚአብሔር ወደ አዘጋጀላቸው ጉባዔ በመምጣት በእርሱ የሚበረቱበትና የጸጋው ኃይል ተጋሪ መሆን የሚችሉበት ልዩ መብትና ጥቅም ለማግኘት ፈቃደኞች ካልሆኑ፤ መንፈሳዊ ህይወታቸው እየተዳከመ በመሄድ ውሎ አድሮ ሁሉንም ነገር ለእርሱ ቀድሶ የመስጠት ምኞት ያጣሉ፡፡ ChSAmh 274.1

    ወንድሞችና እህቶችየሱስን መገናኘት እንድትችሉ ወደ እዚህ የተቀደሰ ጉባዔ ኑ፡፡ እርሱ ወደ ግብዣው ስፍራ መጥቶ አብልጣችሁ ክንውን እንዲያገኝ የምትሹትን ነገር ይፈጽምላችኋል፡፡ የግብርና ሥራችሁ ከፍ ካለው ከነፍሳት ደኅንነት በላቀ የከበረ ሆኖ መታየት የለበትም፡፡ ሐብታችሁ የቱንም ያህል የተትረፈረፈ ቢሆን፤ ዘላለማዊ ጥቅም የሚሆናችሁን ተስፋና ሰላም ሊገዛላችሁ የሚችል አቅም የለውም፡፡ ስለ ዘላለማዊ ነገሮች ጠንካራና ግልጽ ስሜት ሲኖረን ልባችን ለክርስቶስ ለመገዛት ፈቃደኛ ይሆናል፣ ከማንኛውም ምድራዊ ሐብት፣ ደስታና ክብር በላቀ የከበረ በረከት ባለቤት እንሆናለን፡፡Testimonies, vol. 2, pp. 575, 576. ChSAmh 274.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents