Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የመዝሙር አገልግሎት

    ጣፋጭ የሆነውን የወንጌል የውዳሴ ቃና ከነልዩ ባህሪው የቀሰሙ ተማሪዎች በዘማሪ ወንጌላውያንነት የላቀ መልካም አገልግሎት መስጠት ይችላሉ፡፡ በቤተ ክርስቲያን በመዘምራን መካከል አምልኮ የማድረግ ዕድሉን ማግኘት ወዳልቻሉ አያሌ ብቸኛ ስፍራዎች እንዲሁም በአስቸጋሪ ሁናቴና በሐዘን ወደ ተዋጡ ወገኖች በመጓዝ እግዚአብሔር በሰጣቸው መክሊት ዜማና የጸሐይ ጮራ ይፈንጥቁ፡፡ ተማሪዎች ወደ አውራ ጎዳናውም ሆነ ወደ የጥጋቱ ሂዱ፡፡ ጥረታችሁ ከፍ ያለውንም ሆነ በዝቅታ የሚኖረውን የኅብረተሰብ ክፍል ያካተተ ይሁን፡፡ የሐብታሞችንም ሆነ የድኾችን ደጃፍ አልፋችሁ የምትገቡበትን ዕድል ስታገኙ “ጥቂት የወንጌል መዝሙሮችን ብንዘምርላችሁ ደስተኞች ናችሁ?” ብላችሁ ጠይቁ፡፡ የልቦች መለሳለስ እግዚአብሔር በዚያ የሚገኝበትን ጥቂት የጸሎት ቃላት ለመሰንዘር የሚያስችል በር ሊከፍት ይችላል፡፡ ይv ልባዊ የወንጌላዊ አገልግሎት እንደመሆኑ ብዙዎች መዝሙር ለመስማት ተቃውሞ አይኖራቸውም፡፡--Counsels to Teachers, pp. 547, 548.ChSAmh 92.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents