Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    አግባብነት የሌላቸው ምክንያቶች

    የሱስ እያንዳንዱ ሰው የሚሠራውን ሥራ ትቶ ወደ ሰማይ እንደማረጉ--የሚሠራ ሥራ የለም የሚለው አባባል አግባብነት የሌለው ምክንያት ነው፡፡ የሚሠራ የለም የተሰኘው አባባል በወንድሞች መካከል ለሚከሰት ፈተና ዓይነተኛ መንስኤ ነው፡፡ ሰይጣን የሥራ ፈቶችን አእምሮ በራሱ ዕቅዶች በመሙላት እርሱ ባሻው መንገድ እንዲሄዱ ያደርጋል. . . ይህ አባባል በወንድሞች ላይ ክፉ ምስክርነት-- ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ጸብ እንዲነሳ መንስኤ ይሆናል፡፡ “ከእኔ ጋር የማይሰበስብ ይበትናል”፡፡- Review and Herald, March 13, 1888.ChSAmh 149.1

    ወንድሞችና እህቶች ሆይ! አብዛኞቻችሁ ለሌሎች አገልግሎት ለመስጠት ችሎታ እንደሚያንሳችሁ አድርጋችሁ ለራሳችሁ ምክንያት ትሰጣላችሁ፡፡ ለመሆኑ እግዚአብሔር ብቃት የሌላችሁ አድርጎ ፈጥሮአችኋል? ያለ መቻሉ መንስኤ የራሳችሁ ከእንቅስቃሴ መታቀብና የግል ምርጫ አይደለምን? ለራሳችሁ ምቾትና ደስታ ሳይሆን ነገር ግን ለእርሱ አገልግሎት ልታበለጽጉ የምትችሉት ቢያንስ አንድ እንኳ መክሊት አልተሰጣችሁምን? ለእርሱ ለመሥራት የተቀጠራችሁ ሠራተኞች እንደመሆናችሁ እንድታተርፉ የተሰጣችሁን አደራ ጥበብና ችሎታችሁን ተጠቅማችሁ የማትረፍ ግዴታችሁን ተገንዝባችኋልን? ያላችሁን ተሰጥኦ ማጎልበት የምትችሉባቸውን ዕድሎች ችላ አላላችሁምን? ጥቂቶች በእግዚአብሔር የተጣለባቸው ኃላፊነት አንዳችም ስሜት የማይሰጣቸው መሆኑ እሙን ነው::--Testimonies, vol. 5, p. 457.ChSAmh 149.2

    አንዳንዶች ሕይወታቸው በሥራ የተሞላ፣ በንግድ እንቅስቃሴ የተጣበበ በመሆኑ ለነፍሳት ደኅንነትም ሆነ የአዳኛቸውን ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ አንዳችም ማድረግ እንደማይችሉ አድርገው ያስባሉ፡፡ በግማሽ ልብ ምንም መሥራት እንደማይችሉ በመናገ ፊቶቻቸውን ከኃይማኖታዊ ግዴታዎችና ልምምዶች በመመለስ ራሳቸውን በምድራዊው ነገር ውስጥ ይቀብራሉ፡፡ ለንግድ ሥራቸው ቅድሚያ በመስጠት እግዚአብሔርን ስለሚረሱ አምላካቸው በእነርሱ ደስ አይሰኝም፡፡ አምላካዊውን አገልግሎት ከመስጠት፣ በቅድስና ሕይወት ከመመላለስና እግዚአብሔርን ከመፍራት በሚያግደው የንግድ ሥራ ውስጥ የሚገኝ ምንም ሰው ይህን ሥራ አቁሞ የሱስን በየሰዓቱ ሊገናኝ በሚያስችለው የንግድ ሥራ ይሰማራ፡፡-Testimonies, vol. 2, pp. 233, 234.ChSAmh 149.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents