Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ብልሃትና ቅልጥፍና

    እያንዳንዱ ክርስቲያን ሥርዓት፣ ምሉዕነትና ቅልጥፍና ሊኖረው ይገባል፡፡ ተድበስብሶ ለሚሠራና ዝግ ላለ አገልግሎት አንዳችም ምክንያት መቅረብ አይችልም፡፡ አንድ ሰው ሁልጊዜ በሥራ ላይ ሆኖ ነገር ግን ሥራው ፈቅ የማይል ከሆነ አእምሮውና ልቡ በአንድ አልተጠመዱም፡፡ ዝግ ያለና እመርታ ቢስ አገልግሎት የሚሰጥ ሰው ጉድለቶች ሊታረሙ እንደሚገባ መገንዘብ ይኖርበታል፡፡ ምርጥ ውጤት ሊያስገኝለት በሚችል መልኩ ጊዜውን እንዴት ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚኖርበት ዕቅድ በማውጣት አእምሮውን ማለማድ ይርበታል፡፡ አንዳንዶች ዘዴና ብልሃት ተጠቅመው ሌላው አሥር ሰዓት የሚፈጅበትን ሥራ በአምስት ሰዓታት ብቻ ያቀላጥፋሉ፡፡ የአገር ውስጥ አገልግሎት የሚሰጡ ሰዎች አብዛኛውን ስኬታማ የርስቲያን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ብታት ማጎልቻዎች ጊዜአቸውን የሚያጠፉት ሥራ ላይ ነው፡፡ ለዚህ መንስኤው የሚሠሩት ሥራ ሰፊነት ሳይሆን ነገር ግን ጊዜ ለመቆጠብ በሚያስችላቸው መልኩ ዕቅድ ስለማያወጡ ነው፡፡ ቀርፋፋና ዝግ ያለ ዘዴ የሚጠቀሙ በመሆናቸው ከብዙው መሃል እጅግ አነስተኛውን ብቻ ይሠራሉ፡፡ ነገር ግን ሁሉም ይህን የተዘበራረቀ ቀርፋፋ ልማድ ማሸነፍ ይችላሉ፡፡ በሥራቸው ግልጽ ሆኖ የተቀመጠ ዓላማና ግብ ይኑራቸው፡፡ ሊሠራ የታቀደውን ሥራ ለማከናወን የሚፈጀውን ጊዜ ወስኖ በማስቀመጥ በተባለው ጊዜ ለማጠናቀቅ እያንዳንዱ ጥረት ይደረግ፡፡ ቆራጥነት እንዲኖር ልምምድ ማድረግ እጆቻችን በቅልጥፍን እንዲሠሩ ያስችላቸዋል፡፡--Christ’s Object Lessons, p. 344. ChSAmh 328.1

    የክርስቶስ አገልግሎት ፈጣን መታዘዝን ይጠይቃል፡፡-Southern Watchman, Aug. 9, 1904. ChSAmh 329.1

    ነፍሳት ምን ያህል የከበረ ዋጋ እንዳላቸው በፍጥነት የሚሰማቸው፣ መስጠት የሚኖርባቸውን የአገልግሎት ዓይነት በቅጽበት ለይተው የሚረዱና ጌታ በእነርሱ ላይ ያኖረውን ኃላፊነት ለመወጣት ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ መንፈስ በአገልጋዮቹ መሃል እንዲኖር ይጠይቃል፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 123. ChSAmh 329.2

    እግዚአብሔር እንድንሠራ ለመደበልን ሥራ ታማኝ መሆን የእውነተኛ አገልግሎት እጅግ አስፈላጊ ክፍል ነው፡፡ ሰዎች እንደ እግዚአብሔር መሣሪያነታቸው የእርሱን ፈቃድ ለመፈጸም የሚያስችላቸውን ድርሻ ሊወስዱ ይገባል፡፡ መዘግየትና ቸልተኝነት ውድቀት ከማከተል አልፎ አምላካዊውን ክብር ዝቅ ሲያደርግ-በትክክለኛው ሰዓትና ጊዜ የሚከወን ፈጣንና ወሳኝ ድርጊት ደግሞ ባለ ክብር ድል ይቀዳጃል፡፡--Prophets and Kings, p. 676.ChSAmh 329.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents