Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የሕክምና ባለሙያ ወንጌላውያን

    የሕhምና ባለሙያዎች የሆኑ ወንጌላውያን አሁኑኑ ያስፈልጉናል፡፡ እነዚህን ባለሙያዎች ለማዘጋጀት ዓመታት ሊባhኑ አይገባም፡፡ ነፍሳት እውነት ይቀበሉ ዘንድ አሁን ወለል ብሎ የተከፈተው በር ለዘላለም የሚዘጋበት ጊዜ እሩቅ አይደለም፡፡ አሁኑኑ መልእhቱን ይዛችሁ ሂዱ እንጂ ከፊታችሁ ያሉትን ከፍት የእርሻ ስፍራዎች ጠላት ርስቱ እስኪያደርጋቸው አትጠብቁ፡፡ አነስተኛ አባላት ያሏቸው የጥናት ቡድኖች ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጣቸውን ሥራ ለመሥራት ወደ ፊት ይገስግሱ፡፡ በራሪ መንፈሳዊ ጽሑፎቻችንን በማደልና ላገኗቸው ሁሉ እውነትን በመንገር የወንጌላውያንን ሥራ ይሥሩ፡፡ መድኃኒት በመስጠት ፋንታ ለታመሙት መጸለይ፣ በሚያስፈልጋቸው ማገልገል፣ ተፈጥሮአዊ መፍትሔዎችን እየሰጡ በሽታን እንዴት ማስወገድ እንደሚችሉ የምክር አገልግሎት መስጠትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ሊሠሩ ይገባል፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 172. ChSAmh 176.4

    ወንድሞቼና እህቶቼ-ራሳችሁን ለጌታ አገልግሎት አሳልፋችሁ ስጡ፡፡ እጃችሁ የገባውን አጋጣሚ ሳትጠቀሙበት እንዲያልፍ አትፍቀዱ፡፡ የታመሙትንና በሥቃይ የሚገኙትን ወገኖች እየጎበኛችሁ ለእነርሱ ያላችሁን በጎ ፍላጎት አሳዩአቸው፡፡ ነገሮች በተመቻቹላችሁ ቁጥር ይበልጥ ምቾት ሊሰጧቸው የሚችሉትን ነገሮች አድርጉላቸው፡፡ እነዚህን መንገዶች በመጠቀም ወደ ልባቸው መድረስና ስለ hርስቶስ አንዳች ቃል ማካፈል ትችላላችሁ፡፡ ይህ የአገልግሎት ዘርፍ ምን ያህል ውጤት ማስገኘት የሚችል መሆኑን ዘላለማዊነት ብቻ ወደፊት የሚገልጸው ይሆናል፡፡ ጠቀሜታ ባላቸው በሌሎች ዘርፎች አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኞች የሚሆኑ ሁሉ እነሆ ከፊት ለፊታቸው እርሱን የሚጠብቁ ሥራዎች አሉ፡፡--Testimonies, vol. 9, p. 36. ChSAmh 177.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents