Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    መንፈስ ቅዱስ ለመቀበል የሚያስችሉን ሁናቴዎች

    የሕይወት እንጀራን ለጎረቤቶቻቸው ለመቁረስ ለሚለምኑ ሁሉ መንፈስ ቅዱስ ይፈስላቸዋል፡፡Testimonies, vol. 6, p. 90.ChSAmh 349.4

    ልባችንን ወደ ክርስቶስ ሕብረት ስናመጣና ሕይወታችንን ከእርሱ አገልግሎት ጋር ስምሙ ስናደርግ በጴንጤቆስጤ ቀን በደቀ መዛሙርቱ ላይ የወረደው መንፈስ በእኛም ላይ ይወርዳል፡፡-Testimonies, vol. 8, p. 246.ChSAmh 349.5

    አምላካዊው ጸጋ ተትረፍርፎ በምድር ነዋሪው ሰብዓዊ ፍጡር ላይ ያልፈሰሰው በእግዚአብሔር በኩል አንዳች ገደብ በመኖሩ አይደለም፡፡ Christ’s Object Lessons, p. 419. ChSAmh 350.1

    መንፈስ የእኛን ፍላጎትና የመቀበል ዝግጁነት ይጠባበቃል፡፡-Christ’s Object Lessons, p. 121. ChSAmh 350.2

    ኃይል የምንቀበልበት ዓይነተኛ መንገድ የሆነውን የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ የማንራበውና የማንጠማው ለምንድን ነው? ስለ መንፈስ ቅዱስ የማናወራው፣ የማንጸልየውና የማንሰብከው ለምን ይሆን?—The Acts of the Apostles, p. 50. ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጠው ተስፋ እውን በሆን ፋንታ ሲፈጸም መመልከት የማንችል ከሆነ ለተሰጠው ተስፋ ተገቢውን ዋጋም ሆነ ከበሬታ መስጠት አልቻልንም ማለት ነው፡፡ የእኛ የሁላችን ፈቃድ ቢሆን፤ በመንፈስ ቅዱስ በተሞላን ነበር፡፡ —The Acts of the Apostles, p. 50. ChSAmh 350.3

    በየዕለቱ በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ እንድንችል እያንዳንዱ ሠራተኛ እግዚአብሔርን ይለምን፡፡ _ ክርስቲያን ሠራተኞች እንዴት ዕቅድ ማውጣትና ዕቅዳቸውን በብልሃት መተግበር እንዳለባቸው የተለየ ዕርዳታ የሚያገኙበትን ሰማያዊ ጥበብ ለጠየቅ በአንድነት ይሰባሰቡ፡፡ በተለይ እግዚአብሔር በሰበካዎች የተመረጡ አምባሳደሮቹን በመንፈስ ቅዱስ እንዲያጠምቅ ሊጸልዩላቸው ይገባል፡፡The Acts of the Apostles, pp. 50, 51. ChSAmh 350.4

    ክርስቲያኖች ከማንኛውም ጠብ የራቁና የጠፉት እንዲድኑ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር የሰጡ ይሁኑ፡፡ ስለ መንፈስ ቅዱስ የተሰጠው ተስፋ እንዲፈጸም በእምነት ሲጠይቁ በእርግጥም ተስፋው ፍጻሜ ያገኛል፡፡-- Testimonies, vol. 8, p. 21. ChSAmh 350.5

    የነፍሳት ሸክም ያደቀቃቸው ደቀ መዛሙርት ለራሳቸው ብቻ በረhት ለመቀበል አልጸለዩም፡፡ ይልቁንም ክርስቶስ ቃል በገባው መሰረት ወንጌልእስከ ምድር ዳርቻ የሚሰራጭበትን የመንፈስ ቅዱስ በኃይል መውረድ ተግተው ተጠባበቁ፡፡ ከዚያም መንፈስ ቅዱስ በኃይል ወረደ፣ በሺ የሚቆጠሩ ነፍሳትም በአንድ ቀን ጌታን ተቀብለው ተለወጡ፡፡--Southern Watchman, Aug. 1, 1905. ChSAmh 351.1

    ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያኑ መንፈስ ቅዱስን እንደሚሰጥ በገባው ቃል መሰረት ለመጀመሪያዎቹ ሐዋርያት የተሰጠው ተስፋ ለእኛም ተሰጥቶአል፡፡ ሆኖም ይህ ተስፋ በሁናቴዎች ላይ እንዲወሰን የሚያደርግ ግዴታ አለበት፡፡ ጌታ የሰጠውን ተስፋ የሚያምኑና አለን ብለው የሚናገሩ ብዙዎች አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ስለ ክርስቶስና ስለ መንፈስ ቅዱስ ቢናገሩም ነገር ግን ህይወታቸውን መለኮት እንዲመራውና እንዲቆጣጠረው _ ስለማያስገ የሚያገኙት ጥቅም የለም፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሊጠቀምብን ይገባል እንጂ እኛ ልንጠቀምበት አንችልም፡፡ እግዚአብሔር በመንፈሱ አማካይነት “እንደ በጎ ፈቃዱ መፈለግንና ማድረግን” በሕዝቡ ውስጥ ይሠራል፡፡ ነገር ግን ብዙዎች ራሳቸውን ለዚህ አያስገዙም፡፡ ራሳቸውን በራሳቸው ለመምራት ስለሚፈልጉ ሰማያዊውን ስጦታ አያገኙም፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠው በትvትና እግዚአብሔርን ለሚጠባበቁና አመራሩንና ጸጋውን ለማግኘት ለሚሹ ብቻ ነው፡፡ እግዚአብሔር ኃይሉን ለመስጠት የሰዎችን የመቀበል ፍላጎትና ዝግጁነት ይጠባበቃል፡፡ ይህ በእምነት የግላችን ልናደርገው የምንችል የበረከት ተስፋ ሌሎች በረከቶችን ሁሉ ያስገኝልናል፡፡ እንደ ክርስቶስ ባለጸግነት ብዛት የሚሰጠው ይህ ስጦታ እያንዳንዱ ነፍስ ለመቀበል በሚችለው መጠን ተዘጋጅቶአል፡: The Desire of Ages, p. 672. ChSAmh 351.2

    ከእግዚአብሔር ጋር የመሥራት ተሞክሮና ስርጸት ያላቸውን ሕዝቦች እስክናፈራ ድረስ መላውን ዓለም በእርሱ ክብር የሚሞላው የእግዚአብሔር መንፈስ በታላቅ ኃይል መፍሰስ አይችልም፡፡ ራሳቸውን በሙሉ ልብ ለክርስቶስ አገልግሎት ቀድሰው የሰጡ ሰዎችን ስናፈራ እግዚአብሔር በተጨባጭ መንፈሱን አትረፍርፎ ማፍሰስ እንደሚኖርበት ያውቃል፡፡ ነገር ግን ከፍተኛ ቁጥር የያዘው የቤተ ክርስቲያን አባል ከእግዚአብሔር ጋር ሠራተኛ ባልሆነበት ሁናቴ ይህ ተግባራዊ መሆን አይችልም:፡Review and Herald, July 21, 1896. ChSAmh 351.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents