Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ዘዴኛ መሆን

    ራሳቸውን ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር የሚሰጡ አስተሳሰባቸውን፣ ጸሎታቸውንና ጽናታቸውን ቀድሰው በብልሃትና ጥንቃቄ ለአገልግሎት ያስረክባሉ፡፡Signs of the Times, May 29, 1893.ChSAmh 318.3

    አንድ ሰው ዘዴኛ፣ አምራችና ብርቱ ጉጉት ሲኖረው ውሎ አድሮ በሥራው ስኬታማ የማይሆንበት ምክንያት አይኖርም፡፡ ከዚህ ተመሳሳይ ግብአት ለእግዚአብሔር ሥራ ተቀድሶ _ ሲውል መለኮታዊው ኃይል ከሰብዓዊው ጥረት ጋር በሚፈጥረው ጥምረት በእጥፍ የላቀ ውጤት ይገኛል፡፡ Testimonies, vol. 5, p. 276.ChSAmh 318.4

    ነፍሳትን ለማሸነፍ ለአገልግሎት ስንወጣ ታላቅ ዘዴና ጥበብ ሊኖረንየግድ ነው፡፡ አዳኙ ሁልጊዜም እውነትን በፍቅር ከመናገር በቀር አድበስብሶ አልፎ አያውቅም፡፡ ሁል ጊዜ ደግና ቅን አሳቢ የነበረው የሱስ ከሌሎች ጋር ይፈጥር በነበረው ግንኙነት ከፍ ያለውን ዘዴና ብልሃት ጥቅም ላይ ያውል ነበር፡፡ ሰዎችን ከትህትና ውጪ ቀርቦ የማያውቀው ጌታ እጅግ አስፈላጊ ካልሆነ በቀር ጠንካራ ቃል ተናግሮ ወይም ለሆደ ባሻው ነፍስ አላስፈላጊ ህመም ሰጥቶ አያውቅም፡፡ ሰብዓዊውን ደካማነት አልተቸም፡፡ ሆኖም ግብዝነትን፣ አለማመንንና እርክስናን ያለ ፍርሐት ቢያወግዝም ነገር ግን ይህን ግሳጼ ሲሰጥ የርኅራኄ ሳግ እያነቀው ነበር፡፡ እርሱ እውነትን ያቀርብ የነበረው በጥልቅ ርኅራኄና ደግነት እንጂ ጨካኝ አድርጎ _ አቅርቦ አያውቅም፡፡ እያንዳንዱ ነፍስ በፊቱ የከበረ ስፍራ ነበረው፡፡ ክርስቶስ መለኮታዊ ባሕሪ ቢኖረውም ነገር ግን በቅንነትና በርኅራኄ ራሱን በእያንዳንዱ የእግዚአብሔር ቤተሰብ ፊት ዝቅ አደረገ፡፡ ጌታ የማዳን ተልእኮውን በእያንዳንዱ ነፍስ ውስጥ ተመልክቶ ነበር፡፡Gospel Workers, p. 117.ChSAmh 319.1

    እንዳንዶች ታማኝ ቢሆኑም ነገር ግን ችኩልና በስሜት የሚገፋፋ ስብዕና የተላበሱ በመሆናቸው ስለ አንድ ርዕሰ ጉዳይ ንግግር ከተደረገ በኋላ ሳይታሰብ በድንገት የእኛን እምነት ለማይጋሩ የሚያቀርቡት የሰዎችን ስሜት የማይጠብቅ፣ ተጋፊና አላዋቂ አነጋገር ነፍሳት እንዲቀበሉት የምንጓጓለት እውነት የማያስደስትና የሚያርቅ ስሜት ይፈጥርባቸዋል፡፡ “የዚv ዓለም ልጆች ከመሰሎቻቸው ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ከብርሃን ልጆች ይልቅ ብልሆች ናቸውና፡፡” በንግድ ዓለም የተሰማሩ ባለሙያዎችና ፖለቲከኞች ስለ በጎ ምግባርና ይሉኝታ ትምህርት ይቀስማሉ፡፡ ስብዕናቸው በተቻለ በሌሎች ፊት መስvብነት እንዲኖረው አድርጎ ማቅረብ አጥብቀው የሚከተሉት መርኅ ነው፡፡ አድማጮቻቸው ስለ _ እነርሱ _ መልካም አመለካከት እንዲኖራቸውበአእምሮአቸው ላይ ብርቱ ተጽእኖ ለማሳረፍ የሚያስችላቸውን አነጋገርና ሥነ ምግባር ያጠናሉ፡፡ ዓላማቸውን ከግብ ለማድረስ በተቻላቸው መጠን ዕውቀታቸውንና ችሎታቸውን በብልሃትይጠቀማሉ፡፡Testimonies, vol. 4, p. 68.ChSAmh 319.2

    ይህ መልዕክት ለዓለም መቅረቡ የግድ ቢሆንም ነገር ግን መልእክቱን ስናስተላልፍ ብርሐን የሌላቸውን ወገኖች እንዳንጫን፣ እንዳናጨናንቅና እንዳንኮንን አጥብቀን መጠንቀቅ ይኖርብናል፡፡ የካቶሊክ እምነት ተከታይ ወንድም እህቶች ላይ ፈር የለቀቀ ጫና ማድረግ የለብንም፡፡ ከካቶሊኮች መሃል በበራላቸው ብርሃን የሚመላለሱ እግዚአብሔር በእነርሱ አማካይነት የሚሠራ ማስተዋል ያላቸው አያሌ ክርስቲያኖች አሉ፡፡-Testimonies, vol. 9, p. 243. ChSAmh 320.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents