Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ርኅራኄና ተግባቢነት

    በማንኛውም አምላካዊ የአገልግሎት ዘርፍ የሰብዓዊውን ፍጡር ወዮታ የሚካፈሉ ርኅሩኅ ወንዶችና ሴቶች ሊኖሩ የተገባ ቢሆንም ነገር ግን ይህ የሌላውን ስሜት የመጋራት አካሄድ እምብዛም አይስተዋልም፡፡-Review and Herald, May 6, 1890.ChSAmh 321.3

    በክርስቶስ የተገለጠው የደግነትና ርኅራኄ በእኛም ውስጥ ሊኖር የግድ ነው፡፡ ደግነታችን በፊታችን መልካም መስለው ለመቅረብ ለሚሞክሩ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ጭልጥ ባለ ስህተት እየተወሰዱ የመውደቅ መነሳት vይወት ለሚሩ ድኾች፣ በሥቃይ ላሉና ተስፋ ለቆረጡ ሊሆን ይገባል፡፡ --Gospel Workers, p. 141.ChSAmh 321.4

    እንደ ሕዝብ ርኅራኄ ማሳየት ባለመቻላችንና ከሰዎች ጋር አግባብ ባለመፍጠራችን አያሌ ነፍሳትን እያጣን ነው፡፡ ራሱን ከሌሎች አግልሎ አርነት ስለ መውጣት የሚያወራ አገልጋይ እግዚአብሔር ለሚሰጠው ኃላፊነት ብቁ መሆን አይችልም፡፡ እኛ የእግዚአብሔር ልጆች እንደመሆናችን ደስታችን በጋራ ማንነታችን ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ከእግዚአብሔርም ሆነ ከሰብዓዊው ፍጡር ኃላፊነት የተቀበልን እንደመሆናችን ሁላችንም በዚህ ህይወት የድርሻችንን መወጣት ይኖርብናል፡፡ የሰብዓዊ ተፈጥሮአችን አካል በሆኑ የማኅበረሰቡ መሰረታዊ ነገሮች ላይ በጥንቃቄ መሥራት መቻላችን ለወንድማችን እንድንራራ ያደርገናል፡፡ ሌሎችን ለመባረክ ጥረት ስናደርግ እኛው ራሳችን የደስታ ባለቤቶች እንሆናለን፡፡Testimonies, vol 4, pp. 71, 72.ChSAmh 321.5

    አዳኙ በፈሪሳዊው የሠግር ግብዣ ላይ በእንግድነት ተገኝቶ ነበር፡፡ ከሐብታሞችም ሆነ ከድኾች ይቀርብለት የነበረውን ግብዣ ይቀበል የነበረው ጌታ እንደ ልማዱ የተገኘበትን ትዕይንት ከእውነት አስተምህሮ ጋር ትስስር ለመፍጠር ይጠቀምበት ነበር፡፡--Christ’s Object Lessons, p. 219.ChSAmh 322.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents