Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምስክሮች

    እኛ የክርስቶስ ምስክሮች እንደመሆናችን ምድራዊ ፍላጎቶችና ዕቅዶች ጊዜአችንንና ትኩረታችንን ውጠው እንዲያስቀሩ መፍቀድ የለብንም፡፡-Testimonies, vol. 9, pp. 53, 54. ChSAmh 19.1

    እናንተ ምስክሮቼ. . . ናችሁ ይላል እግዚአብሔር፡፡ ገልጫለሁ፣ አድኛለሁ፣ ተናግሬአለሁ በመካከላችሁ እኔ እንጂ ባዕድ አምላክ አልነበረም፡፡ እኔ አምላh እንደሆንሁ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፡፡” “እኔ እግዚአብሔር በጽድቅ ጠርቼሃለሁ፤ እጅህንም እይዛለሁ፤ እጠብቅሃለሁ፤ ለሕዝቡ ቃል ኪዳን ለአሕዛብም ብርሃን አደርግሃለሁ፡፡ የዕውሮች ዐይን ትከፍታለv፣ ምርኮኞችን ከእሥር ቤት፣ በጨለማ የተቀጡትንም ከወህኒ ታወጣለህ፡፡” The Acts of the Apostles, p. 10. ChSAmh 19.2

    የዚህ ዓለም ሕዝቦች የሐሰት አማልክት እያመለኩ ይገኛሉ፡፡ እነዚህን ሕዝቦች ከሐሰት አምልኮ ለመመለስ የሚበጀው አካሄድ ጣኦቶቻቸውን የሚያወግዙ ቃላት እንዲሰሙ መፍቀድ ሳይሆን የተሻለውን ነገር እንዲመለከቱ ማድረግ ነው፡፡ የእግዚአብሔር መልካምነት እንዲታወቅ ማድረግ ይገባል፡፡ “እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ’ ይላል እግዚአብሔር”-- Christ’s Object Lessons, p. 299. ChSAmh 19.3

    ወደ እግዚአብሔር ከተማ የሚገቡ ሁሉ በማንኛውም ምድራዊ vይወታቸው ክርስቶስን ሊያስቀድሙ ይገባል፡፡ የእርሱ መልእክተኞችና ምስክሮች የሚያደርጋቸው ይኸው ነው፡፡ በማናቸውም የክፉ ልምዶችና ድርጊቶች ላይ ምስክር ለመሆን በመወሰንና ኃጢአተኞችን የዓለምን ኃጢአት ወደ ሚያስወግደው በግ በማመላከት በግልጽ ጸንተው መቆም ይኖርባቸዋል፡፡Testimonies, vol.9, p.23. ChSAmh 19.4

    ደቀ መዛሙርቱ እንደ ክርስቶስ ምስክርነታቸው ስለ እርሱ ያዩትንና የሰሙትን ለማወጅ ወደፊት መጓዝ ነበረባቸው፡፡ ይህ የተሰጣቸው ኃላፊነት ማንኛውም ሰብዓዊ ፍጡር ከተጠራበት ይልቅ በእጅጉ አስፈላጊ ነበር፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ሰዎችን ለማዳን ከእግዚአብሔር ጋር በአንድነት ወደ ሥራ መሰማራት ነበረባቸው፡፡--The Acts of the Apostles, p. 19.ChSAmh 20.1

    መለኮታዊው መምህር እውነትን ለማስተማርና ስለ ኃጢአት ለመውቀስ መንፈሱ ብቻውን በቂ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ውጪያዊ ነገሮች በአእምሮ ላይ የሚያሳድሩት ተጽእኖ ከጊዜያዊ የዘለለ ባለመሆኑ እውነት በሕሊና ላይ ባለው ብርቱ ተጽእኖ ሰዎች ጊዜአቸውን፣ ገንዘባቸውንና ዕውቀታቸውን ተጠቅመው በመላው ዓለም ለእርሱ _ ለመመስከር አጽንኦት ይሰጣሉ፡፡-Testimonies, vol. 7, p. 159. ChSAmh 20.2

    ስለ እርሱ ታማኝነት የምንሰጠው ምስክርነት ክርስቶስ ለዓለም የሚገለጽበት ሰማያዊ ዘዴ ነው፡፡ በጥንት ቅዱሳን ሰዎች አማካይነት እንድናውቀው ስለተደረገው ጸጋው እንደንመሰክር _ ይጠበቅብናል፡፡ ሆኖም የበለጠ ውጤታማ የሚሆነው በእኛ ላይ ስለደረሰው ሁኔታ መመስከር የቻልን እንደሆነ ነው፡፡ በሕይወታችን እየሠራ የሚገኘውን መለኮታዊ ኃይል ስንገልጽ ለእግዚአብሔር መሰከርን ማለት ነው፡፡ የእያንዳንዱ ግለሰብ ሕይወት ከሌሎች የተለየ እንደመሆኑ የሕይወት ገጠመኙም የዛኑ ያህል የተለየ ነው፡፡ እግዚአብሔር እያንዳንዳችን እንደ ግለሰብ ምስጋና እንድናቀርብለት ይሻል፡፡ ይህ ለጸጋው ክብር የሚቀርብ የምስጋና ምስክርነት የክርስቶስን ሕይወት በመሰለ የኑሮ ዘይቤ ሲደገፍ ለነፍሳት ማዳን አገልግሎት የሚውል ምንም ነገር ሊቋቋመው የማይችል >ይል ነው፡፡ --The Desire of Ages, p. 347. ChSAmh 20.3

    እግዚአብሔር በመላው ምድር ተበታትነው የሚገኙ ምስክሮች ሳይኖሩት የፈቃዱን ዕውቀትና አስገራሚውን አምላካዊ ጸጋ ለማያምነውዓለም ማሳየት አይችልም፡፡ በየሱስ ክርስቶስ አማካይነት የዚህ ታላቅ ደኅንነት ወራሽ የሆኑ ወገኖች-የእርሱ ወንጌላውያን፣ የሕዝቦች አምበል፣ በዓለም የተሰራጩ የብርሃን አካላት፣ በሰዎች የሚታወቁና የሚነበቡ ሕያው ደብዳቤዎች፣ እምነታቸውና ሥራዎቻቸው በቅርቡ የሚገለጠውን አዳኝ የሚመሰክሩና የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳልተቀበሉ የሚያሳዩ እንዲሆኑ ዕቅዱ ነው፡፡ ሕዝቦች ስለሚመጣው ፍርድ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ የማስጠንቀቂያ መልእክት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡-Testimonies, vol. 2, pp. 631, 632. ChSAmh 21.1

    ደቀ መዛሙርቱ ንጹህና ቅዱስ በሆነው ሐይወት ዙሪያ አምልኮ ያደርጉ በነበረበት ወቅት በፍቅር ለተሞላው የክርስቶስ ጸባይ በሕይወታቸው ብቻ ምስhር መሆን ቢችሉ--ማንኛውም ዓይነት ልፋት ወይም መሥዋዕትነት ሊከብዳቸው ወይም ዳገት ሊሆንባቸው እንደማይችል ተሰምቶአቸው ነበር፡፡ ደቀ መዛሙርቱ እነዚያን የአብሮነት ሦስት ዓመታት ዳግም ሊያገኙአቸው ቢችሉ እንዴት ከቀድሞው የተለዩ ሊሆኑላቸው እንደሚችሉ አስበው ነበር፡፡ መምህሩን ብቻ ዳግም ሊያዩት ቢችሉ ለእርሱ ያላቸው ፍቅር እጅግ ጥልቅ መሆኑን ሊሳዩት በታገሉ፣ ከአንደበታቸው በወጣ አጉል ቃል ወይም ባለማመን ባሳዩት ድርጊት ምን ያህል እንዳዘኑ በትvትና ሊገልጹለት በወደዱ ነበር! ሆኖም ይቅር በመባላቸው መጽናናት ቻሉ፡፡ ደቀ መዛሙርት ለቀድሞው አለማመን ንስሐ በመግባት አቅማቸው የፈቀደውን ያህል ለዓለም በጀግንነት ለመመስከር ቁርጥ ሃሳብ አደረጉ፡፡The Acts of the Apostles, p. 36. ChSAmh 21.2

    የሱስ “hዐሥሩ ከተሞች” የመጀመሪያ ወንጌላውያን አድርጎ የላካቸው እነዚህን ከርኩስ መናፍስት ነጻ የወጡትን ሁለት ሰዎች ነው፡፡ ለአጭር ጊዜ የየሱስን ትምህርት የመስማት ዕድል የነበራቸው እነዚህ ሰዎች ብቻ ነበሩ፡፡ ከእርሱ አንደበት የወጣ አንድም ስብከት ወደ ጆሮአቸው አልደረሰም ነበር፡፡ በየዕለቱ ከየሱስ ተለይተው የማያውቁት ደቀ መዛሙርት ሊያስረዱ የሚችሉትን ያህል እነዚህ ሰዎች ለሕዝቡ ማስረዳት አይችሉም ነበር፡፡ ነገር ግን የሱስ መሲህ ለመሆኑ ራሳቸው የዐይን ምስክሮች ነበሩ፡፡ ያወቁትን፣ ራሳቸው በዐይናቸው ያዩትን፣ የሰሙትንና የክርስቶስ ኃይል እንዴት እንደተሰማቸው መናገር ይቸሉ ነበር፡፡ በእግዚአብሔር ጸጋ ልቡ የተነካ ሁሉ ይህን ማድረግ ይችላል፡፡ ተወዳጁ ዮሐንስ የሚከተለውን ጽፎአል፡ “ከመጀመሪያው ስለነበረው ስለ ሕይወት ቃል እንጽፍላችኋለን፣ ይህ የህይወት ቃል የሰማነውና ባዐይኖቻችን ያየነው _ የተመለከትነውና በእጆቻችን የዳሰስነው _ ነው:: ይህ ሕይወት ተገልጦአል፡፡ _ እኛም አይተነዋል፣እንመሰክራለን፡፡. . . ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተም እንነግራችኋለን፡፡” እኛ የክርስቶስ መስካሪዎች የምናውቀውን፣ በዐይናችን ያየነውን ፣ በጆሮአችን የሰማነውንና በራሳችን ላይ የደረሰውን መናገር አለብን፡፡ የሱስን ደረጃ በደረጃ ስንከተለው ቆይተን ከሆነ እንዴት እንደመራን በትክክል የምናውቀውን መናገር እንችላለን፡፡ ተስፋውን እንደሞከርነውና እውነተኛም ሆኖ እናዳገኘነው ማውራት እንችላለን፡፡ ስለ ክርስቶስ ጸጋ ያወቅነውን መመስከር እንችላለን፡፡ ጌታ የሚጠራን ለዚህ ዓይነት ምስክርነት ሲሆን ዓለምም በመጥፋት ላይ ያለው ይህን ምስክርነት በማጣቱ ነው፡፡-- The Desire of Ages, p. 340.ChSAmh 21.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents