Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የክርስቲያን አገልግሎት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    እምነት

    የእግዚአብሔር ሠራተኞች አገልግሎታቸውን በትኩረት በሚከታተለውና ተገቢውን ዋጋ በሚሰጠው አምላክ ላይ እምነት ሊኖራቸው የግድ ነው፡፡ የመለኮት ወኪሎች ከእግዚአብሔር ጋር ሠራተኞች ከሆኑ ነፍሳት ጋር ለአገልግሎት ተመድበዋል፡፡ እግዚአብሔር በተናገረው መሰረት ለመሥራትም ሆነ ሠራተኞቹን በትኩረት ለመከታተል ጊዜ እንደሌለው አድርገን ስናስብ የፈጣሪያችንን ክብር እንነካለን፡፡-Southern Watch man, Aug. 2, 1904. ChSAmh 323.1

    ለእግዚአብሔር አገልግሎት የሚሰጥ ሠራተኛ የጠንካራ እምነት ባለቤት ሊሆን ይገባል፡፡ ምንም እንኳ በዐይኖቻችን የምንመለከተው ነገር ተስፋ አስቆራጭ ቢመስልም ነገር ግን እጅግ በጨለማ ከተዋጠው ሰዓት ባሻገር የሚፈነጥቅ የብርሃን ጸዳል አለ፡፡ ለእግዚአብሔር በእምነትና በፍቅር አገልግሎት የሚሰጡ ወገኖች ጉልበት ዕለት ዕለት ይታደሳል፡፡--Gospel Workers, p. 262.ChSAmh 323.2

    ከልብ በመነጨ እምነት ውስጥ ጊዜ ወይም አድካሚ ሥራ ሊያዳክመው የማይችል የደስተኝነት መንፈስን የሚያሰርጽ ጽኑና የማይወላውል ለመርኅ ታዛዥ የዓላማ ጽናት አለ፡፡Christ’s Object Lessons, p. 147.ChSAmh 323.3

    ብዙውን ጊዜ የክርስትና ህይወት በአደጋ የተከበበ እንደመሆኑ ቀናውን ተግባር መፈጸም ቀላል አይደለም፡፡ ከክስተቱ እንደምንረዳው ከእነዚህ ሕዝቦች በስተኋላ ውድመት፣ ግዞት ወይም ሞት ደረስኩባችሁ ቢልም፤ የእግዚአብሔር ድምፅ ግን በግልጽ እንደተመለከተው “ወደፊት” ተጓዙ የሚል ነበር፡፡ ምንም እንኳ ዐይኖቻችን በድቅድቁ ጨለማ ማየት ባይችሉና ቀዝቃዛው ወጀብ እግሮቻችንን ዘልቆ ቢሰማን፤ ትእዛዙን ልንከተል ይገባል፡፡ የመጠራጠር መንፈስ እስካለን ድረስ እድገታችንን የሚገቱ እንቅፋቶች ሊወገዱ አይችሉም፡፡ በውስጣችን የሚሰማን የጥርጣሬ ጥላ እስኪወገድና ልንወድቅ ወይም ልንሸነፍ የምንችልበት አደጋ እስኪወገድ እግዚአብሔርን መታዘዛችንን እናዘግይ የሚሉ፤ መቼውንም ታዛዥ አይሆኑም፡፡ “ከፊታችን ያለው መሰናክል _ እስኪወገድ ከቆየን መንገዳችን ጠርቶ ማየት እንችላለን” ሲል አለማመን በጆሮአቸው ያንሾካሹካል፡፡ እምነት ግን በሁሉም ተስፋ እንድናደርግና በሁሉም እምነት እንዲኖረን እያደፋፈረ በብርታት ወደፊት እንስግስ ይላል፡፡Patriarchs and Prophets, p. 290. ChSAmh 323.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents