Go to full page →

እውነትን የያዘው ብጣሽ ወረቀት የትም እንዳይጣል ChSAmh 211

ክርስቶስ ጥቂት ዳቦዎችና ዓሣዎች ተጠቅሞ በተአምራት ብዙ ሕዝብ በመገበበት ውቅት ከእርሱ አልፎ ወደ ተቀባዮች የደረሰው ምግብ መጠኑ ጨምሮ እንደነበር--በኅትመት ውጤቶቻችን ስርጭት ተመሳሳይ ክስተት ገቢራዊ ይሆናል፡፡ የእግዚአብሔር እውነትከሚያስተላልፈው እጅ ሲወጣ በብዙ እጥፍ ይበዛል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ አንድም ፍርፋሪ እንዳይወድቅ የሱስ የሰጣቸውን ትእዛዝ ተከትለው ከሕዝቡ የተረፈውን እንደሰበሰቡ ሁሉ እኛም ለዚህ ዘመን የተሰጠውን እውነት የያዘውን እያንዳንዱን ብጣሽ የኅትመት ውጤት የትም መጣል የለብንም፡፡ የሦስቱን መላእክት መልእክት የያዘ ብጣሽ ወረቀት እውነትን በተጠማው ልብ ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተጽእኖ ማንም ሊገምት አይችልም፡፡Southern Watchman, Jan. 5, 1904. ChSAmh 211.2