Go to full page →

የሰማያዊው የዐይን ጠብታ አስፈላጊነት ChSAmh 53

ምዕመናን የቀረቡላቸውን መልካም ዕድሎች ተመልክተው እግዚአብሔርን ማገልገል ይችሉ ዘንድ ቤተ ክርስቲያን ሰማያዊውን በእግዚአብሔር ሕዝቦች መሃል የሚስተዋሉ ሁናቴዎች የዐይን ጠብታ ተጠቅማ ዕይታዋን ልታጠራ ይገባል፡፡ የእግዚአብሔር ቤት በሰዎች የተሞላ ይሆን ዘንድ ወደ አውራው መንገድ ወጥተን ነፍሳትን እንድናድም ጌታ በተደጋጋሚ ጥሪ ሲያደርግ ኖሮአል፡፡ ሆኖም ምን ያህል ለነፍሳቸው እንደምንጨነቅ እንዲያስቡ ሊያደርጋቸው የሚችል በቂ ፍላጎት ያላሳየናቸው የገዛ ቤተሰቦቻችን በራሳችን ደጃፍ ጥላ ስር ይገኛሉ፡፡ ጌታ አሁን ለቤተ ክርስቲያን ጥሪ እያደረገ ያለው ይህን አጠገባችን ያለውን ሥራ በቁርጠኝነት እንድንሠራ ነው፡፡ “ባልንጀራዬ ማነው?” ብለን መጠየቅ ሳይሆን-የእኛን ርኅራኄና እርዳታ የሚሻ ሁሉ ባልንጀራችን መሆኑን ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ በጠላት የቆሰለውና ጉዳት የደረሰበት እያንዳንዱ ነፍስ፣ እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ንብረት ባልንጀራችን ነው፡፡ ባልንጀራዬ ማነው--በሚል በአይሁዳውያን የተቀመጠው ልዩነት በክርስቶስ ተወግዶአል፡፡ ከእንግዲህ ሰው ሠራሽ ድንበር፣ ክልል፣ መለያየት፣ መሳፍንት ወይም መኳንንት የለም፡፡-Testimonies, vol 6, p. 294. ChSAmh 53.1