Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
አእምሮ፣ባሕርይና ማንነት፣ክፍል 1 - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 16—የቅድመ ወሊድ ተጽእኖዎች

    የቅድመ ወሊድ ተጽእኖዎች አስፈላጊነት።--ብዙ ወላጆች የቅድመ ወሊድ ተጽዕኖዎችን እንደ ትንሽ ነገር አድርገው ተመልክተውታል፣ ነገር ግን ሰማይ እንደዚያ አይመለከተውም። መልእክቱ በእግዚአብሔር መልአክ መላኩና ሁለት ጊዜ እጅግ ኮስተር ባለ ሁኔታ መሰጠቱ የሚያሳየው የእኛን እጅግ በጥንቃቄ የተሞላ ሀሳብ የሚፈልግ መሆኑን ነው።--MH 372 (1905). {1MCP 131.1}1MCPAmh 107.1

    እርካታ ያለው መንፈስ በልጅ ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል።--ለእናትነት እየተዘጋጀች ያለች እያንዳንዷ ሴት፣ አከባቢዋ ምንም ቢሆን፣ በዚህ አቅጣጫ ለምታደርገው ጥረት ሁሉ በልጇ አካላዊም ሆነ ግብረገባዊ ባሕርይ ውስጥ አስር እጥፍ እንደሚከፈላት በማወቅ ያለማቋረጥ ደስተኛ የሆነ፣ ፈገግታ የተሞላ፣ እርካታ ያለው ባሕርይ ማደፋፈር አለባት። ይህ ብቻም አይደለም። በልማድ ራሷን አስደሳች ከሆነ አስተሳሰብ ጋር ማለማመድ ትችላለች፣ በዚህ መልኩ ደስተኛ የሆነ አእምሮን በማበረታታት፣ የራሷን ደስተኛ የሆነ መንፈስ አስደሳች ነጸብራቅ በቤተሰቧ ላይና ግንኙነት ከምትፈጥርባቸው ሰዎች ላይ ማሳረፍ ትችላለች። {1MCP 131.2}1MCPAmh 107.2

    እጅግ ከፍተኛ በሆነ ደረጃ አካላዊ ጤንነቷ ይሻሻላል። ለሕይወት ምንጮች ኃይል ይሰጣቸዋል፣ ለተስፋ መቁረጥና ለጨለምተኝነት ብትሸነፍ ኖሮ ሊሆን እንደሚችለው ደም እየተንቀረፈፈ አይንቀሳቀስም። የአእምሮና የግብረ ገብ ጤና ከደስተኛ መንፈሷ የተነሳ ብርታት ያገኛል። --RH, July 25, 1899. (CH 79.) {1MCP 131.3}1MCPAmh 107.3

    እናት የሚኖሯት ስሜቶች በማህጸኗ ያለውን ልጅ ጠባይ ይቀርጻሉ።--የእናት ሀሳቦችና ስሜቶች ለልጇ በምትሰጠው ውርስ ላይ ኃይለኛ የሆነ ተጽእኖ አላቸው። አእምሮዋ በራሷ ስሜቶች ላይ እንዲያርፍ ከፈቀደች፣ ራስ ወዳድነትን ከተለማመደች፣ ነጭናጫ/ በትንሽ በትልቁ የምትቆጣ እና የፈለገችውን አስገድዳ የምታገኝ ከሆነች፣ የልጇ ጠባይ ያንን እውነታ ይመሰክራል። ከዚህ የተነሣ ብዙዎች ሊያሸንፏቸው የማይችሉአቸውን የክፉ ዝንባሌዎች እንደ ብኩርና መብት ተቀብለዋል። --ST, Sept 13, 1910. (Te 171.) {1MCP 132.1}1MCPAmh 107.4

    እናት ሳትናወጥ ለትክክለኛ መርሆዎች ከተገዛች፣ መሻቷን የምትገዛና ራሷን የካደች ከሆነች፣ ደግ፣ ጨዋ እና ከራስ ወዳድነት የጸዳች ከሆነች፣ ለልጇ እነዚህን የከበሩ ባሕርያት ትሰጣለች። --MH 373 (1905). {1MCP 132.2}1MCPAmh 107.5

    ሰላም በቅድመ ወሊድ ላይ ያለው ተጽእኖ።--እናት ለመሆን እየጠበቀች ያለች ሴት ነፍሷን በእግዚአብሔር ፍቅር መጠበቅ አለባት። አእምሮዋ ሰላም መሆን አለበት፤ የክርስቶስን ቃላት በመለማመድ በኢየሱስ ፍቅር ማረፍ አለባት። እናት ከእግዚአብሔር ጋር አብራ ሰራተኛ መሆኗን ማስታወስ አለባት። --ST, Apr 9, 1896. (AH 259.) {1MCP 132.3}1MCPAmh 107.6

    አባትነትን እየጠበቀ ያለ ሰው ከአካል ሕጎች ጋር መተዋወቅ አለበት።--የእናት ብርታት በጥንቃቄ እንክብካቤ ሊደረግለት ይገባል። ክቡር ብርታቷን በሚያደክም ሥራ ብርታቷን እንዳትጨርስ ጭንቀቷና ሸክሞቿ ሊቃለሉላት ይገባል። ብዙ ጊዜ ባልና አባት የሆነው ሰው ስለ ቤተሰቡ ደህንነት እንዲያስተውል ከሚፈለግበት የአካል ሕግ ጋር ትውውቅ የለውም። ለኑሮ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ለማሟላት በሚደረግ ትግል ስለተጠመደ፣ ወይም ሀብት ወደ ማግኘት ስላደላ እና ጭንቀትና ግራ መጋባት ስለተጫኑት እናትና ሚስት በሆነችው ላይ እጅግ ወሳኝ በሆነ ወቅት ላይ ሥራ በማብዛት፣ ጫና የሚፈጥሩባትን ሸክሞች እንድትሸከም በመፍቀድ ደካማና በሽተኛ እንድትሆን ያደርጋታል። --MH 373 (1905). {1MCP 132.4}1MCPAmh 108.1

    የአእምሮ እድገትን የተቀሙ ልጆች።--እናት ማግኘት የሚገባትን ጥንቃቄና ምቾት ከተከለከለች፣ ጉልበቷ ከመጠን በላይ በመስራት ወይም በስጋትና በጭንቀት እንዲንጠፈጠፍ ከተደረገች፣ ልጆቿ ከእሷ መውረስ የሚገባቸውን ወሳኝ ኃይል፣ አእምሮ ከሁኔታዎች ጋር ራሱን የማስተካከል ችሎታንና ደስታን ይቀማሉ። የእናትን ሕይወት ብሩህና ደስተኛ በማድረግ፣ ከእጦት፣ ከአድካሚ ሥራና ጭንቀት ከሚያስከትል ሀላፊነት በማሳረፍ፣ ልጆቿ በራሳቸው ብርታት በሕይወት መንገድ የራሳቸውን ትግል መታገል እንዲችሉ፣ ጥሩ የሰውነት አቋም እንዲወርሱ መደረግ አለባቸው።-- MH 375 (1905). {1MCP 132.5}1MCPAmh 108.2

    እናት የሚያስፈልጓት ነገሮች ችላ መባል የለባቸውም።--የእናት አካላዊ ፍላጎቶች በምንም መንገድ ችላ መባል የለባቸውም። በእሷ ላይ ሁለት ሕይወቶች ስለሚደገፉ ምኞቶቿ ትኩረት ሊሰጣቸውና የሚያስፈልጓት ነገሮች በልግስና ሊሰጧት ይገባል። ነገር ግን በአመጋገብና በሌሎች መስመሮችም ቢሆን፣ በዚህን ጊዜ፣ ከሁሉ ነገር ይበልጥ የአካልን ወይም የአእምሮ ብርታትን የሚቀንሰውን ማንኛውንም ነገር መተው አለባት። በእግዚአብሔር በራሱ ትዕዛዝ ራስን መግዛትን እንድትለማመድ እጅግ ጥብቅ የሆነ ግዴታ አለባት።--MH 373 (1905). {1MCP 133.1}1MCPAmh 108.3

    የሚስት ሀላፊነት።--በመርህ የሚኖሩና በደንብ የተማሩ ሴቶች ከሁሉም ጊዜ ይልቅ በዚህ ሰዓት (በእርግዝና ጊዜ) ቀለል ካለ የአመጋገብ ደንብ አይርቁም። በእነርሱ ላይ ሌላ ሕይወት እንደሚደገፍ ስለሚያውቁ በልምዶቻቸው ሁሉ፣ በተለይም በአመጋገብ ጥንቁቅ ይሆናሉ።--2T 382 (1870). {1MCP 133.2}1MCPAmh 108.4

    ምንም ክፋት የሌለባቸው የዋህ ልጆች ይሰቃያሉ።--ወላጆች ከአግባብ ውጭ የምግብ ፍላጎታቸውን ከማሟላታቸው የተነሣ ታማሚ ልጆች ይወለዳሉ። አእምሮ የሚፈልገው የምግብ ዓይነት የአካል ሥርዓት የማይፈልገው ነው። አእምሮ ስላሰበው ብቻ ወደ ሆድ መግባት አለበት የሚለው አስተሳሰብ ክርስቲያን የሆኑ ሴቶች መቀበል የሌለባቸው ትልቅ ስህተት ነው። ሀሳብ የአካል ክፍሎችን ፍላጎቶች እንዲቆጣጠር መፈቀድ የለበትም። የምግብ ጣዕም እንዲገዛቸው የሚፈቅዱ ሰዎች የአካላቸውን ሕጎች የመተላለፍን ቅጣት ይቀበላሉ። ጉዳዩ እዚህ ብቻ አያበቃም፤ ምንም የማያውቁ የዋህ ልጆችም ይሰቃያሉ።--2T 383 (1870). {1MCP 133.3}1MCPAmh 109.1

    ለልጆቿ ደህንነት ሲባል፣ እናት እያንዳንዱን ምኞትና የልብ ምት እንድታሟላ ጥበብ የጎደላቸው አማካሪዎች ይገፋፏታል። እንደዚህ ያለ ምክር ስህተትና አታላይ ነው። በራሱ በእግዚአብሔር ትዕዛዝ እናት ራሷን መቆጣጠርን እንድትለማመድ እጅግ ጥብቅ ግዴታ አለባት። መስማት ያለብን የማንን ድምጽ ነው--የመለኮታዊ ጥበብ ድምጽ ወይስ የሰብአዊ ጥንቆላ ድምጽ?-- ST, Feb. 26, 1902. {1MCP 133.4}1MCPAmh 109.2

    ነፍሰጡር እናት ራስን የመካድ ልምዶችን መመስረት አለባት።--ለልጆቿ መምህርት ለመሆን ገጣሚ የሆነች እናት ልጆች ከመወለዳቸው በፊት ራስን የመካድና የመቆጣጠር ልማዶች መመስረት አለባት፤ ይህ መሆን ያለበት ለልጆቿ የራሷን ችሎታዎች፣ ጠንካራና ደካማ ባሕርያትን ስለምታስተላልፍ ነው። ይህን ጉዳይ ብዙ ወላጆች ከሚረዱት በተሻለ ሁኔታ የነፍሳት ጠላት ይረዳል። እናት፣ ከልተቋቋመችው በቀር፣ ጠላት በእርሷ አማካይነት በልጇ ላይ ችግር ለማምጣት ፈተናን ያመጣባታል። የእናት ብቸኛ ተስፋ ያለው በእግዚአብሔር ነው። ጸጋና ብርታትን ለማግኘት ወደ እርሱ ልትሸሽ ትችላለች። በከንቱ እርዳታን አትፈልግም። ልጆቿ በዚህ ሕይወት ስኬትን እንዲያገኙና የዘላለምን ሕይወት እንዲያገኙ የሚረዱአቸውን ችሎታዎች ማስተላለፍ እንድትችል ያስችላታል። --ST, Feb. 26, 1902. (CD 219.) {1MCP 134.1}1MCPAmh 109.3

    የትክክለኛ ባሕርይ መሰረት።--በወደፊቱ ሰው ውስጥ የትክክለኛ ባሕርይ መሰረት ሊጸና የሚችለው እናት ልጇን ከመውለዷ በፊት በሚኖሩአት ጥብቅ መሻትን የመግዛት ልማዶች ነው።…ይህ ትምህርት በቸልታ መታየት የለበትም።--GH, Feb, 1880. (AH 258.) {1MCP 134.2}1MCPAmh 109.4

    የሰው ዘር በተጠራቀመ ዋይታ ሥር ሆኖ እየቃተተ ነው።--ከቀድሞዎቹ ትውልዶች ኃጢአቶች የተነሣ የሰው ዘር ከተጠራቀመ ዋይታ ሥር ሆኖ በመቃተት ላይ ይገኛል። እንዲህም ሆኖ የዚህ ትውልድ ወንዶችና ሴቶች ያለ አንዳች ሀሳብ ወይም ጭንቀት ከመጠን በላይ በመኖር እና በስካር መሻታቸውን ካለመግዛታቸው የተነሣ ለወደፊቱ ትውልድ በሽታን፣ ደካማ አእምሮን፣ እና የሞራል ብክለትን እንደ ውርስ ትተው ያልፋሉ። --4T 31 (1876). {1MCP 134.3}1MCPAmh 110.1

    እርካታ የሌላቸው መጓጓቶችና ያልተቀደሱ ፍላጎቶች ወደ ልጅ ይተላለፋሉ።--ሁለቱም ወላጆች የራሳቸውን የአእምሮና የአካል ባሕርያት፣ ዝንባሌንና የምግብ ፍላጎትን ለልጆቻቸው ያስተላልፋሉ። አስካሪ መጠጥ ተጠቃሚዎችና ትንባሆ አጫሾች የራሳቸውን በቃኝ የማይል መጓጓት፣ የተቆጣ ደምና የተረበሹ ነርቮችን ለልጆቻቸው ያስተላልፋሉ። ፍትወተኞች ብዙ ጊዜ ያልተቀደሱ ፍላጎቶቻቸውን እና የሚያስጠሉ በሽታዎችን ለልጆቻቸው እንደ ቅርስ ያወርሳሉ። ልጆች ፈተናን የመቋቋም ኃይላቸው ከወላጆች ይልቅ አነስተኛ ስለሆነ እያንዳንዱ ትውልድ ካለፈው ትውልድ እየወረደ የመሄድ ዝንባሌ አለ።--PP 561 (1890). {1MCP 134.4}1MCPAmh 110.2

    እንደ ደንብ ስንወስድ፣ እያንዳንዱ መሻቱን ሳይገዛ ልጆችን የሚያሳድግ ሰው ክፉ ዝንባሌዎቹን ወደ ልጆቹ ያስተላልፋል።--RH, Nov 21, 1882. (Te 170.) {1MCP 135.1}1MCPAmh 110.3

    ሳምሶን ከመወለዱ በፊት የነበረው ሕይወት በእግዚአብሔር ቁጥጥር ተደርጎበት ነበር።--ለማኖኣ ሚስት የተነገሩ ቃላትን የዛሬ እናቶች ቢያጠኑ የሚጠቅም እውነት ይዘዋል። ጌታ ለዚህች እናት በመናገር በዚያን ጊዜ በስጋት ውስጥ ለነበሩና ላዘኑ እናቶች እና ቀጥሎ ባለው ትውልድ ለሚኖሩ እናቶች ሁሉ ተናግሯል። አዎን፣ እያንዳንዷ እናት ተግባሯን ልትረዳ ትችላለች። የልጆቿ ባሕርይ በውጫዊ ጥቅሞችና ጉዳቶች ላይ ከሚደገፍ ይልቅ ከመወለዳቸው በፊት እሷ በነበሩአት ልማዶችና ከተወለዱ በኋላም በምታደርጋቸው የግል ጥረቶች ላይ እንደሚደገፍ ታውቅ ይሆናል።--ST, Feb 26, 1902. (CD 218.) {1MCP 135.2}1MCPAmh 110.4

    እግዚአብሔር ቃል ለተገባው የማኖኣ ልጅ አስፈላጊ የሆነ ሥራ ነበረው፣ የእናቲቱና የልጇ ልማዶች በጥንቃቄ ቁጥጥር ሊደረግባቸው ያስፈለገው ልጁ ለዚህ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ ብቃቶችን እንዲያገኝ ነበር።…ልጁ ከእናት ልማዶች የተነሣ መጥፎ ወይም መልካም ተጽእኖ ሊያድርበት ይችላል። እናት የልጇን ደህንነት የምትፈልግ ከሆነች ለመርህ መገዛትና መሻትን መግዛትንና ራስን መካድን መለማመድ አለባት።--CTBH 38, 1890. (Te 90.) {1MCP 135.3}1MCPAmh 110.5

    እናቶችም አባቶችም ይሳተፋሉ።--በዚህ ሀላፊነት እናቶችም ሆኑ አባቶች ድርሻ ስላላቸው ተጽእኖአቸው እግዚአብሔር የሚያረጋግጠው እንዲሆን በቅንነት መለኮታዊ ጸጋን መሻት አለባቸው። የእያንዳንዱ አባትና እናት ጥያቄ መሆን ያለበት ‹‹ለሚወለደው ልጅ ምን ማድረግ አለብን?›› የሚል መሆን አለበት። ብዙዎች የቅድመ ወሊድ ተጽእኖ የሚያስከትለውን ችግር አቅልለው ተመልክተውታል፤ ነገር ግን ለእነዚያ ዕብራውያን ወላጆች ከሰማይ የተላከው መመሪያ እጅግ ግልጽና ኮስተር ባለ ሁኔታ ሁለት ጊዜ መደገሙ ፈጣሪ ጉዳዩን እንዴት እንደሚመለከተው ያሳያል። --ST, Feb 26, 1902. {1MCP 135.4}1MCPAmh 111.1

    ለልጆች የተሰጠ የወላጆች የራሳቸው አሻራ።--ወላጆች…የራሳቸውን ፍላጎት በማሟላት የእንስሳ ስሜቶች እንዲጠናከሩ አድርገዋል። እነዚህ ነገሮች ሲጠናከሩ የግብረገብና የአእምሮ ችሎታዎች ይደክማሉ። መንፈሳዊው በስጋዊው ይሸነፋል። ልጆች፣ የእንስሳ ስሜት በከፍተኛ ሁኔታ አድጎ፣ የወላጆቻቸው የባሕርይ አሻራ ተሰጥቶአቸው ይወለዳሉ።…የአእምሮ ኃይል ይዳከማል፣ የማስታወስ ችሎታ ይላሽቃል።…ወላጆች የራሳቸውን የፍትወት ዝንባሌ አሻራ ለልጆቻቸው ስለሰጡ የወላጆች ኃጢአት በልጆች ይጎበኛል። --2T 391 (1870). {1MCP 136.1}1MCPAmh 111.2

    ሰይጣን አእምሮዎችን ሊያረክስ ይሻል።--ሰይጣን የራሱን የሚያስጠላ ምስል በልጆቻቸው ላይ ለማተም ስለሚፈልግ በጋብቻ የሚጣመሩ ሰዎችን አእምሮዎች ሊያረክስ እንደሚፈልግ እንዳይ ተደርጌያለሁ።.... {1MCP 136.2}1MCPAmh 111.3

    የወላጆችን አእምሮ እንዲህ ባለ ሁኔታ መቆጣጠር ስለሚችል በእነርሱ አማካይነት የራሱን የባሕርይ አሻራ ለልጆቻቸው ይሰጥና ወላጆቹን ማድረግ ከቻለው የበለጠ የእነርሱን ዝሪያ መቅረጽ ይችላል። ስለዚህ ብዙ ልጆች የሚወለዱት የሞራል ኃይሎች እየደከሙ፣ ነገር ግን የእንስሳ ፍላጎቶች በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ ነው።--2T 480 (1870). {1MCP 136.3}1MCPAmh 111.4

    የማሰብ ችሎታ የልጆችን ቁጥር መወሰን አለበት።--የልጆቻቸውን ቁጥር እየጨመሩ የሚሄዱ ሰዎች፣ አእምሮአቸውን አማክረው ቢሆን ኖሮ፣ እያወረሱ ያሉት የአካልና የአእምሮ ድክመት መሆኑን እና ከእግዚአብሔር ትዕዛዛት መካከል የመጨረሻዎቹን ስድስቱን እየተላለፉ መሆናቸውን ባወቁ ነበር።…ባልንጀራቸውን በመጉዳት የትውልድን ማሽቆልቆልና የሕብረተሰብን ዝቅጠት በመጨመር የራሳቸውን ድርሻ እየተወጡ ናቸው። እግዚአብሔር ለጎረቤት መብቶች ግድ የሚለው ከሆነ ቀረብ ላሉትና እጅግ ቅዱስ ለሆኑት ግንኙነቶች ግድ አይለውምን? እርሱ ሳያውቅ ድንቢጥ እንኳን በምድር ላይ የማትወድቅ ከሆነ፣ ይብዛም ይነስም፣ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ በአካልና በአእምሮ በሽተኞች ሆነው እንዲሰቃዩ በዚህ ዓለም ላይ የሚወለዱ ልጆች ጉዳይ ግድ አይለውምን? የማሰብ ኃይል የተሰጣቸው ወላጆች ይህን ከፍ ያለ የማሰብ ችሎታ ወደ ጎን በመተው የስሜት ባሪያዎች በመሆናቸውና ከዚህ የተነሣ ትውልዶች የእነርሱን የአካል፣ የአእምሮ፣ እና የግብረገብ ጉድለቶችን እንዲሸከሙ በማድረጋቸው እግዚአብሔር ተጠያቂ አያደርጋቸውምን? --HL (Part 2) 30, 1865. (2SM 424.) {1MCP 136.4}1MCPAmh 111.5

    እጅግ ያነሰ ጉልበት ማስተላለፍ።--ታማሚና በሽተኛ የሆኑ ወንዶችና ሴቶች የጋብቻ ግንኙነት ሲፈጥሩ በራስ ወዳድነት ስለ ራሳቸው ደስታ ብቻ ያስባሉ። ከዝርያዎቻቸው ከልጅ ልጆቻቸው ምን እንደሚጠብቁ ማሰብን በተመለከተ ጉዳዩን ከከበሩ፣ ከፍ ካሉ መርሆዎች አንጻር በደንብ ሳያጤኑ፣ ሕብረተሰቡን ከፍ የሚያደርግ ሳይሆን የበለጠ ወደ ታች እንዲዘቅጥ የሚያደርግ የወረደ የአካልና የአእምሮ ጉልበትን አውርሰዋል።--HL (Part 2) 28, 1865. (2SM 423.) {1MCP 137.1}1MCPAmh 112.1

    ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ በሽታ።--ብዙ ጊዜ ታማሚ የሆኑ ወንዶች ጤናማ የሆኑ ሴቶችን በፍቅር ያሸንፉና እርስ በርሳቸው ስለሚዋደዱ ብቻ ለመጋባት ፍጹም ነጻነት እንዳላቸው ይሰማቸዋል።…እነዚያ ወደ ጋብቻ ግንኙነት የሚገቡ ብቻ ችግሩ የሚመለከታቸው ቢሆን ኖሮ ኃጢአታቸው ይህን ያህል ትልቅ ባልሆነም ነበር። ልጆቻቸው ከእነርሱ በተላለፈ በሽታ ለመሰቃየት ይገደዳሉ። ከዚህ የተነሣ በሽታ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲቀጥል ይደረጋል። …በሕብረተሰቡ ላይ ደካማ ዘርን በመዝራት፣ ተላላፊ በሽታን በማምጣትና ሰብአዊ ስቃይ እንዲበዛ በማድረግ፣ ዘርን በማበላሸት የራሳቸውን ድርሻ ተጫውተዋል። --HL (Part 2) 28, 1865. (2SM 423.) {1MCP 137.2}1MCPAmh 112.2

    የእድሜ ልዩነት ጉዳይ።--በዚህ ትውልድ ሌላኛው የአካል ብርታትና የግብረገብ ብቃት እጦት መንስኤ ሰፊ የዕድሜ ልዩነት ያላቸው ሰዎች በጋብቻ መጣመር ነው።…ከዚህ ዓይነት ጥምረት የሚገኙ ልጆች በአብዛኛው ሚዛናዊ የሆነ አእምሮ የላቸውም። በአካል ብርታትም ጉድለት አለባቸው። እንደ እነዚህ ባሉ ቤተሰቦች ውስጥ ብዙ ጊዜ የተለያዩ፣ ወጣ ያሉ፣ እና በአብዛኛው አሳዛኝ ባሕርያት ይታያሉ። አብዛኛውን ጊዜ ያለ ዕድሜያቸው ይሞታሉ፣ ወደ ብስለት ዕድሜ ሲደርሱም፣ በብዙ አጋጣሚዎች፣ በአካልና በአእምሮ ጉድለት ያለባቸውና የግብረገብ ብቃት የሌላቸው ይሆናሉ። {1MCP 138.1}1MCPAmh 112.3

    ስለዚህ ለህብረተሰብ ሸክም የሆኑ ፍጡራን በዓለም ላይ እየተዘሩ ነው። በልጆቻቸው ውስጥ ለጎለበተውና ከትውልድ ወደ ትውልድ ለሚተላለፈው ባሕርይ ወላጆቻቸው በከፍተኛ ደረጃ ተጠያቂ ናቸው።--HL (Part 2) 29, 30, 1865. (2SM 423, 424.) {1MCP 138.2}1MCPAmh 113.1

    በቅድመ ወሊድ ሊደረግ የሚገባውን ጥንቃቄ ችላ ላልንበት እግዚአብሔር ተጠያቂ ያደርገናል።--ሴቶች ከስሜት ይልቅ የአእምሮ ትዕዛዝን ሁል ጊዜ አልተከተሉም። በልጆቻቸው ውስጥ ዝቅ ያለ ግብረገብን እንዳይፈጥሩና ጤንነትንና ሕይወትንም ጭምር መስዋዕት በማድረግ የወረደ የምግብ ፍላጎትን ማርካትን ሊመሰርቱ የሚችሉ የሕይወት ግንኙነቶችን እንዳይፈጥሩ በላያቸው ያረፉት ከፍተኛ ሀላፊነቶች አልተሰሙአቸውም። ለመጪው ትውልድ ላስተላለፉት የአካል ጤንነትና የግብረገብ ባሕርያት እግዚአብሔር በከፍተኛ ደረጃ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል። .... {1MCP 138.3}1MCPAmh 113.2

    ከዚህ ክፍል የሚመደቡ እጅግ ብዙ ሰዎች ተጋብተው የራሳቸውን የአካል ድክመትና የተበላሸ ግብረገብ አሻራዎች ለልጆቻቸው አውርሰዋል። የእንስሳ ፍላጎቶችን ማርካትና አጠቃላይ ፍትወተኛነት ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲወርድ ሲዋረድ በመምጣት ሰብአዊ ስቃይ በሚያስፈራ ደረጃ እንዲጨምርና የትውልዱ ዋጋ እንዲወርድ ማድረግ የእነርሱ ዝርያ መለያ ባሕርያት ሆነዋል።--HL (Part 2) 27, 28, 1865. (2SM 422, 423.) {1MCP 138.4}1MCPAmh 113.3

    ወላጆች ለልጅ የሕይወትን ትጥቅ ይሰጣሉ። ወላጆች የሆኑትን፣ በከፍተኛ ደረጃ፣ ልጆችም ይሆናሉ። የወላጆች አካላዊ ሁኔታ፣ ባሕርያቸውና የምግብ ፍላጎታቸው፣ የአእምሮና የግብረ ገብ ዝንባሌዎቻቸው፣ ይብዛም ይነስም በልጆቻቸው ውስጥ ይባዛሉ።--MH 371 (1905). {1MCP 138.5}1MCPAmh 113.4

    ህብረተሰብንና የወደፊት ሁኔታን መቅረጽ።--ዓላማዎች የከበሩ ከሆኑ፣ የአእምሮና የመንፈሳዊ ስጦታዎች ከፍ ያሉ ከሆኑ፣ እና የወላጆች አካላዊ ኃይሎች በደንብ የጎለበቱ ከሆኑ፣ ለልጆቻቸው የሚሰጡአቸው የሕይወት ትጥቆች የተሻሉ ይሆናሉ። በውስጣቸው ያለውን ከሁሉ የተሻለውን ነገር ሲያሳድጉ፣ ህብረተሰቡን ለመቅረጽና የወደ ፊት ትውልዶችን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማንሳት ተጽእኖ እያሳደሩ ናቸው።.... {1MCP 139.1}1MCPAmh 113.5

    የምግብ ፍላጎትንና ጥልቅ ስሜትን በማርካት ጉልበቶቻቸው ባክነዋል፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ለዚህ ዓለምም ሆነ ለሚመጣው ዓለም ገጣሚዎች ላይሆኑ ጠፍተዋል። ልጆች እነዚህን ፈተናዎች መጋፈጥ እንዳለባቸው ወላጆች ማስታወስ አለባቸው። ልጁ ገና ከመወለዱ በፊት ከክፉ ጋር የሚደረገውን ጦርነት በተሳካ ሁኔታ መዋጋት የሚያስችል ዝግጅት መጀመር አለበት። {1MCP 139.2}1MCPAmh 113.6

    በእናት ላይ በተለየ ሁኔታ ሀላፊነት ያርፍባታል። በህይወት ደሟ ልጇን የምትመግብና አካላዊ መዋቅሩ የተገነባባት እናት፣ አእምሮንና ባሕርይን ወደ መቅረጽ የሚያዘነብለውን አእምሮአዊና መንፈሳዊ ተጽእኖዎችን ለልጇ ታጋራለች።--MH 371, 372 (1905). {1MCP 139.3}1MCPAmh 114.1

    ወላጆች ለልጆቻቸው የራሳቸውን የባሕርይ አሻራ ሰጥተዋል።-- ወላጆች ለልጆቻቸው የራሳቸውን የባሕርይ አሻራ ሰጥተዋል፤ በአንድ ልጅ ውስጥ አንዳንድ ባሕርያት ባልተገባ ሁኔታ አድገው ከሆነ እና ሌላኛው ልጅ ደግሞ የማይወደድ የተለየ የባሕርይ ክፍል ቢያሳይ፣ እንደ ወላጆች ትዕግስተኛ፣ ቻይ እና ቸር መሆን ያለበት ማን ነው? በልጆቻቸው ውስጥ በክርስቶስ ኢየሱስ የታዩትን ክቡር ጸጋዎች ለማሳደግ እንደ እነርሱ በቅንነት መጣር ያለበት ማን ነው? {1MCP 139.4}1MCPAmh 114.2

    እናቶች የተሰጡአቸውን ዕድሎችና አጋጣሚዎች ግማሹን እንኳን አያደንቁም። ከፍ ባለ ስሜት ሲታይ ልጆቻቸው የተስተካከለ ባሕርይን እንዲገነቡ በመርዳት ሂደት ሚስዮናውያን፣ ከእግዚአብሔር ጋር አብረው ሰራተኞች መሆን እንደሚችሉ ያስተዋሉ አይመስሉም። ይህ ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው ከባድ የስራ ሸክም ነው። እናት ልጆቿን ወደ ክርስትና በመለወጥ ሂደት የእግዚአብሔር ወኪል ነች። --RH, Sept 15, 1891. {1MCP 139.5}1MCPAmh 114.3

    ለቅድመ ወሊድ ተጽእኖ የወላጆች ኃለፊነት።- ልጆችን በማሰልጠን ረገድ መደረስ ያለበት የመጀመሪያው ትልቁ ዓላማ የአካል አቋም ጤናማነት ነው፤ ይህ በከፍተኛ ደረጃ ለአእምሮና ለግብረገብ ስልጠና መንገድ ያዘጋጃል። የአካልና የግብረገብ ጤንነት በቅርበት የተገናኙ ናቸው። ወላጆች ልጆቻቸው ከመወለዳቸው በፊት የሚከተሉት መንገድ ከተወለዱ በኋላ በባሕርይ እድገታቸው ላይ ብዙ ተጽእኖ እንዳለው ከተገነዘብን በወላጆች ላይ ያረፈው እንዴት ያለ ከባድ ሀላፊነት ነው። --HL (Part 2) 32, 1865. (2SM 426.) {1MCP 140.1}1MCPAmh 114.4

    ስለዚህ ነገር ምን ማድረግ እንደሚቻል።-- ልጆች አጥብቀው መሻታቸውን እንዲገዙ እና ንጹህና ቅዱስ ልማዶች እንዲኖሩአቸው የማስተማርንና የማሰልጠንን ሥራ የበለጠ ከባድ የሚያደርጉ ዝንባሌዎችን ወላጆች ለልጆቻቸው አስተላልፈው ሊሆን ይችላል። ጤናማ ላልሆኑ ምግቦች፣ ለአነቃቂዎችና ለአደንዛዥ እፆች የተፈጠረ ፍላጎት ከወላጆች ወደ ልጆች እንደ ቅርስ ተላልፎ ከሆነ፣ እነዚህ ወላጆች ለልጆቻቸው የሰጡአቸውን ክፉ ዝንባሌዎች የመመከት እጅግ አስፈሪ የሆነ ሀላፊነት በላያቸው ያርፋል። ወላጆች ለእነዚህ ላልታደሉ ልጆች፣ በእምነትና በተስፋ፣ እንዴት ባለ ቅንነትና ትጋት ተግባራቸውን ለመፈጸም መስራት ይጠበቅባቸው ይሆን! --3T 567, 568 (1875). {1MCP 140.2}1MCPAmh 114.5

    ወላጆች መልስ የሚሰጡበት ቀን።--በመጨረሻው መልስ በሚሰጥበት ቀን ወላጆችና ልጆች ሲገናኙ፣ እንዴት ያለ እይታ ይሆን! ለምግብ ፍላጎትና ለሚያዋርድ መጥፎ ነገር ባሪያ የሆኑ፣ በሕይወታቸው የግብረገብ ብልሽት የገጠማቸው በሺሆች የሚቆጠሩ ልጆች፣ አሁን የሆኑትን እንዲሆኑ ካደረጉአቸው ወላጆች ጋር ፊት ለፊት ይቆማሉ። ይህን አስፈሪ የሆነ ኃላፊነት ከወላጆች በስተቀር ማን ይሸከማል? እነዚህን ወጣቶች እንዲበላሹ ያደረገው እግዚአብሔር ነው ወይ? አይደለም! አይደለም! ታዲያ ይህንን አስፈሪ ሥራ የሰራው ማን ነው? በተዛባ የምግብ ፍላጎትና ምኞት አማካይነት የወላጆች ኃጢአት ወደ ልጆች አልተላለፈምን? እግዚአብሔር በሰጣቸው ምሳሌ ማሰልጠንን ችላ ባሉት ሰዎች ሥራው አልተፈጸመምን? እነዚህ ወላጆች ሁሉ፣ ልክ እንዳሉ ሆነው፣ በእግዚአብሔር ፊት ለግምገማ ይቀርባሉ። --CTBH 76, 77, 1890. (FE 140, 141.) {1MCP 140.3}1MCPAmh 115.1

    ከሰብአዊ ጥበብ በላይ የሆነ ነገር ያስፈልጋል።--ልጆቻቸው ፈተናዎችን እንደሚጋፈጡ ወላጆች ማስታወስ አለባቸው። ከልጁ መወለድ በፊት እንኳን፣ ከክፉ ጋር የሚደረገውን ጦርነት በተሳካ ሁኔታ ማሸነፍ እንዲችል የሚያደርግ ዝግጅት መጀመር አለበት። --MH 371 (1905). {1MCP 141.1}1MCPAmh 115.2

    በሕይወታቸው መለኮታዊውን ነገር የሚያንጸባርቁ ብጹዓን ናቸው።--የእግዚአብሔር ተስፋዎችና ትዕዛዛት በልጃቸው ውስጥ አመስጋኝነትንና አክብሮትን መቀስቀስ እንዲችል ሕይወታቸው እውነተኛ የመለኮት ነጸብራቅ የሆኑ ወላጆች ብጹአን ናቸው፤ ደግነታቸው፣ ፍትሃዊነታቸውና ትዕግስተኛነታቸው ለልጆቻቸው የእግዚአብሔርን ፍቅር፣ ፍትሃዊነትና ትዕግስት ተርጉሞ የሚያቀርቡላቸው ወላጆች ብጹዓን ናቸው፤ ልጃቸው እንዲወዳቸው፣ እንዲታመንባቸውና እንዲታዘዛቸው በማስተማራቸው በሰማይ ያለውን አባቱን እንዲወድ፣ እንዲታመንበትና እንዲታዘዘው እያስተማሩ ናቸው። እንደዚህ ያለውን ስጦታ ለልጃቸው የሚሰጡ ወላጆች ከዘመናት ሁሉ ሀብት የበለጠ ውድ ሀብት--ለዘላለም የሚኖር ሀብት ሰጥተውታል ማለት ነው። --MH 375, 376 (1905). {1MCP 141.2}1MCPAmh 115.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents