Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የልጅ አመራር - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 53—የቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት

    ቤተ ክርስቲያን እንደ ጉበኛ — ጌታ ወላጆችን ልጆቻቸውን በፊታች ላለ ጊዜ እንዲያስተምሯቸው እና እንዲያዘጋጇቸው ለመርዳት የቤተ ክርስቲያናትን ትምህርት ቤትን ይጠቀማል፡፡ እንግዲያው ቤተክርስቲያን የትምህርትን ሥራ በትጋት ትያዝ እና ጌታ እንዲሆን የሚፈልገውን ታድርግ፡፡ CGAmh 295.1

    እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን በወጣቶች እና በልጆች ላይ ቅናተኛ ትሆን ዘንድ፣ እና ጠላት መቅረቡን ተመልክቶ የአደጋ ማስጠንቀቂያን እንደሚሰጥ ተረኛ ወታደር ጉበኛ አድርጎ ሾሟታል፡፡ ነገር ግን ቤተክርስቲያን ሁኔታዋን አላስተዋለችም፡፡ ተረኛ ወታደር ሆና ተኝታለች፡፡ በዚህ አደገኛ ጊዜ አባቶች እና እናቶች ነቅተው ለራሳቸው ሕይወት እንደሚሰሩ መስራት አለባው፣ ሁሉ መነቃቃት እና መሥራት አለባቸው፣ ካልሆነ ብዙ ወጣቶች ለዘላለም ይጠፋሉ፡፡ 601Counsels to Parents, Teachers, and Students, 167.CGAmh 295.2

    የእግዚአብሔር ህግ ከፍ መደረግ አለበት— ቤተክርስቲያኗ ልጆቿ በትምህርት ቤትም ሆነ በሌላ በማንኛውም ማህበር በብልሹ ልምዶች ተጽዕኖ ሥር እንዳይወድቁ በማስተማር እና በማሠልጠን ረገድ ልዩ ሥራ አላት፡፡ ዓለም በኃጢኣት የተሞላች እና የእግዚአብሔርን መጠይቆች ችላ ያለች ናት…፡፡ 602Counsels to Parents, Teachers, and Students, 165.CGAmh 295.3

    የፕሮቴስታንት አብያተ ክርስቲያናት የጳጳሳዊ ሥርዓት ልጅ የሆነውን ሐሰተኛ ሰንበትን ተቀብለው ከእግዚአብሔር ቅዱስ እና ብሩክ ቀን በላይ ከፍ ከፍ አድርገውታል፡፡ የሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን እውነተኛ ሰንበት አለመሆኑን እና እውነተኛው ሰንበት ምን እንደ ሆነ ከተገለጠልን በኋላ ይህን መታዘዛችን ግልጽ የሆነውን የእግዚአብሔርን ህግ የሚጻረር መሆኑን ለልጆቻችን በግልጽ ማሳወቅ የእኛ ተግባር ነው፡፡3Testimonies For The Church 6:193. CGAmh 295.4

    በሙያ የተካኑ ሠራተኞች ለክርስቶስ መሠልጠን አለባቸው— እንደ ቤተ-ክርስቲያን፣ እንደ ግለሰቦች፣ በፍርድ ጊዜ እንከን የሌለብን ሆነን መቆም የምንፈልግ ከሆነ፣ በአደራ በእጆቻችን በተሰጠን በታላቁ ሥራ የተለያዩ የሥራ ዘርፎች በተሻለ ሁኔታ ብቁ ይሆኑ ዘንድ ለወጣቶች ስልጠና ይበልጥ ብዙ ጥረት ማድረግ አለብን፡፡ የክርስቶስ ሥራ ሥራቸውን በትጋት እና በታማኝነት ለሚሰሩ በሙያ የተካኑ ሰራተኞች እጥረት ሳቢያ እንዳይሰናከል ተሰጥኦ ያላቸው ሰዎች ብልህ አእምሮዎች ከፍ ወዳለ ደረጃ ለመድረስ እንዲበረታ፣ እንዲሰለጥን እና እንዲስተካከል ጥበብ የተሞላበት ዕቅድ መዘርጋት አለብን፡፡ 603Counsels to Parents, Teachers, and Students, 43. CGAmh 296.1

    ሁሉም ወጭውን መጋራት አለበት— ሁሉም ወጭውን ይጋራ። የእርሷን ጥቅም መቀበል የሚገባቸው ሰዎች ትምህርት ቤት እየተከታተሉ መሆኑን ቤተክርስቲያኗ ታረጋግጥ፡፡ ደካማ ቤተሰቦች መታገዝ አለባቸው፡፡ በበራችን ላይ የሚገኙ በጣም አሳሳቢ ዕድሜ ላይ የሚገኙትን እና ለእግዚአብሔር አገልግሎት ብቁ የሚያደርጋቸውን እውቀት እና ልምድን ለማግኘት የእኛን እርዳታ የሚፈልጉትን ሰዎች ችላ የምንል ከሆነ እውነተኛ ሚስዮናውያን ነን ብለን ራሳችንን ልንጠራ አንችልም፡፡ ጌታ በልጆቻችን ትምህርት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድናደርግ ይፈልጋል፡፡5Testimonies For The Church 6:217.CGAmh 296.2

    ለወጣቶች ተገቢ ለሆነ ሥልጠና የገንዘብ ሸክምን መሸከም— በልዩ ልዩ አከባቢዎች ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ወጣቶችን በማሠልጠን እና በሚስዮናዊነት ሥራ ውስጥ የመሳተፍ ችሎታን እንዲያዳብሩ የማስተማር ከባድ ኃላፊነት እንደተጣለባቸው ሊሰማቸው ይገባል፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ ጠቃሚ ሰራተኛ ለመፍጠር ቃል የገቡ ነገር ግን በትምህርት ቤት እራሳቸውን መርዳት የማይችሉ ሰዎችን ከተመለከቱ እነርሱን ወደ አንድ ማሠልጠኛ ትምህርት ቤታችን የመላክ ሀላፊነት መውሰድ አለባቸው፡፡ በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ወደ አገልግሎት መምጣት የሚያስፈልገው እጅግ በጣም ጥሩ ችሎታ አለ፡፡ በጌታ የወይን እርሻ ውስጥ ጥሩ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ሰዎች አሉ፣ ነገር ግን ብዙዎች የሚፈልጉትን ትምህርት ማግኘት የማይችሉ ድሆች ስለሆኑ ያለ እርዳታ ይህን ማድረግ አይችሉም፡፡ አብያተ ክርስቲያናት እንደነዚህ ያሉ ወጭዎችን በመሳተፍ የመሸፈን ልዩ ዕድል እንዳገኙ ሊሰማቸው ይገባል፡፡ CGAmh 296.3

    በልባቸው ውስጥ በእውነት ያላቸው ሰዎች አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሁሉ እርዳታ ለማድረግ ልበ ቅኖች ናቸው፡፡ የእነርሱን ምሳሌ ይከተሉ ዘንድ ሌሎችንም ይመራሉ። አንዳንድ ትምህርት የሚያስፈልጋቸው ነገር ግን ለትምህርታቸው ሙሉ ወጪ መሸፈን የማይችሉ ሰዎች ካሉ አብያተ ክርስቲያናት እነርሱን በመርዳት ልግስናቸውን ያሳዩ፡፡ 604Counsels to Parents, Teachers, and Students, 69.CGAmh 297.1

    ከፍተኛ ትምህርትን ለማቋቋም የሚውል የትምህርት ቤት እርዳታ ገንዘብ— የትምህርት ሥራን ለማሻሻል ሲባል ትምህርት ቤቶችን ለማቋቋም የልግስና አስተዋጽኦ ገንዘብ ማሰባሰቢያ መንገድ ይፈጠር፡፡ በአብያተ ክርስቲያናት ጥቅም ይሰሩ ዘንድ በደንብ የሰለጠኑ፣ በደንብ የተማሩ ሰዎች እንፈልጋለን፡፡ ወጣቶቻችንን በሌሎች የኃይማኖት ክፍሎች ወደ ተቋቋሙ የትምህርት ተቋማት እና ኮሌጆች ለመላክ፣ የኃይማኖታቸው ሥልጠና ችላ ወደማይባልባቸው ትምህርት ቤቶች እነርሱን ለመሰብሰብ አመኔታ የሌለን መሆኑን ሐቁን ማቅረብ አለባቸው፡፡605 Counsels to Parents, Teachers, and Students, 44, 45. CGAmh 297.2

    ለሚስዮኖች ስጡ ነገር ግን በቤት ውስጥ ያሉትን ወጣቶችን ችላ አትበሉ — የቤተክርስቲያን አባላት በሌሎች ሥፍራዎች የሚሰራ የክርስቶስ ሥራ ወደፊት እንዲጓዝ ገንዘብን በመስጠት እና የራሳቸውን ልጆች የሰይጣንን ሥራ እና አገልግሎት እንዲያራምዱ መተው ይኖርባቸው ይሆን?606Testimonies For The Church 6:217. CGAmh 297.3

    ምንም እንኳን በዙሪያችን ላሉት ብዙ ህዝቦች ልባዊ ጥረት ማድረግ እና ሥራውን ውጭ አገር ወደሚገኙት ሌሎች መስኮች መግፋት ቢኖርብንም፣ የልጆቻችን እና የወጣቶቻችን ትምህርት ችላ እንድንል ሊያደርገን የሚችል በዚህ መስመር የሚሰራ ምንም ዓይነት ሥራ የለም። እነርሱ የእግዚአብሔር ሠራተኞች እንዲሆኑ መሰልጠን አለባቸው፡፡ ልጆች ለእግዚአብሔር እና ለሥራው እንደ ብረት የበረቱ ተማኞች ይሆኑ ዘንድ ወላጆችም ሆኑ አስተማሪዎች፣ በመምሪያ እና ምሳሌ፣ የእውነት እና ሐቀኛነት መርሆዎችን በአእምሮአቸው እና በልባቸው ማሳደግ አለባቸው፡፡ 607Counsels to Parents, Teachers, and Students, 165.CGAmh 297.4

    በእምነት ጸልዩ; እግዚአብሔር መንገዶችን ይከፍታል— አንዳንዶች “እንደዚህ ያሉ ትምህርት ቤቶች እንዴት ይቋቋማሉ?” ብለው ይጠይቁ ይሆናል፤ እኛ ሀብታም ሰዎች አይደለንም፣ ነገር ግን በእምነት ከጸለይንና ጌታ ሥራችንን እንዲሠራ ከፈቀድን፣ ለወጣቶቻችን ትምህርት በቅዱሳት መጻሕፍት እና በሌሎች መጽሐፍት ብቻ ሳይሆን በሌሎች የሙያ ሥራዎች ትምህርት እንዲያገኙ ራቅ ባሉ ሥፍራዎች ትናንሽ ትምህርት ቤቶችን ለማቋቋም በፊታችን መንገዶችን ይከፍታል፡፡608 Counsels to Parents, Teachers, and Students, 204. CGAmh 298.1

    “ተነስተን እንገንባ።” [ማስታወሻ፡- ይህ ከግል ቤቷ አቅራቢያ የቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት እንዲገነባ የሚጠይቅ ሐምሌ 14 ቀን 1902 የተሰጠው አድራሻ ክፍል ነው]— ክሪስታል ስፕሪንግስ [ሳኒታሪየም፣ ካሊፎርኒያ] ውስጥ በትክክለኛው መንገድ ሥራውን መመስረት አለብን፡፡ ልጆቻችን እዚህ ናቸው፡፡ በዓለም— ማለትም በኃጢያቷ፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዛት በችላ ባይነቷ እንዲበከሉ እንፈቅድላቸዋለን? ልጆቻቸው ለመመረዝ ተጋላጭ ወደሚሆኑበት ወደ ሕዝብ ትምህርት ቤቶች ለመላክ በማቀድ ላይ ያሉ ሰዎችን እጠይቃለሁ፣ እንዴት እንዲህ ዓይነቱን አደጋ እንዴት ልታስተናግዱ ትችላላችሁ?CGAmh 298.2

    ለልጆቻችን የቤተክርስቲያን ትምህርት ቤትን ግንባታ ማቆም እንፈልጋለን፡፡ ለገንዘብ ብዙ ጥሪዎች ስለሚደረጉ፣ በቂ ገንዘብን ለማግኘት ወይም ትንሽ እና ምቹ የሆነ ትምህርት ቤት ለመገንባት ከፍተኛ የሆነ ፍላጎትን ለማነሳሳት ከባድ ጉዳይ ይመስላል፡፡ ለትምህርት ቤት ዓላማ የሚጠቀሙበት እስከሆነ ድረስ ለተወሰነ ጊዜ የተወሰነ መሬት ለእነርሱ እንደምከራይ ለትምህርት ቤቱ ኮሚቴ ተናግሬያለው፡፡ ልጆቻችን የእግዚአብሔር ልጅ ሕያው ደም እና ሥጋ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ሊማሩ የሚችሉበት ህንፃን ለማቆም የሚያስችለን በቂ ፍላጎት እንደሚያነሳሳ ተስፋ አደርጋለሁ…፡፡ የእግዚአብሔር ቃል የሚስተማርበት የዚህን የትምህርት ቤት ህንፃ ግንባታ ለማቆም ፍላጎት አይኖራችሁምን? አንድ ሰው እየተሰራ ስላለው ትምህርት ቤት ምን ያህል ለመስጠት ፈቃደኛ እንደሆነ ሲጠየቅ፣ በቀን ሦስት ዶላር እና ምግብ እና መጠለያ ብንሰጠው እንደሚረዳን ነግሮን ነበር፡፡ ነገር ግን እኛ እንደዚህ አይነት ሥጦታዎችን አንፈልግም። እርዳታ ወደ እኛ ይመጣል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምርበት፣ ጸሎቶች ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡበት፣ እና ልጆች የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ መርኾዎችን የሚማሩበት የትምህርት ቤት ግንባታ እንዲኖረን ተስፋ እናደርጋለን። ከጎናችን ሊቆም የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህን ሕንጻ ለማቆም የመሳተፍ ፍላጎት እንደሚኖረው እንጠብቃለን፡፡በዚህ ኮረብታ ላይ አነስተኛ የሰራተኛ ሠራዊት እንዲሰለጥኑ እንጠብቃለን፡፡ 609Manuscript Releases 10:0.1902.CGAmh 298.3

    በጉልበት ሥራ እንዲሁም በገንዘብ እርዱ — ሁሉም ለዚህ ድርጅት ስኬት ፍላጎት እንዳላቸው እናውቃለን። ትርፍ ጊዜ ያላቸው ሰዎች ይህንን የትምህርት ቤት ግንባታ ለማገዝ ጥቂት ቀናትን ይስጡ፡፡ አስፈላጊውን ቁሳቁስ ብቻ ለመግዛት እንኳ ገና በቂ የገንዘብ መዋጮ አልተዋጣም። በተሰጠው ነገር ደስተኞች ነን፣ ነገር ግን በቅርቡ ልጆቻችን መጽሐፍ ቅዱስን የሚያጠኑበት የእውነተኛ ትምህርት መሠረት የሆነ ቦታ ይኖረን ዘንድ ሁሉም ሰው ይህንን ጉዳይ በትኩረት እንዲይዝ አሁን እንጠይቃለን፡፡ እግዚአብሔር መፍራት— መስተማር ያለበት የመጀመሪያ ትምህርት— የጥበብ መጀመሪያ ነው፡፡CGAmh 299.1

    ይህ ጉዳይ መጎተት ያለበት ምንም ምክንያት የለም፡፡ ሕንፃው ተሠርቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ እያንዳንዱን ሰው በማይዝል ፍላጎት በትጋት ለመርዳት ተሳትፎ ያድርግ። እያንዳንዱ ሰው የሆነ ነገር ይስራ፡፡ አንዳንዶች ሥራውን ለማገዝ ጠዋት አሥር ሰዓት ላይ መነሳት ሊኖርባቸው ይችላል። እኔ በተለምዶ ሥራዬን የምጀምረው ከዚያን ሰዓት በፊት ነው። ልክ ጎህ ሲቀድ፣ አንዳንዶች ቁርስ ከመብላታቸው በፊት አንድ ወይም ሁለት ሰዓት አስተዋጽኦ በማድረግ ህንፃውን በመሥራት መጀመር ይችላሉ፡፡ ሌሎች ይህን ማድረግ አልቻሉም፣ ነገር ግን ሁሉም ግን ልጆች ለእግዚአብሔር አገልግሎት ተግሣጽ እና ስልጠና በሚያገኙበት ትምህርት ቤት እንዲማሩ ያላቸውን ፍላጎት ለማሳየት አንድ ነገር ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ የእርሱ በረከት በእርግጠኝነት እንደዚህ ባሉ ጥረቶች ሁሉ ላይ ያርፋል…፡፡CGAmh 299.2

    ወንድሞች እና እህቶች፣ የቤተክርስቲያን ትምህርት ቤትን ለመገንባት ምን ታደርጋላችሁ? እያንዳንዱ ሰው የዚህ ትምህርት ቤት ግንባታ ባለቤት መሆንን እንደ ልዩ ዕድል እና በረከት እንደሚቆጥረው እምነታችን ነው። ተነስተን እንሠራለን በማለት የሥራውን መንፈስ እንያዝ፡፡ ሁሉም በአንድነት ስራው ላይ የሚሳተፍ ከሆነ፣ በየቀኑ ልጆቻችን የጌታን መንገድ የሚማሩበት ትምህርት ቤት በቅርቡ ይኖረናል፡፡ የተቻለንን ሁሉ ስናደርግ የእግዚአብሔር በረከት በእኛ ላይ ያርፋል፡፡ ተነስተን አንገነባምን? 610Ibid.CGAmh 299.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents