Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የልጅ አመራር - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 58—ለተግባራዊ ሕይወት ማሰልጠን

    ለምን እግዚአብሔር ለአዳምና ለሔዋን ሥራን መረጠ— ጌታ አዳምንና ሔዋንን ፈጠረና የአትክልት ስፍራውን እንዲንከባከቡ እና ለጌታ እንዲጠብቁ በኤደን ገነት ውስጥ አኖራቸው፡፡ የተወሰነ ሥራ ማግኘታቸው ለደስታቸው ነበር፣ አለበለዚያ ጌታ ሥራ ባልመረጠላቸው ነበር። 660Manuscript Releases 24b, 1894.CGAmh 327.1

    ዓለም ከመፈጠሩ በፊት ከአብ ጋር በሚማከሩበት ጊዜ ጌታ እግዚአብሔር በኤደን ውስጥ ለአዳምና ለሔዋን የአትክልት ስፍራ እንዲተክልና የፍራፍሬ ዛፎችን የመንከባከብ እንዲሁም ዕፅዋትን የማልማትና የማበጀት ሥራ እንዲሠጣቸው ታስቦ ነበር፡፡ ፋይዳ ያለው ሥራ ጥበቃ እንዲሆንላቸው እና እስከ ትውልዶች ሁሉ ድረስ እስከ ምድር ታሪክ መዝጊያ ድረስ እንዲዘልቅ ነበር፡፡661The Signs of the Times, August 13, 1896. CGAmh 327.2

    የኢየሱስ ምሳሌ እንደ ፍጹም ሰራተኛ— በምድራዊ ሕይወቱ፣ ክርስቶስ ... በቤት ውስጥ ታዛዥ እና አጋዥ ነበር። እርሱ የአናጢነትን ሙያ ተምሮ በናዝሬት ትንሿ ቤት ውስጥ በገዛ እጁ ይሠራ ነበር፡፡... መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ኢየሱስ ሲናገር “ሕፃኑም አደገ በጥበብም ሞልቶበት በመንፈስ ጠነከረ፣ የእግዚአብሔርም ጸጋ በእርሱ ላይ ነበር” ይላል፡፡ እርሱ በልጅነት እና በወጣትነት ዕድሜው ሥራ ሲሰራ፣ አእምሮው እና ሰውነቱ ጎለበቱ፡፡ እርሱ አካላዊ ኃይሎቹን በግዴለሽነት አልተጠቀመም ነበር፣ ነገር ግን በእያንዳንዱ ዘርፍ ላይ ምርጥ ስራን እንዲሰራ ጤናን የሚጠብቅ አይነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሰጣቸው፡፡ በመሳሪያዎች አያያዝም ቢሆን እንከን ያለበት ለመሆን ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ በባህሪው ፍጹም እንደ ነበረ ሁሉ እንደ ሥራ እንደሚሰራ ሰውም ፍጹም ነበር፡፡662Fundamentals of Christian Education, 417, 418.CGAmh 327.3

    እርሱ የሰራው እያንዳንዱ ዕቃ በጥሩ ሁኔታ የተሰራ፣ የተለያዩ ክፍሎች በትክክል የሚጣጠሙ፣ መላው አካል ፈተናዎችን መቋቋም የሚችል ነው፡፡4Evangelism, 378.CGAmh 328.1

    በታጋሽ እጆች በየቀኑ ይለፋ ነበር— ኢየሱስ በምሳሌው የሰውን ዝቅተኛ የሕይወት ጎዳናዎችን የተቀደሰ አድርጓል፡፡... ህይወቱ በትጋት የተሞላ አምራች ነበር፡፡ የሰማይ ባለ ግርማ የሆነው እርሱ ቀላል የተራ ሠራተኛ ልብስ ለብሶ በጎዳናዎች ላይ ተመላለሰ፡፡ ወደ ትሁት ሥራው በመሄድ እና በመመለስ በተራራማው አቀበቶች ላይ እና ታች በማለት ይለፋ ነበር፡፡ መላእክት አድካሚውን አቀበት በክንፋቸው ላይ እንዲሸከሙት ወይም ተራ የሆነውን ተግባሩን በማከናወን ኃይላቸውን እንዲሰጡት አልተላኩም፡፡ ሆኖም በዕለት ተዕለት ሥራው ለቤተሰቡ የድጋፍ አስተዋጽኦ ለማድረግ ሲወጣ አምስት ሺህ የተራቡትን ነፍሳት በገሊላ ዳርቻ በመመገብ ተአምር እንዳደረገው ሁሉ ተመሳሳይ ኃይል ነበረው፡፡CGAmh 328.2

    እርሱ ግን ሸክሙን ለመቀነስ ወይም ድካሙን ለማቃለል መለኮታዊ ኃይሉን አልተጠቀመም፡፡ እርሱ ከተያያዥ ሕመሞቹ ሁሉ ጋር የሰው ልጅን መልክ ለብሶ ለከባድ ፈተናዎቹ ፍንክች አላለም፡፡ በገበሬ ቤት ውስጥ ኖረ፣ ሻካራ ልብስ ለብሰ፣ ከተራ ሰዎች ጋር ተቀላቀ፣ በየቀኑ በታጋሽ እጆቹ ይለፋ ነበር፡፡ የእርሱ ምሳሌ እንደሚያሳየን ታታሪ መሆን የሰው ግዴታ፣ ሥራ ክቡር እንደሆነ ነው፡፡ 663Health Reformer, October, 1876. CGAmh 328.3

    የሕይወትን ተራ ግዴታዎችን በሚወጣበት ጊዜ ሰዎች ከእግዚአብሔር ዘንድ አጠገብ እንዴት መኖር እንደሚችሉ ማስተማር ይችል ዘንድ ኢየሱስ ያልተከበረ ወይም ያልታወቀ ሆኖ በናዝሬት ለረጅም ጊዜ ኖረ፡፡ የሰማይ ልዑል የሆነው ክርስቶስ ራሱን ዝቅ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ከባድ ሸክሞችን እና እጅግ በጣም ተራ ስራዎችን መስራቱ፣ ዝቅ ማለቱ ለመላእክት ምስጢር ነበር፡፡ የሰዎችን ልጆች ድካም፣ ሀዘን እና ልፋትን ማወቅ ይችል ዘንድ ከእኛ እንደ አንዱ ለመሆን ይህን አደረገ፡፡6Ibid.CGAmh 328.4

    ጠቃሚ ለሆኑት ክንውኖች ምኞትን ማነቃቃት— በልጆችና በወጣቶች ውስጥ ለራሳቸው የሚጠቅም እና ሌሎችንም የሚራዳ ነገር ለመስራት ምኞታቸው መነቃቃት አለበት፡፡ አእምሮን እና ባህሪን የሚያዳብር፣ እጆች ጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስተምር፣ ወጣቶች በህይወት ሸክም ውስጥ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የሚያሠለጥን እንቅስቃሴ ለአካል ብርታት የሚሰጥ እና እያንዳንዱን ብቃት የሚቀሰቅስ ነው፡፡ እናም በበጎ ታታሪነት ውስጥ መልካም ለመሥራት የመኖር ልማድን በማጎልበት ውስጥ ሽልማት አለ፡፡ 664Counsels to Parents, Teachers, and Students, 147.CGAmh 328.5

    ሕይወት ማለት ቀና ሥራ፣ ኃላፊነት፣ ተንከባካቢ ማለት እንደሆነ ማስተማር ያስፈልጋል፡፡ ድንገተኛ ሁኔታዎችን መቋቋም የሚችሉ ወንዶች እና ሴቶች— ተግባራዊ እንዲሆኑ የሚያስችል ስልጠና ያስፈልጋቸዋል፡፡ በስርዓት የተሰራ፣ በጥሩ ሁኔታ ቁጥጥር የሚደረግበት ሥራ፣ በሕይወት ውስጥ የሚከሰቱት ውጣ ውረዶች ለመከላከል ብቻ ሳይሆን ለሁለንተናዊ ዕድገት እገዛ ለማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ሊማሩ ይገባል፡፡8Education, 215.CGAmh 329.1

    የጉልበት ሥራ የሚያዋርድ አይደለም— ሥራን እንደ አዋራጅ መቁጠር በብዙ ሰዎች ዘንድ እውቅና ያለው ስህተት ነው፤ በመሆኑም ወጣት ወንዶች አስተማሪዎች፣ ጸሐፊዎች፣ ነጋዴዎች፣ ጠበቆች እንዲሆኑ እና አካላዊ የጉልበት ሥራን የማይጠይቅ ማንኛውንም ቦታ ለመያዝ ራሳቸውን ለማስተማር በጣም ይጓጓሉ፡፡ ወጣት ሴቶች የቤት ውስጥ ሥራን እንደ አዋራጅ ይቆጥራሉ፡፡ እና በጣም አደገኛ ካልሆነ፣ ምንም እንኳን የቤት ውስጥ ሥራን ለማከናወን የሚያስፈልገው የአካል እንቅስቃሴ ጤናን ለማሳደግ የተሰላ ቢሆንም፣ አስተማሪዎች ወይም ጸሐፊዎች ለመሆን የሚያስችላቸውን ትምህርት ይፈልጋሉ ወይም እንቅስቃሴ የሌለው ቤት ውስጥ የሚያደርጋቸውን የተወሰነ ሙያ ይማራሉ፡፡ 665Counsels to Parents, Teachers, and Students, 291.CGAmh 329.2

    ዓለም ምንም ጠቃሚ ሥራ ባለማወቃቸው በሚኮሩ ወጣት ወንዶችና ሴቶች ተሞልቷል፤ ደግሞም እነርሱ ሁልጊዜ ማለት በሚቻል አይነት ሁኔታ፣ የማይረቡ፣ ከንቱ፣ ታይታን የሚወዱ፣ ደስተኞች ያልሆኑ፣ እርካታ የሌላቸው እና እጅግ አብዛኛውን ጊዜ ብኩኖች እና መርህ አልባ ናቸው። እንደነዚህ ያሉት ባህሪያት ለሕብረተሰቡ ጥፋት እና ለወላጆቻቸው ውርደት ናቸው፡፡10Health Reformer, December, 1877.CGAmh 329.3

    አነሳ እና የባርነት ሥራ ቢመስልም እንኳ፣ ማናችንም ብንሆን በስራ ማፈር የለብንም፡፡ ሥራ ያስከብራል፡፡ በጭንቅላት ወይም በእጆች የሚደክሙ ሁሉ ሰራተኛ ወንዶች ወይም ሰራተኛ ሴቶች ናቸው፡፡ እንዲሁም ሁሉም ወደ ስብሰባ እንደሚሄዱ ሁሉ በማጠቢያ ገንዳ ሲሰሩ ወይም ሳህኖችን ሲያጥቡ ግዴታቸውን እየተወጡ እና ሃይማኖታቸውን እያከበሩ ናቸው ማለት ነው፡፡ እጆች እጅግ በተለመደው ሥራ ላይ በሚሠሩበት ጊዜ አዕምሮ በንጹህ እና በቅዱስ ሀሳቦች ከፍ ይላል፣ ይክብራልም፡፡ 666Testimonies For The Church 4:590.CGAmh 330.1

    ወጣትነት የሥራ ባሪያዎች ሳይሆኑ ጌቶች ይሁኑ— ወጣቱ ትክክለኛውን የሥራ ክብር እንዲያይ ሊመራ ይገባል። 667Education, 214.CGAmh 330.2

    አካላዊ ድካም ዝቅ ተደርጎ ከሚታይባቸው አንዱ ትልቁ ምክንያት ብዙውን ጊዜ ሥራው የሚከናወንበት የደንታ ቢስነት መንገድ ነው፡፡ ሥራው የሚሰራው አስፈላጊ በመሆኑ እንጂ በምርጫ አይደለም፡፡ ሠራተኛው ልቡን በሥራው ላይ አይጥልም፣ እንዲሁም የራሱን አክብሮት አይጠብቅም ወይም በሌሎች ዘንድ አክብሮትን አያገኝም። ያለ ማሽን የሚሰራ የሥራ ሥልጠና ይህንን ስህተት ማረም አለበት፡፡ የትክክለኛነትን እና የጠንቃቃነት ልማዶችን ማዳበር አለበት፡፡ ተማሪዎች ዘዴ እና ብልሃትን መማር አለባቸው፤ ጊዜን በቁጠባ መጠቀምን እና እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ዋጋ እንዲኖረው መማር አለባቸው፡፡ የተመረጡ ዘዴዎችን መማር ብቻ ሳይሆን ዘወትር ለመሻሻል ምኞት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ የሰው አእምሮ እና እጆች ማድረግ በሚችሉት መጠን ሁሉ ሥራቸውን ፍጹም የተሟላ ለማድረግ ዓላማቸው ይሁን፡፡ CGAmh 330.3

    እንዲህ ዓይነቱ ሥልጠና ወጣቶችን ጌቶች እንጂ የሥራ ባሪያዎች አያደርጋቸውም፡፡ እርሱ በብርቱ የሚለፋውን ሰው ዕጣ ቀለል ያደርጋል፣ ተራ የሆነውንም ሥራ እንኳን የከበረ ያደርጋል። ስራን የማያስደስት አድርጎ የሚቆጥር እና በራሱ በመደሰት ድንቁርና የሚኖር፣ ለማሻሻል ምንም ጥረት የማያደርግ፣ እርሱ በእርግጥ ሸክም ሆኖ ያገኘዋል። ነገር ግን በተራ ሥራ ውስጥ ለሳይንስ እውቅና የሚሰጡ ሰዎች በውስጡ ክብር እና ውበትን ያያሉ፣ በታማኝነት እና በብቃት ሥራውን በማከናወናቸውም ይደሰታሉ። 668 Education, 222.CGAmh 330.4

    ሐብት የሕይወት ተግባራዊ ሥልጠና ላለመውሰድ የሚቀርብ ምክንየት አይደለም— በብዙ ሁኔታዎች አንጻር ሀብታም የሆኑ ወላጆች በተግባራዊ የሕይወት ግዴታዎችም ሆነ በሳይንሱ ላይ ለልጆቻቸው ትምህርት መስጠቱ አስፈላጊ እንደሆነ አይሰማቸውም። ጠቃሚ የጉልበት ሥራን በጥልቀት እንዲገነዘቡ ለልጆቻቸው አዕምሮ እና ሥነ ምግባሮች እንዲሁም ለወደፊቱ ጠቃሚነታቸው ያለውን አስፈላጊነት አይመለከቱም፡፡ ይህ ለልጆቻቸው ነው፣ ምክንያቱም ክፉ ዕድል ቢመጣ፣ እጆቻቸውን እንዴት እንደሚጠቀሙ ቢያውቁ ኖሮ በነፃነት ክብር መቆም ይችሉ ነበር፡፡ የጉልበት ክምችት ካላቸው ዶላር ባይኖራቸውም ድሆች ሊሆኑ አይችሉም፡፡CGAmh 331.1

    በወጣትነት ዕድሜ ውስጥ በባለጸጋነት ሁኔታዎች ውስጥ የነበሩት ብዙዎች ሀብታቸውን ሊነጠቁ እና ወላጆቻቸው፣ ወንድሞቻቸው እና እህቶቻቸው ለኑሮ በእነርሱ ላይ ጥገኛ ሊሆኑ ይችላሉ። ስለዚህ እያንዳንዱ ወጣት ሥራ ማወቁ ለማንኛውም ድንገተኛ ሁኔታ ዝግጁ እንዲሆኑ ምን ያህል አስፈላጊነት ያለው ነገር ነው! ሐብታሞች ሐብታቸው ለተግባራዊ ሕይወት ብቁ የሚያደርጋቸውን ጠቃሚ የሥራ እውቀት እንዳያገኙ በወንዶች እና ሴቶች ልጆቻቸው መንገድ ላይ የሚቆም ከሆነ ሐብት እርግማን ነው፡፡ 669Testimonies For The Church 3:150.CGAmh 331.2

    ልጆች የቤት ውስጥ ሥራዎችን መካፈል አለባቸው— ታማኝ እናት የልጆቿን ድንገተኛ አምሮቶችን ለማሟላት እና ሥራ እንዳይሰሩ ለማድረግ የፋሽን አምላኪ አትሆንም፣ መሆንም አትችልም፣ ወይም ደግሞ የቤቱ ሥራ ባሪያም አትሆንም፡፡ የተግባራዊ ሕይወት ዕውቀት እንዲኖራቸው የቤቱን ሥራ እንዲጋሩ ታስተምራቸዋለች፡፡ ልጆች ሥራን ከእናታቸው ጋር ከተጋሩ ጠቃሚ ሥራ ደስታን ለመስጠት አስፈላጊ እንደሆነ፣ ከሚያዋርድ ይልቅ የሚያስከብር እንደሆነ አድርገው ይመለከቱታል፡፡ ነገር ግን እናት ሴት ልጆቿን ሰነፎች እንዲሆኑ ካስተማረቻቸው፣ ከባድ የቤት ውስጥ ሸክሞችን የምትሸከም ሲሆን፣ እሷን እንደ ባሪያ ዝቅ አድርገው እንዲመለከቷት፣ እነርሱ መስራት ያለባቸውን ነገሮችን እንዲያቆዩ እያስተማረቻቸው ነው፡፡ እናት መቼም ክብሯን መጠበቅ አለባት፡፡ 670Pacific Health Journal, June, 1890.CGAmh 331.3

    አንዳንድ እናቶች ሴት ልጆቻቸውን ከልፋትና ከሥራ ነጻ በማድረግ ስህተት ይሰራሉ፡፡ ይህን በማድረጋቸው በስንፍና ያበረታቷቸዋል፡፡ እነዚህ እናቶች አንዳንድ ጊዜ የሚያቀርቡት ምክንያት “ሴት ልጆቼ ጠንካራ አይደሉም” የሚል ነው፡፡ ነገር ግን እነርሱን ደካማ እና ውጤታማ ያልሆኑ ለማድረግ እርግጠኛውን መንገድ ይከተላሉ፡፡ በትክክለኛው መንገድ የሚመራ ሥራ በሕይወት ውስጥ የሚያስቸግሩ የተለያዩ ፈተናዎችን እንዲቋቋሙ ጠንካራ፣ ብርቱ፣ ደስተኛ እና ደፋር እንዲሆኑ የሚያስፈልጋቸው ሥራ ብቻ ነው፡፡ 671The Signs of the Times, August 19, 1875.CGAmh 332.1

    ጠቃሚ ተግባራትን ለልጆች ስጧቸው— ወላጆች ለልጆቻቸው የሥራ ስምሪት ለመስጠት ቸል የማለታቸው ግድየለሽነት የብዙ ወጣቶችን ሕይወት በማጥፋት እና በሚያሳዝን ሁኔታ የእነርሱን ጠቃሚነት በማሽመድመድ ሊነገር የማይቻል ክፋትን አስከትሏል፡፡CGAmh 332.2

    እግዚአብሔር ወላጆችም ሆኑ አስተማሪዎች ልጆችን በዕለት ተዕለት የሕይወት ተግባራዊ ግዴታዎች እንዲያሠለጥኗቸው ይፈልጋል፡፡ ታታሪነትን አበረታቱ፡፡ ሴት ልጆች— እና ከቤት ውጭ ሥራ የሌላቸው ወንዶችም እንኳን — እናትን እንዴት መርዳት እንደሚችሉ መማር አለባቸው፡፡ ከልጅነት ጊዜ ጀምሮ ወንዶች እና ሴቶች በቤተሰብ ድርጅት ሥራ ውስጥ በእውቀት በማገዝ ከባድ ሸክሞችን እንዲሸከሙ ማስተማር አለባቸው፡፡ እናቶች፣ ልጆቻችሁን እጆጃቸውን እንዴት እንደሚጠቀሙ በትዕግሥት አሳየአቸው፡፡ እጆቻቸው በቤተሰብ ሥራ ውስጥ ልክ እንደ እናንተ በብቃት መጠቀምን እንዲገነዘቡ አድርጓቸው፡፡ 672The Review and Herald, September 8, 1904. CGAmh 332.3

    ቤተሰብ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ልጅ አንድ የሚሸከመው የቤተሰብ ሸክም ክፍል ሊኖረው ይገባል፣ ስራውንም በታማኝነት እና በደስታ ማከነወንን መማር አለበት። ስራው በዚህ መንገድ ከተከፋፈለ እና ልጆች ተገቢ ሀላፊነቶችን መሸከም የለመዱ ከሆነ ማንም የቤተሰቡ አባል ከመጠን በላይ ጫና አይበዛበትም፣ በቤት ውስጥም ሁሉም ነገር ደስ በሚያሰኝ እና በተቀላጠፈ ሁኔታ ይከናዋናል። እያንዳንዱ ሰው የቤቱ ዝርዝር ጉዳዮችን በደንብ ስለሚያውቅ እና ፍላጎት ስለሚያድርበት ትክክለኛ ቁጠባ ይመሰረታል።18The Signs of the Times, August 23, 1877.CGAmh 332.4

    ምግብ ማብሰል እና ሥፌት መስፋት፣ መሰረታዊ ትምህርቶች ናቸው— እናቶች ሴት ልጆቻቸውን ይዘው ወደ ማእድ ቤት በመግባት በመብሰያ ክፍል ውስጥ የተሟላ ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ እንዲሁም መሰረታዊ የልብስ ስፌት ጥበብ ሊያስተምሯቸው ይገባል፡፡ ልብሶችን በቁጠባ እንዴት እንደሚቆርጡ እና በንጽህና እንዴት እንደሚሰፉ ሊያስተምሯቸው ይገባል፡፡ አንዳንድ እናቶች ልምድ የሌላቸውን ሴት ልጆቻቸውን በትዕግሥት ለማስተማር ይህንን ችግር ከመቀበል ይልቅ ሁሉንም ነገር እራሳቸው ማከናወን ይመርጣሉ፡፡ ነገር ግን ይህን በማድረጋቸው አስፈላጊ የሆነውን የትምህርት ዘርፍ ችላ በማለት በልጆቻቸው ላይ ትልቅ ስህተት ይፈጽማሉ፤ ምክንያቱም የእነዚህ ነገሮች እውቀት በማጣታቸው ካደጉ በኋላ እፍረት ይሰማቸዋል፡፡ 673An Appeal to Mothers, 15.CGAmh 333.1

    ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች ልጆች ሥልጠና ስጧቸው— ወንዶችም ሆኑ ሴቶች በቤት ሥራ ውስጥ ድርሻ ስላላቸው ወንዶች እና ሴቶች ልጆች የቤተሰብ ግዴታዎች እውቀት ማግኘት አለባቸው፡፡ አልጋ ማንጠፍ እና አንድን ክፍል በሥርዓት ማስያዝ፣ ሰሃኖችን ማጠብ፣ ምግብ ማዘጋጀት፣ የራሱን ልብስ ማጠብ እና መጠገን ማንኛውንም ወንድ ከወንድነት ዝቅ የማያደርግ ሥልጠና ነው፤ የበለጠ ደስተኛ እና የበለጠ ጠቃሚ ያደርገዋል። እንዲሁም ሴቶች ልጆች በበኩላቸው ፈረስ መጫን እና መጋለብን መማር ከቻሉ፣ [ማስታወሻ፡ ይህ የተፃፈው እ.ኤ.አ. በ 1903 ነው] የመጋዝ እና የመዶሻ አያያዝን፣ እንዲሁም ቆሻሻ መጥረግ እና ቀለም መቀባትን ካወቁ፣ የሕይወትን ድንገተኛ ሁኔታዎችን ለመግጠም በተሻለ ሁኔታ ብቁ ይሆናሉ። 674Education, 216, 217.CGAmh 333.2

    ሴት ልጆቻችን ልክ እንደ ወንዶች ልጆቻችን ሁሉ ተገቢውን የጊዜ አጠቃቀም መማራቸው በጣም አስፈላጊ ነው፣ እንዲሁም እነርሱ ሰዓትን በሚጠቀሙበት መንገድ በእግዚአብሄር ዘንድ እኩል ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ሕይወት የተሰጠን እኛ ያለንን ተሰጥኦዎችን በጥበብ እንድናሻሽል ነው፡፡ 675Health Reformer, December, 1877.CGAmh 333.3

    የእናትን ጥንካሬ መጠበቅ ልዩ አጋጣሚዎችን ፈልጉ—በየቀኑ የሚከናወኑ የቤት ሥራዎች አሉ— እነርሱም ምግብ ማብሰል፣ ሰሃኖችን ማጠብ፣ መጥረግ እና አቧራን ማስወገድ ናቸው፡፡ እናቶች፣ ሴት ልጆቻችሁ እነዚህን የዕለት ተዕለት ግዴታዎችን እንዲወጡ አስተምራችኋልን?... ጡንቻዎቻቸው እንቅስቃሴ ያስፈልጋቸዋል፡፡ በመዝለል እና ኳስ ወይም ክሮኩዌት በመጫወት የአካል እንቅስቃሴ ከማድረግ ይልቅ የአካል እንቅስቃሴያቸው ለተወሰነ ዓላማ ይሁን፡፡ 676Manuscript Releases 12:9, 1898.CGAmh 334.1

    ልጆች ከቤተሰብ ሸክሞች ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ አስተምሯቸው፡፡ በተወሰነ ጠቃሚ ሥራ ላይ እንዲሰማሩ አድርጓቸው፡፡ ሥራቸውን በቀላል እና በጥሩ ሁኔታ እንዴት መስራት እንዳለባቸው አሳዩዋቸው፡፡ የእናታቸውን ሸክም በማቃለል ጥንካሬዋን እየጠበቁ እና ህይወቷን እያራዘሙ እንደሆነ እንዲገነዘቡ እርዷቸው፡፡ አያሌ የዛሉ እናቶች ያለ ጊዜያቸው ወደ መቃብር የገቡት ልጆቻቸው ሸክሟን እንዲካፈሉ ካለማስተማር በስተቀር በሌላ ምንም ምክንያት አይደለም፡፡ በቤት ውስጥ ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ የአገልግሎት መንፈስን በማበረታታት ወላጆች ልጆቻቸውን ከራስ ወዳድነት ነጻ ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ እንዲቀርቡ ያደርጓቸዋል፡፡23Manuscript Releases 7:0.1903.CGAmh 334.2

    በደስተኝነት ውስጥ ያለ ጥናት— ልጆች ሆይ፣ እናታችሁን ቀላል ባለ ወንበር ላይ አስቀምጧት እና መጀመሪያ ምን መስራት እንደምትፈልግ እንድታሳያችሁ ጠይቋት። ይህ ብዙ ለዛሉ፣ ከመጠን በላይ በሥራ ለተጠመዱ እናቶች ምንኛ አስገራሚ ይሆናል! ልጆች እና ወጣቶች መቼም የቤት ውስጥ ሥራዎችን በታማኝነት በመፈፀም የደከሙ እጆችን እና የዛለ ልብ እና አዕምሮን እስኪያሳርፉ ድረስ የእርካታ ሰላም አይሰማቸውም፡፡ እነዚህ የከፍተኛ ትምህርትን ለመቀበል ወደፊት የሚያራምዷቸው መሰላል ለይ ያሉ በእድገት ደረጃዎች ናቸው፡፡ CGAmh 334.3

    ለእውነተኛ የቤት ሰራተኛ እርካታ እና ሰላምን የሚያመጣው የእለት ተእለት ተግባሮችን በታማኝነት መፈጸም ነው። የድርሻቸውን የቤት ሀላፊነቶችን ለመሸከም ችላ የሚሉ ሰዎች በብቸኝነት እና አለመርካት የሚቸገሩ ሰዎች ናቸው፤ ምክንያቱም ሌሎች ደስተኛ የሆኑት ደስተኞች የሆኑበት ምክንያት በእናት ወይም በሌሎች የቤተሰቡ አባላት ላይ የሚያርፈውን የየዕለት የሥራ ድርሻ ስለሚጋሩ ደስተኛ የመሆናቸውን እውነት አልተማሩም። ብዙዎች ቢረዱት ለመጻኢ ጥቅማቸው አጅግ አስፈላጊ የሆኑ ትምህርቶችን ሳይማሩ ቀርተዋል፡፡ 677Manuscript Releases 12:9, 1898.CGAmh 335.1

    የቤት ውስጥ ግዴታዎችን በታማኝነት የመወጣት ሽልማቶች— የቤት ውስጥ ግዴታዎች በታማኝነት መፈጸም፣ በጣም ቀላል እና ተራ ቢሆንም እንኳ በጥሩ ሁኔታ መሸፈን የሚችሉትን ቦታ መሸፈን በእውነት የሚያስከብር ነው፡፡ ይህ መለኮታዊ ተጽዕኖ ያስፈልጋል። በዚህ ውስጥ ሰላምና ቅዱስ ደስታ አለ፡፡ የመፈወስ ኃይል አለው። የነፍስ ቁስሎች አልፎ ተርፎም የአካልን ሥቃይ በድብቅ እና ሳይታወቅ ያስታግሳል። ከንጹህ እና ከቅዱስ ዓላማዎች እና ድርጊቶች የሚመጣ የአእምሮ ሰላም ለሁሉም የሰውነት አካላት ነፃ እና ብርቱ ምንጭ ይሰጣል፡፡ በቀንበጥ ተክል ላይ እንደሚወርድ ጠል በውስጣችን ያለው ሰላምና በእግዚአብሔር ላይ ከበደል ነጻ የሆነ ሕሊና አእምሮን ያነቃቃል እንዲሁም ያበረታል፡፡ ከዚያ በኋላ ፈቃድ በትክክል የሚመራ እና ቁጥጥር ሥር የሚሆን እና ይበልጥ ቆራጥ ሲሆን ከጠማማነት ግን የፀዳ ነው። የተቀደሱ ከመሆናቸው የተነሳ የሚያሰላስሉት ነገር አስደሳቾች ናቸው፡፡ የሚኖራቸው የአእምሮ እርከታ ከእናንተ ጋር የሚገናኙትን ሁሉ ይባርካል ፡፡ CGAmh 335.2

    ይህ ሰላምና መረጋጋት ከጊዜ በኋላ ተፈጥሯዊ በመሆን ተመልሶ በእናንተ ላይ ለማንጸባረቅ በዙሪያችሁ ባሉት ሁሉ ላይ ውድ ጨረሮቹን ያንፀባርቃል። ይህንን ሰማያዊ የአእምሮ ሰላም እና ጸጥታን በቀመሳችሁ ቁጥር ይበልጥ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ ይህ ሕይወት ያለው፣ ሕያው ደስታ፣ ሥነ ምግባራዊ ኃይልን ሁሉ ወደ ፍዘት የሚጥል ሳይሆን ነገር ግን ለተጨማሪ እንቅስቃሴ የሚያነቃቃቸው ነው። ፍጹም ሰላም መላእክት ያላቸው የሰማይ ባሕርይ ነው። 678Testimonies For The Church 2:326, 327.CGAmh 335.3

    በሰማይ ውስጥ ሥራ ይኖራል— መላእክት ሠራተኞች ናቸው፤ እነርሱ ለሰው ልጆች የተሰየሙ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው፡፡ እነዚያ እንቅስቃሴ-አልባ የሆነ መንግስተ ሰማይን በጉጉት የሚጠባበቁ ሰነፍ አገልጋዮች ሰማይ ምን ማለት እንደሆነ የሐሰት አመለካከቶች አሏቸው፡፡ ፈጣሪ ለሰነፍ ኃጢአተኛ እርካታ ለመስጠት ሲል ምንም ሥፍራ አላዘጋጀም፡፡ ሰማይ የሚያስደስት የሥራ ቦታ ነው፤ ነገር ግን ለደከሙና ሸክም ለበዛባቸው፣ በጎውን የእምነት ገድል ለታገሉት የክብር ዕረፍት ይሆናል፤ ምክንያቱም የማይሞት ወጣትነት እና ጥንካሬ የእነርሱ ይሆናል፣ ከእንግዲህ ወዲህ ከኃጢአትና ከሰይጣን ጋር አይዋጉም። ለእነዚህ ብርቱ ሠራተኞች ዘላለማዊ ስንፍና አሰልቺ ይሆንባቸዋል፡፡ እርሱ ለእነርሱ ሰማይ አይሆንም፡፡ በምድር ላይ ለክርስቲያን የተሰጠው የልፋት መንገድ ከባድ እና አድካሚ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን በአዳኙ ዱካዎች የተከበረ ሆኗል፣ እናም ያንን ቅዱስ መንገድ የሚከተል ደህንነቱ የተረጋገጠ ነው። 679Christian Temperance and Bible Hygiene, 99.CGAmh 336.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents