Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ብቸኝነት ይሰማችኋል?

    እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፡፡
    ማቴ 28፡20

    እግዚአብሔር ከቶ አልተውህም፤
    በፍጹም አልጥልህም” ብሎአል፡፡
    ዕብ 13፡5

    ብቸኞች እንደሆንን ፈጽሞ ሊሰማን አይገባም፡፡ መላእክት አብረውን አሉ፡፡ ክርስቶስ በስሙ ሌልክልን ቃል የገባው አጽናኝ ከእኛ ጋር ይኖራል፡፡ ወደ እግዚአብሔር ከተማ በሚወስደው መንገድ ላይ ሲጓዙ፣ በእርሱ የሚታመኑት ማሽነፍ የማይችሏቸው አስቸጋሪ ነገሮች የሉም፡፡ ጌታ መፍትሔ ያላዘጋጀላቸው ሰቆቃዎች፣ ምሬቶች፣ ወይም ሰብአዊ ድክመቶች የሉም፡፡...እቃገ 26.1

    ሰብአዊ ተፈጥሮን የተላበሰው ኢየሱስ ለሰብአዊ ፍጥረት ስቃይ፣ መራራትን ያውቃል፡፡ ክርስቶስ እያንዳንዱን ነፍስና የዚያንም ነፍስ የተለየ ፍላጎትና መከራ ብቻ ሳይሆን የሚያውቀው፣ መንፈስን የሚያስጨንቅን ነገር በሙሉ ያውቃል፡፡ እጁም ለእያንዳንዱ በስቃይ ውስጥ ላላ ልጁ በርህራሄ ይዘረጋል፡፡ ክርስቶስ ሩቅ እንዳለ ሆኖ ፈጽሞ አይሰማችሁ፡፡ እርሱ ሁልጊዜ ቅርብ ነው፡፡ የፍቅር ሀልዎቱ (መገኘቱ) ዙሪያችሁን ይከባል፡፡እቃገ 26.2

    ኢየሱስ በወል ያውቀናል፤ በድካማችንም ልቡ ይነካል፡፡ ሁላችንንም በስም ያውቀናል፡፡ የምንኖርባትን ሴት ያውቃል፤ በዚያም ውስጥ ያሉትን ሰዎች በስም ያውቃቸዋል፡፡አገልጋዮቹንም ወደ ተወሰነ ከተማ፣ ወደ ተወሰነ ቤት በመሄድየእርሱን አንድ በግ እንዲያገኙ ይልካቸው ነበር፡፡እቃገ 26.3

    በማንኛውም ጊዜና በየትኛውም ቦታ፣ በማንኛውም ስቃይና መከራ፣ ነገሮች ሁሉ ሲጨላልሙና የወደፊቱ ሁኔታም በጭንቀት ሲሞላን፣ ከዚህም የተነሳ ረዳተ ቢስና ብቸኛች እንደሆንን ሲሰማን፣ በእምነት ወደ እርሱ ለምንጸልየው ጸሎት ምላሽ ይሆን ዘንድ አጽናኙ ይላክልናል፡፡እቃገ 27.1

    ሁኔታዎች ከምድራዊ ወዳጆቻችን ሌላዩን ይችላሉ፤ ነገር ግን ምንም አይነት ሁኔታ፣ የትኛውም አይነት የቦታ ርቀት ከሰማያዊው አጽናኝ ሊለየን አይችልም፡፡ የትም ብንሆን የት የትም ብንሄድ የት፣ ሊረዳን፣ ሊደግፈን፣ ሊሸከመንና ሊያስደስተን ሁልጊዜ በቀናችን ነው፡፡እቃገ 27.2

    ፈጽሞ ብቸኛች አይደለንም፡፡ ብንመርጠውም ባንመርጠውም እርሱ አብሮን አለ፡፡ የትኛውም ስፍራ ብንሆን ማንኛውንም ነገር ብናደርግ እግዚአብሔር በዚያ እንዳለ እናስታውስ፡፡ ከክርስቶስ ጋር ራሳቸውን ላስተዋወቁ ሁሉ፣ ምድር የብቸኝነት ስፍራእቃገ 27.3

    አትሆንባቸውም፡፡ ይልቁንም ወደ እርሷ መጥቶ በሰዎች መካከል ባደረው ጌታ የተሞላች የአባታቸው ቤት ትሆንላቸዋለች፡፡ እግዚአብሔር ከልብ ለሚያገለግሉት ችግሮችን ተጋፍጠው ያሽንፉ ዘንድ ብቻቸውን በፍልሚያ ውስጥ አይተዋቸውም፡፡ ነፍስ ከምታሰማው ሲቃ፣ ስቃይና ምሬት መካከል የሰማይ አባትን ልብ ሳይነካ የሚያልፍ አንድም የለም፡፡ ... እግዚአብሔር የጭቁኖችን ልቅሶ ለመስማት ከዙፋኑ ዘንበል ይላል፡፡ ለእያንዳንዱ እውነተኛ ጸሉት “እነሆኝ፤ እዚህ አላሁ” በማለት መልስ ይሰጣል፡፡ የተጨነቁትንና የተረገጡትን ያነሳል፤ በስቃያችን ሁሉ እርሱም ይሰቃያል፡፡ በእያንዳንዱ መከራና ፈተና ውስጥ የፊቱ መላእክ ሌታደገን በአጠገባችን ይገኛል፡፡እቃገ 27.4

    በህይወት ጎዳና የምንራመደው እያንዳንዱ እርምጃ ወደ ኢየሱስ ሌያስጠጋን፣ ፍቅሩን በጥልቀት እንድንለማመድ ሊረዳን፣ እንዲሁም ወደ ተባረከው የሰላም ቤታችንም አንድ እርምጃ ሊያቀርበን ይችላል፡፡እቃገ 28.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents