Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ሕመም ሲመጣ

    ኃጢአትሽን ሁሉ ይቅር የሚል፣
    ደም ሁሉ የሚፈውስ፤
    መዝ 103፡3

    “አንተን ግን መልሼ ጤነኛ አደርግሃለሁ፤ ቁስልህንም
    እፈውሳለሁ” ይላል እግዚአብሔር
    ኤር 30፡17

    ልክ ምድራዊ ወዳጅ ያደርግልናል ብለን ተማምነን ውለታ እንዲውልልን እንደምንጠይቅ፡ የነፍስን ፍላጎት ለእግዚአብሔር የምናሳውቅበት ከእውነተኛ ልብ የሚመነጭ ጸሎት ፣ የእምነት ጸሎት ነው፡፡ እግዚአብሔር ስርአታዊ የሆነውን የማወደሻ ቃል ለመስማት አይፈልግም፤ ይልቁንም በኃጢአተኝነት ስሜት ልቡ የተሰበረውንና ድካሙን ኣስተውሉ የአብን ምህረት ለማግኘት ቃላት የሌለውን ጩኸት በማሰማት የሚቀርበውን ነፍስ ሊገናኝ ይናፍቃል፡፡እቃገ 38.1

    ይፈወሱ ዘንድ እንዲጸለይላቸው የሚፈልጉ ሁሉ የእግዚአብሔርን ተፈጥሮአዊም ሆነ መንፈሳዊ ሕግ መተላለፍ ኃጢአት እንደሆነ ግልጽ ሊደረግላቸው ይገባል፤ እናም የእርሱን በረከት መቀበል ይችሉ ዘንድ በቅድሚያ ኃጢአታቸውን መናዘዝና መተው ያስፈልጋቸዋል፡፡እቃገ 38.2

    በጤና ያሉ ሰዎች በየዕለቱ፣ ከዓመት ወደ ዓመት ለእነርሱ የበዛውን ግሩም ምህረት ይዘነጋሉ፡፡ ለእግዚአብሔርም ምስጋና አይሰጡም፡፡ ነገር ግን በሽታ ሲመጣ፣ እግዚአብሔር ይታወሳል፡፡ የሰው ጉልበት ተሟጦ ሲያልቅ፣ ሰዎች የመለኮት እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ይሰማቸዋል፡፡ መሐሪው እግዚአብሔርም በእውነት ከእርሱ እርዳታ ከሚፈልጉት ፊቱን አያዞርም፡፡ እርሱ በጤና ጊዜ መጠጊያችን እንደሆነ ሁሉ በህመምም ጊዜ እንደዚያው ነው::እቃገ 38.3

    ለጸሎታችን ፈጣን ምላሽ እንዳላገኘን ቢሰማን፣ ተስፋ መቁረጥ እንዳያጠቃን እምነታችንን አጥብቀን መያዝ አለብን፡፡ ተስፋ መቁረጥ ከእግዚብሔር ጋር ይለየናል፡፡ በእግዚአብሔር ላይ ያለን መተማመን ትልቅ ሊሆን ይገባል፡፡ በጣም በፈለግነውም ጊዜ በረከቶቹ እንደ ዝናብ በእኛ ላይ ይወርዳሉ፡፡እቃገ 39.1

    ክርስቶስ በሰዎች መካከል በአካል በተመላለሰበት ጊዜ የተጠቀመበት ኃይል አሁንም ቢሆን በቃሉ አማካኝነት ከእኛ ጋር አለ፡፡ ኢየሱስ በሽታን የፈወሰው፣ አጋንንትንም ያስወጣው በቃሉ ነበር፡፡ ... በቃሉ ውስጥ የሰፈረው የተስፋ ቃል እንዲሁ ለእኛም ነው፡፡ በተስፋው ቃል በኩል በግላችን የእርሱን ድምጽ እንደምንሰማ ያህል እናስተውል፤ ክርስቶስ ጸጋውንና ኃይሉን ለእኛ የሚገልጸው በተስፋ ቃሉ በኩል ነው።እቃገ 39.2

    በህመም ጊዜ እና ልንወጣው የሚገባንን የስራ ድርሻ አስመልክቶ ጌታችን በሐዋሪያው ያዕቆብ በኩል ግልጽ የሆነ መመሪያ ሰጥቶናል። የሰው እገዛ በማይሳካበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ለህዝቡ ረዳት ይሆናል። “ከእናንተ መካከል የታመመ ሰው አለ? የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎችን ይጥራ፤ እነርሱም በጌታ ስም ዘይት ቀብተው ይጸልዩለት፡፡ በእምነት የቀረበ ጸሉት የታመመውን ሰው ይፈውሰዋል፡፡ ጌታም ያስነሳዋል፡፡”እቃገ 39.3

    አንዳንድ ጊዜ የጸሎት መልሶቻችን በፍጥነት ይመጡልናል፤ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ የምንፈልጋቸውን ነገሮች ለማግኘት በትእግስት መጠበቅና ልመናችንንም በትጋት መቀጠል ያስፈልገናል፡፡ ... ጌታን በተስፋ ለሚጠባበቁ፣ በቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ የሰፈሩ ክቡር ተስፋዎች አሉ፡፡ ሁላችንም ለጸሎታችን ፈጣን ምላሽ ለማግኘት እንመኛለን፤ ጸሉታችንም ወዲያው ካልተመለሰ ተስፋ ለመቁረጥ እንፈተናላን፡፡ ...መዘግየቱ ግን ለእኛ የተለየ ጥቅም ስላለው ነው፡፡እቃገ 40.1

    ለመጸለይ ድምጽና ጊዜ ካገኛችሁ፣ እግዚአብሔር ደግሞ ለመመለስ ድምጽና ጊዜ ያገኛል፡፡እቃገ 40.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents