Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  በሃሰት ተወንጅላችኋል?

  ወዳጆች ሆይ! ለእግዚአብሔር ቁጣ ፈንታ ስጡ እንጂ
  አትቀሉ! “በቀል የእኔ ነው! እኔ ብድራትን እመልሳለሁ’ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።
  ሮሜ 12፡19

  እግዚአብሔር ከዮሴፍ (በሐሰት ከተወነጀለው) ጋር ሆኖ
  ሥራውን ሁሉ ያሳካለት ስለ ነበር የወህኒ ቤት አዛዥ
  በዮሴፍ ኃላፊነት ስር ስላለው ስለማንኛውም
  ጉዳይ ሐሳብ አይገባውም ነበር፡፡
  ዘፍ 39፡23

  ምርጦቹን ለመዘረር የሚዘጋጁትን መሳሪያዎች ሁሉ ለማምከን እግዚአብሔር ይችላል፡፡ የሰዎች ርኀራሄ የጎደላቸው ንግግሮች እንዲጎዷችሁ አትፍቀዱላቸው፡፡ ስለ ኢየሱስ ሰዎች ክፉ ከመናገር ተመልሰዋልን? እናንተ ግን ልትሳሳቱና ሰዎችም ክፉ ሊያወሩባችሁ የሚችሉበትን አጋጣሚ ልትፈጥሩላቸው ትችላላችሁ፤ ነገር ግን ኢየሱስ ፈጽሞ ስህተትን አልሰራም፡፡ እርሱ ንጹህ፣ እንከን የለሽ፣ ሰአንዳች ያልረከሰ ነበር፡፡ ... የቤተክርስቲያናችሁ አባላትም እንኳን ሳይቀሩ ልባችሁን የሚያሳዝን ነገር ሊናገሩና ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ሰተረጋጋ መንፈስ ሰኢየሱስ በመታመንና በእግዚአብሔር ውድ ልጅ ደም የተገዛችሁ የክርስቶስ ንብረት እንጂ የራሳችሁ እንዳልሆናችሁ ለማስታወስ፣ እንዲሁም ሰብአዊ ፍጥረትን ለመባረክ በእርሱ ስራ እንደተሰማራችሁ በማሰብ ወደ ፊት ቀጥሉ፡፡እቃገ 48.1

  በሃሰት መወንጀላችን ስማችንን ጭቃ ሊቀባ ቢችልም፣ ባህሪያችንን ግን አያበላሽም፡፡ ያ በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ የሚገኝ ጉዳይ ነው፡፡ ከኃጢአት ጋር እካልተስማማን ድረስ፣ ነፍሳችንን ሊያሳድፍ የሚችል ሰብአዊም ሆነ ሰይጣናዊ ኃይል የለም፡፡ እግዚአብሔርን የምትተማመን ነፍስ የእግዚአብሔር ሞገስና ብርሃን በደመቀበት በብልጽግና ወራት እንደምትሆነው በጣም በስቃይ በተሞላና ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥም እንደዚያው ትቀጥላላች፡፡እቃገ 49.1

  ክርስቶስ ህይወቱን ምሳሌ ይሆነን ዘንድ ሰጥቶናል፡፡እያንዳንዱን ጉሸማ እውነተኛም ይሁን ሃሳባዊ- ለመበቀልበምናደርገው ጥረት እርሱ አይከብርም፡፡ ስምን ለማስጠበቅ ስለ ራስ ማስተባበያን ለመስጠት ሁልጊዜ መዘጋጀት የታላቅ አእምሮ መገለጫ አይደለም፡፡ በበቀል መንፈስ ወይም ሰንዴት አንድን ነፍስ ከመጉዳት፣ አንድ መቶ ጊዜ ያለ ጥፋታችን ብንሰቃይ ይመረጣል፡፡ ከእግዚአብሔር ልንቀሰላው የሚገባን ብርታት አለ፡፡እርሱ ሊረዳን ይችላል፡፡ ጸጋና ሰማያዊ ጥሰብን ሊሰጠን ይችላል፡፡በእምነት ከጠየቃችሁ፣ ትቀበላላችሁ፤ ነገር ግን ተግታችሁ ጸልዩ።እቃገ 49.2

  በደል ሲደርስባችሁ ወይም በስህተት ብትወነጀሉ በቁጣ መልስ ከመስጠት ይልቅ፣ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ለራሳችሁ ድገሙ።እቃገ 49.3

  ኢየሱስ ከነብዙ ስህተታቸው የተሽከማቸው ሰዎች፣ በሌሎች ደረሰብን ለሚሉት እውነተኛም ይሁን ሃሳባዊ ጥቃት ቅር ሊሰኙ አይገባም፡፡ ስለ እነርሱ የሌሎች የልብ ሃሳብ ምን እንደሆነ ለማወቅ ሁል ጊዜ ፍለጋ ውስጥ ያሉ ሰዎች አሉ። እነርሱን ለማበሳጨት ተብሎ ባልተነገረ ቃላት ሁሉ ውስጥ ክፋትን ይመለከታሉ፡፡ ይህም የሰይጣን አሰራር ነው።እቃገ 49.4

  የሃሰት ዜናዎች ስለ እኛ ሊሰራጩ እንደሚችሉ ልንጠባበቅ ይገባል። ነገር ግን ትክክለኛውን መንገድ የምንከተል ከሆነ፣ ወሬዎቹን ቸል ብንላቸው፣ ሌሎችም ችል ይሏቸዋል፡፡ የስማችንን ነገር ለእግዚአብሔር አደራ እንስጠው፡፡ ... የሐሜት እሳት በእኛ የአኗኗር ሁኔታ ሊከስም ይችላል፡፡ በንዴት ቃላት ግን ሊጠፋ አይችልም፡፡ ዋናው ጭንቀታችን እግዚአብሔርን በመፍራት መኖርና የሚነዙብንም የሃሰት ወሬዎች ውሸት እንደሆኑ በተግባራችን ማሳየት ይሁን፡፡ ባህሪያችንን ከእኛ ይልቅ ሊያበላሽ የሚችል ማንም የለም፡፡እቃገ 50.1

  በዓለም እስካለን ድረስ ክፉ ተጽእኖን መጋፈጣችን አይቀሬ ነው፡፡ ትዕግስታችንን የሚፈታተን ነገር ይገጥመናል፡፡ የመንፈስ ፍሬዎችን በህይወታችን ማሳደግ የምንችለውም እነዚህን ፈተናዎች በትክክለኛው መንገድ መጋፈጥ ስንችል ነው፡፡ ክርስቶስ በእኛ ውስጥ ከኖረ፣ በሚያበሳጩና በሚያናድዱ ነገሮች መካከል ታጋሾች፣ ሩህሩሆች፣ ደስተኛች መሆን እንችላለን፡፡እቃገ 50.2

  ሻካራና ያልታረሙ ቃላትን ለሚሰነዝርባችሁ ሰው ልትሰጡት የምትችሉት ጠንካራ ተግሳጽ ዝምታ ነው፡፡ ፍጹም በዝምታ እላፉት፡፡ ብዙ ጊዜ ዝምታ አንደበተ ርቱዕነት ነው፡፡እቃገ 50.3

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents