Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  የሞት ጥላ ሲያጠላባችሁ

  በሞት ጥላ ሽለቆ ውስጥ ብሄድ እንኳ፣
  አንተ ከእኔ ጋር ስለሆንህ ክፉን አልፈራም፤
  መዝ 23፡4

  በአንዲት ሳንቲም ከሚሰጡት ሁለት ድንቢጦች አንዳቱ
  እንኳ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር አትወድቅም፡፡ የራስ
  ጠጉራችሁ እንኳ አንድ ሳይቀር የተቆጠረ ነው፤ ስለዚህ
  አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች ይልቅ ዋጋችሁ የከበረ ነው፡፡
  ማቴ 10፡2931

  የክርስቶስ ሰላም ወደ ነፍሳችሁ ይምጣ፡፡ እርሱ ለተስፋው ቃል የታመነ ነውና እናንተም በእርሱ ላይ ባላችሁ እምነት ታማኞች ሁኑ፡፡ ደካማና በፍርሃት የሚንቀጠቀጥ እጃችሁን በእርሱ ጠንካራ እጅ ውስጥ አስገቡ፡፡ እርሱም ይያዛችሁ፤ ያጠንክራችሁ፤ በደስታና በመጽናናት ይሙላችሁ፡፡እቃገ 41.1

  እግዚአብሔር ምንም ረብ በሌላው ሰቆቃ፣ ምሬትና የተስበረ ልብ እንድንጨፈለቅ አይፈቅድም፡፡ ወደ እርሱ ቀና ብለን የተወደደ የፍቅር ፊቱን እንድናይ ይፈልጋል፡፡ ዓይናችን በእንባ ከመሽፈኑ የተነሳ፣ እርሱን ማየት ቢያቅተንም የተባረከው አዳኝ ግን ከብዙዎቻችን ኣጠገብ ቆሞአል፡፡ እጃችንን በመያዝ፣ እንዲመራን በመፍቀድ በእምነት እርሱን እንድናየው ይናፍቃል፡፡ ልቡ ለሃዘናችንና ለመከራችን ክፍት ነው፡፡ ... ነፍስን ከየዕለቱ ሰቆቃና ጭንቀት ከፍ በማድረግ ወደ ሰላሙ ቀጠና ያወጣታል። እቃገ 41.2

  በተዋረደ ልብ መለኮታዊ ምሪትን በማንኛውም መከራና ጭንቀት ውስጥ የምንፈልግ ከሆነ፣ በጸጋ የተሞላ መልስ እንደሚሰጠን በቃሉ ተረጋግጦልናል፡፡ እቃገ 42.1

  ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ በተዋጡ ቀናት ውስጥ ስታልፉ አትፍሩ፡፡ በእግዚአብሔር ላይ እምነት ይኑራችሁ፡፡ እርሱ የሚያስፈልጋችሁን ያውቃል፡፡ ኃይል ሁሉ የእርሱ ነው፡፡ ወሰን የለሽ ፍቅሩና ርህራሄው አይቀዘቅዝም፡፡ የተስፋ ቃሉን ላይፈጽም ይችላል በማለት አትስጉ፡፡ እርሱ ዘላለማዊ እውነት ነው፡፡ ከሚወዱት ጋር የገባውን ኪዳን አይለውጥም፡፡ ለታማኝ አገልጋዮቹም የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ የሚያገኙበትን ብቃት ይሰጣል፡፡እቃገ 42.2

  በችግር ውስጥ ሲወድቁ ብዙዎች ለምድራዊ ወዳጆቻቸው ጭንቀታቸውን በመግለጽ የእርዳታ እጅ ይዘረጋላቸው ዘንድ ልመናቸውን ያቀርባሉ፡፡ ፈታኝ የሆኑ ሁኔታዎችም ሲገጥሙዋቸው ልባቸው ባለማመን ይሞላል! መንገዱም ይጨልምባቸዋል፡፡ በሁሉም ጊዜ ግን የዘመናት መካር የሆነው ሃያል ጌታ ከእነርሱ ጎን ነው! በእርሱም ላይ መተማመናቸውን እንዲያደርጉ ይጋብዛቸዋል፡፡ ኢየሱስ ታላቱ ተሸካሚያችን እንዲህ ይላናል፡፡ “ወደ እኔ ኑ! ... እኔም አሳርፋችኋለሁ፡፡” ታዲያ ፊታችንን ከእርሱ መልሰ7 ሰማያስተማምነት፣ እነርሱ ራሳቸው እንደ እኛ በእግዚአብሔር ላይ መደገፍ በሚያስፈልጋቸው ሰብአዊ ፍጡራን ላይ አንታመን?እቃገ 42.3

  ብዙ ጊዜ ታላላቅ መከራ የተሸከሙ ሰዎች በየሄዱበት የተስፋን ብርሃን በመፈንጠቅ ላሌሎች ታላቅ መጽናናት የሚያመጡ ናቸው፡፡ እንዲህ ያሉት ሰዎች በመከራቸው የታረሙና የጣፈጡ ሲሆኑ፣ መከራ ሲመጣባቸው በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን መታመን አይጥሉም፤ ይልቁንም ወደ ጠባቂ ፍቅሩ የሰለጠ ይጠጋሉ፡፡ የእግዚአብሔር በገርነት የተሞላ እንክብካቤ ጨለማውንና ብርሃኑን ሰማፈራረቅ ለበጎ ዓላማው ገጣሚ እንደሚያደርገን እነዚህ ሰዎች ምስክር ናቸው፡፡ እቃገ 42.4

  ሞትን አሸንፎ የተነሳ ህያው አዳኝ አለን፡፡ ... ሕይወት ሰጪውም በቅርብ ይመለሳል፡፡ ... ምርኮኞችን ነጻ በማውጣት “እኔ ትንሳኤና ሕይወት ነኝ በማለት ያውጃል፡፡ የትንሳኤው ጌታ ወደ ቤታችን ሊያስገባን ቆሞ ይጠብቀናል፡፡ በመጨረሻ ወደ ቅዱሳን አዕምሮ የሚመጣው ሃሳብ ሞትና ስቃዩ ነው፡፡ ... ይሁን እንጂ እንዲህ የሚል አዋጅ ይከተላል! “ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ? ሲኦል ሆይ ድል መንሳትህ የት አለ?” ... ቅዱሳን የማይሞተውን ይለብሳሉ! ጌታንም ለመገናኘት ሰአየር ይነጠቃሉ፡፡ የእግዚአብሔር ከተማ ደጆች ሰፈታቸው ይከፈታሉ፡፡ በአውነት ላይ የጸኑት ህዝቦችም በደጁ አልፈው ይገባሉ፡፡እቃገ 43.1

  እያንዳንዱ ጸሎታችሁ በጸጋው ዙፋን ፊት እንደቀረበና የተስፋው ቃል አስተማማኝ በሆነው አምላክ ምላሽ እንደተሰጠው በመቁጠር ጉዞአችሁን ወደ ፊት ቀጥሉ፡፡ በሃዘንና በሽክም ጫና በዛላችሁ ጊዜም ሲሆን፤ ለእግዚአብሔር ሰልባችሁ ሰመንት እየዘመራችሁ ወደ ፊት ገስግሱ፡፡ ... ብርሃን ይገለጥልናል! ደስታም በልባችን ይሞላል! ደመናውና ጭጋጉም ሁሉ ይገፈፋል፡፡ እቃገ 43.2

  በጣም ተስፋ ያደረግንባቸው ነገሮች ሌንሸራተቱ ይችላሉ! የምንወዳቸውን ሰዎች ሞት ሊነጥቀን ይችላል፡፡ ነገር ግን አስከ ዘላላም አልተለያየንም! ሰኢየሱስ ሆነው ያንቀላፉትን እንደገና ልናገኛቸው ተስፋ አለን፡፡ ከጠላት ምድር ይነሳሉ፡፡ ህይወት ሰጪው በቅርብ እየመጣ ነው፡፡ በመንገዱም እልፍ አእላፍ መላእክት ያጅቡታል፡፡ የሞትን ማሰሪያ ይሰጣጥሳል! የመቃብሩን መዝጊያ ይቆርጣል! ውድ የሆኑት የሞት ምርኮኞችም በፍጹም ጤንነት የማይሞትን ውሰት ተላብሰው ይነሳሉ፡፡እቃገ 43.3

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents