Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ወዳጆቻችሁ ቢከዷችሁ

    አባቴና እናቴ ቢተውኝ እንኳ’ እግዚአብሔር ይቀበለኛል፡፡
    መዝ 27፡10

    ከወንድም አብልጦ የሚቀርብ ጓደኛም አለ፡፡
    ምሳ 18፡24

    ምድራዊ ዘመዶቻችሁ ወደ እናንተ ከሚጠጉት በላይ እግዚአብሔር ወደ እናንተ የተጠጋና የተወደደ ነው፡፡እርሱም ወዳጃችሁ ይሆናል፤ ፈጽሞም አይተዋችሁም፡ የእርሱም ወዳጅነት የሚጣፍጥ ሰላም ይዞላችሁ ይመጣል፡፡እቃገ 51.1

    ከስቃይ ሁሉ የከፋው ስቃይ በቤት ውስጥ በሚነሳ ችግርየሚደርስ ስቃይ ነው፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ እንዲህ ይላል፤ “እናቱንወይም አባቱን ከእኔ አስበልጦ የሚወድ የእኔ ሊሆን አይገባም፡፡በስውር እየተሰቃዩ ያሉ ብዙ ህያው ሰማዕቶች አሉ፡፡ እነርሱም በምላስ ዱላ እየተገረፉ፣ በከባድ ተቃውሞ እየቆሰሉ የሚገኙ ሲሆኑ ዕጣፈንታቸውም መኖርና መሰቃየት ብቻ ይመስላል፡፡ሆኖም ግን የኃይላቸው ምንጭ ከሆነው ከኢየሱስ ብቻ መጽናናትን ይቀበላሉ፡፡ እንዲህ ያሉት ነፍሳት ሚሲዮናዊያን ናቸው፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ የተከበሩ ሲሆኑ በሰጉ የሕይወት መጽሐፍ ላይ ስማቸው ሰፍሮአል፡፡እቃገ 51.2

    በአንድ ቅጽበት፣ በጥድፊያና በስሜት ውስጥ ሆነን በምንሰነዝረው ግድየለሽ ቃል፣ ሰዕድሜ ዘመናችን ሁሉ ንስሓ ብንገባ የማንለውጠውን ክፋት ልንፈጽም እንችላለን፡፡ እርዳታና ፈውስ የሚያመጡ ቃላትን ከመሰንዘር ፈንታ በሻከሩና በችኮላ በተነገሩት ቃላት ልባቸው የተሰበረና ህይወታቸው የተመሰቃቀለ ስንቶች ናቸው!እቃገ 51.3

    ለማይገባቸው ሰዎች የተነገረ መልካምና ሩህሩህ ቃል የሚያሳድረውን ተጽዕኖ እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ማስተዋል አንችልም፡፡ ምስጋና ቢስ የሆነና ኃላፊነቱን ያልተወጣ ሰው ሲያጋጥመን ቁጣችንንና ንዴታችንን ለማሳየት ውስጣችን ይነሳሳል፡፡ ይህንን ግን ጥፋተኛውም ሰው ቢሆን ይጠባበቀዋል፡፡ለዚያም ተዘጋጅቶአል፡፡ ነገር ግን በርህራሄ የሚደረግለት መስተንግዶ ያስደንቀዋል፡፡ ለመልካም ህይወትም ያነሳሳዋል፡፡እቃገ 52.1

    በምህረቱና በታማኝነቱ እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ እምነታችንን የጣልንባቸውን ሰዎች እንዲክዱን ይፈቅዳል፡፡ ይህንንም የሚያደርገው ሰሰው የመታመንን ሞኝነት እንድናስተውል ነው፡፡ሙሉ በሙሉ፣ ራሳችሁን በማዋረድና፣ ያለ አንዳች ራስ ወዳድነት በእግዚአብሔር ታመኑ፡፡እቃገ 52.2

    ሰማይ ለሰው ከሚሰጣቸው ስጦታዎች መካከል ከክርስቶስ ጋር በስቃዩ እንደመካፈል ያለ ትልቅ ክብደት ያለውና ከፍተኛ ክብር ያለበት ስጦታ የለም፡፡እቃገ 52.3

    ኢየሱስ ሁሉን እንደሚያውቀው አስታውሱ፤ እያንዳንዱን ሰቆቃና ሃዘናችሁን እርሱ ያስተውለዋል፡፡ ክንዶቹ ከእናንተ በታች ናቸውና ትሰጥሙ ዘንድ አይተዋችሁም፡፡ በእርግጥም ታጋሽና ሩህሩህ ብትሆኑ ለባልንጀሮቻችሁ ብርሃንን መፈንጠቅ ትችላላችሁ።እቃገ 52.4

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents