Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 2 - ኢየሱስ ለኃጢያተኛው ስስማስፈስጉ

    ሰው በመጀመሪያ ከፍ ያለ ማዕረግና ችሎታ እንዲሁም ሚዛኑን የጠበቀ አስተሳሰባዊ ዉበት ነበረው፡፡ ሰው በፍጡርነቱም ሆነ ከእግዚአብሔር ጋር በነበረው ኅብረት ፍጹም ነበር፡፡ አስተሳሰቡ በንጽህና የተሞላ ዓላማውም ቅዱስ ነበር፡፡ ሆኖም በአለመታዘዝ ጠንቅ የነበረውን ችሎታ አጣ፣ እራስ ወዳድነት በፍቅር ቦታ ተተካ፡፡ ሰብዓዊው ተፈጥሮ የተሰጠውን ትእዛዝ በመተላለፉ ደካማ ሆነ፡፡ ይህን ተከትሎም በራሱ ብርታትና ጥንካሬ ክፉውን መቋቋም የማይችል ሆነ፡፡ ሰው በሰይጣን ግዞት ስር ወደቀ፡፡ እግዚአብሔር በተለየ መልኩ ጣልቃ ባይገባ ኖሮ ለዘላለም በዚህ ሁኔታ በቀጠለ ነበር፡፡ፈጣሪ ለሰዎች የነበረውን መለኮታዊ ዕቅድ ማሰናከል፣ ምድርን በሥቃይና መከራ መሙላት የፈታኙ ዓላማ ነበር፡፡ ይህ ሥቃይና መከራ እግዚአብሔር ሰው መፍጠሩን ተከትሎ የመጣ ውጤት እንደሆነም አድርጎ ያቀርባል፡፡ክየመ 15.1

    ሰው በኃጢአት ከመውደቁ አስቀድሞ «የተሰወረ የጥበብና የዕውቀት ሐብት ሁሉ በእርሱ ዘንድ…» (ቆላ. 2፡3) ከሆነው ከአምላኩ ጋር በደስታ የተሞላ ግንኙነት ነበረው፡፡ ነገር ግን ኃጢአት ከሠራ በኋላ በቅድስናው ያገኝ የነበረውን ደስታ አጣ፤ ይህን ተከትሎም ከእግዚአብሔር ፊት መደበቅ ፍላጎቱ ሆነ፡፡ ይህ ሁናቴ ዛሬም ዳግም ባልተወለደ ልብ ውስጥ ይስተዋላል፡፡እንዲህ ዓይነቱ ልብ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ስለሌለው ከእርሱ ጋር አንድነት በመፍጠር ደስታ አያገኝም፡፡ኃጢአተኛው እግዚአብሔር ባለበት ቦታ በመገኘቱ አይደሰትም፤ ከቅዱሳን ጋር ሕብረት ከማድረግ ይሸሻል፡፡ ይህ ሰው ሰማይ እንዲገባ ቢፈቀድለት እንኳ ሰማይ አስደሳች ስፍራ ሊሆንለት አይችልም፡፡ ከክርስቶስ ጋር በሰማይ የሚነግሠው እያንዳንዱ እራስ ወዳድነት ያልተጠናወተው አፍቃሪ ልብ ፍጹም ከሆነው አምላክ ጋር ልብ ለልብ የተሳሰረ አንድነት ሲፈጥር፣ ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት የሌላት ልብ ግን ከፈጣሪዋ ጋር የሚያገናኛት መስመር በመበጠሱ ምላሽ መስጠትም ሆነ መቀበል አትችልም:: የግለሰቡ አስተሳሰብም ሆነ ፍላጎት በዚያ ስፍራ ከሚኖሩ ጻድቃን ጋር የሚጻረር ይሆናል፡፡ ግሩም ጣዕም በተላበሰው በሰማያዊው ዜማ መሃል እርሱ ግን ምላሽ የማይሰጥ የተበጠሰ የሙዚቃ ክር ይሆናል፡፡ ለእንዲህ ያለው ሰው ሰማይ የሥቃይ ስፍራ ይሆንበታል፡፡ለአዲሲቱ ኢየሩሳሌም እንደ ጸሐይ ከሚያበራላትና የደስታዋ ማዕከል ከሆነው ጌታ ለመደበቅ ይናፍቃል፡፡ የኃጢአተኛው ከሰማይ መቅረት በእግዚአብሔር በኩል ያለ በቂ ምክንያት በችኮላ የታወጀ ውሳኔ አይደለም፡፡ነገር ግን መጀመሪያውኑ ግለሰቡ ራሱ ከዚህ አምላክ ጋር ወዳጅነት ለመመስረት ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ አምላካዊው ክብር ለእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች እንደሚፋጅ እሳት ነው:: እነርሱን ለማዳን ሲል የሞተውን ጌታ ፊት ላለማየት ሲሉ መደበቅን በመምረጥ ጥፋት በላያቸው ላይ እንዲመጣ ይመኛሉ፡፡ክየመ 15.2

    ከሰመጥንበት የኃጢያት አረንቋ በራሳችን አምልጠን በመውጣት አንችልም።

    ከሰመጥንበት የኃጢአት አረንቋ በራሳችን አምልጠን መውጣት አንችልም፡ልባችን በክፋት ተሞልቶአል ልንለውጠውም አንችልም።ለመሆኑ «ከርኩስ ነገር ውስጥ ንጹህን ማን ሊያወጣ ይችላል? አንድ እንኳ የሚችል የለም!» (ኢዮ. 14፡4)። «ለኃጢአት የተገዛ አእምሮ ከእግዚአብሔር ጋር ጠበኛ ነው» (ሮሜ 8፡1)፡፡ ትምህርት፣ ባህል፣መልካም ውሳኔ መወሰን ፣ የአእምሮን አቅም አሟጦ መጠቀም፣ እንዲሁም ሰብዓዊው ጥረት እኚህ ሁሉ የራሳቸው አግባብና ጠቀሜታ ያላቸው ቢሆኑም ነገር ግን እዚህ ላይ አቅመቢስ ሆነው እናገኛቸዋለን። እነዚህ ነገሮች ምናልባት የታረመ ውጫዊ ባህሪ ማፍራት ቢችሉም ልብን መቀየር ግን አይሆንላቸውም ፤ የህይወትን ምንጮች ሊያነጹ አይችሉም። ሰዎች ከኃጢአተኝነት ወደ ቅድስና ከመለወጣቸው አስቀድሞ፣አዲስ ህይወት ሊሰጣቸው የሚችል ከላይ የተላከ ኃይል በውስጣቸው ሊሠራ የግድ ነው:: ያ ኃይል ደግሞ ክርስቶስ ነው:: የእርሱ ጸጋ ብቻውን ለደረቀችው ነፍስ የለመለመ ህይወት በመስጠት በቅድስና ወደ እግዚአብሔር ሊስባት ይችላል፡፡ክየመ 16.1

    ማንም ከላይ «ካልተወለደ»፣ አዲስ ልብ፣ አዲስ መሻት፣ አዲስ ዓላማ ወይም አዲስ ተነሳሽነት ካልተቀበለ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም» ዮሐ 3:3) በማለት አዳኙ ተናግሮአል፡፡ «ሰው በተፈጥሮው የተላበሰውን መልካም ነገር ማጎልበት ብቻውን በቂ ነው» የሚለው ጽንሰ ሃሳብ ለሞት የሚያደርስ ማታለያ መንገድ ነው፡፡ «መንፈሳዊ ያልሆነ ሰው ከእግዚአብሔር መንፈስ የሆነውን ነገር ሊቀበል አይችልም፤ ምክንያቱም እንዲህ ያለው ነገር ለእርሱ ሞኝነት ነው፤ በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊረዳው አይችልም» (1ኛ ቆሮ. 2:14)፡፡ «ዳግመኛ መወለድ አለባችሁ ስላልሁህ አትገረም» ዮሐ. 3:7)፡፡ ስለ ክርስቶስ እንደሚከተለው ተጽፎአል (ህይወት በእርሱ ነበረች ፤ ይህች ህይወት የሰው ብርሃን ነበረች» (ዮሐ. 1፡4)፡፡ «እንድንበት ዘንድ ለሰዎች ከሰማይ በታች የለምና» (ሐዋ. 4፡12)፡፡ክየመ 17.1

    የእግዚአብሔርን አፍቃሪነትና ደግነቱን፣ ርኅራኄውንና አባታዊ ጥንቃቄውን መገንዘብ ብቻውን በቂ አይደለም፡፡ እንዲሁም በዘላለማዊው የፍቅር መርኅ ላይ የተመሰረተውን አምላካዊውን ጥበብና የሕጉን ፍትሐዊነት መረዳት ብቻውን የትም አያደርስም:: ሐዋርያው ጳውሎስ ይህንን በማወቁ ነበር እንዲህ የተናገረው፡- «ሕጉ በጎ እንደሆነ እመሰክራለሁ» «ስለዚህ ሕጉ በራሱ ቅዱስ ነው፤ ትእዛዙም ቅዱስ፣ ጻድቅና መልካም ነው» (ሮሜ 7፡12)፡፡ ሐዋርያው ነፍሱን ዘልቆ ይሰማው ከነበረ ታላቅ ሥቃይና ተስፋ መቁረጥ በመነሳት «እኔ ግን ለኃጢአት እንደ ባሪያ የተሸጥኩ ሥጋዊ ነኝ» (ሮሜ 7፡14) በማለት ጨምሮ ይናገራል፡፡ ሐዋርያው ሊደርስበት ያልቻ ለውን ንጽህናና ጽድቅ በመናፈቅ «እኔ ምን ዓይነት ጎስቋላ ሰው ነኝ! ከዚህ ለሞት ከሰተጠ ሰውነት ማን ሊያድነኝ ይችላል? » (ሮሜ 7:24) በማለት ሲጮኽ ይደመጣል፡፡ እንዲህ ያለው ለቅሶ በዘመናት ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ኃጢአት ከተጫናቸው ልቦች ወደ ሰማይ ሲተም ኖሮአል፡፡ ለእነዚህ ወገኖች መልሱ አንድ ሲሆን ይኸውም «እነሆ! የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ» ዮሐ. 1:29) የተሰኘ ነው።ክየመ 17.2

    የእግዚአብሔር መንፈስ በተለያዩ ብዙ ምሳሌዎች ይህን እውነት ግልጽ ሲያደርግ እንመለከታለን፡፡ ይህን የሚያደርግበት ምክንያትም ከኃጢአት የጸጸት ሸክም ነጻ ለመሆን ለሚናፍቁ ነፍሳት የእግዚአብሔርን ዓላማ ግልጽ ለማድረግ ነው፡፡ ኤሳውን የማታለል ኃጢአት ከፈጸመ በኋላ ያዕቆብ ከአባቱ ቤት ሲኮበልል የጸጸት ስሜት አደቀቀው። በብቸኝነት የተዋጠውና ነቀፌታየደረሰበት ያዕቆብ ከደከመባቸውና መላ ህይወቱን የከበረ አድርገውለት ከነበሩ ነገሮች ተለየ፡ነገር ግን ከሁሉ በላይ ነፍሱን የተጫነው ነገር ቢኖር ሰማይ እንዳይተወውና ኃጢአቱ ከእግዚአብሔር እንዳይለየው ያደረበት ስጋት ነበር፡፡ፀሐይዋ ስትጠልቅ ዙሪያውን በኮረብቶች የተከበበውና ልቡ በሐዘን የተሞላው ያዕቆብ፤ በብሩህ ከዋክብት በደመቀው ሰማይ ስር እንቅልፍ ወሰደው:: እንግዳ ብርሃን በሕልሙ ያየው ያዕቆብ እርሱ ተኝቶ ከነበረበት ስፍራ አንስቶ ጫፉ ሰማይ ደጃፍ የሚደርስ በረጅሙ የተዘረጋ መሰላል አየ፡፡በዚህ መሰላል ላይ የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡና ይወርዱ ነበር፡፡ ይህ ሰማያዊ ክብር እየተገለጸ እያለ፤ ማጽናኛና ተስፋ የያዘ መለኮታዊ ድምፅ ተሰማ፡፡ በዚህም አዳኙን ነፍሱ አጥብቃ ለናፈቀችው ለያዕቆብ ሁሉም ነገር ግልጽ ሆነለት፡፡ ያዕቆብ ኃጢአተኛም ቢሆን ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት እንዲኖረው የሚያስችለው ሰማያዊ መንገድ ተገልጾለት በደስታና በምስጋና ተመለከተ፡፡ ያዕቆብ በሕልሙ የተመለከተው ምስጢራዊ መሰላል ሰውንና እግዚአብሔርን በብቸኝነት የሚያገናኘውን ኢየሱስን የሚወክል ነበር፡፡ክየመ 18.1

    ይህ የመሰላል ተምሳሌት ክርስቶስ ከናትናኤል ጋር ካደረገው ንግግር ጋር ተመሳሳይ ነው «ሰማይ ተከፍቶ የእግዚአብሔርም መላእክት በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ» (ዮሐ. 1:51)። ሰው በአምላኩ ላይ ክህደት በመፈጸም እራሱን ከእግዚአብሔር ነጠለ፤ ይህን ተከትሎም ምድር ከሰማይ ተለያየች። በሰማይና በምድር መሃል ግዙፍ ሸለቆ ቢከሰትም ነገር ግን በክርስቶስ አማካኝነት ምድር ዳግመኛ ከሰማይ ጋር ተገናኘች፡፡ ኃጢአት የፈጠረውን ሸለቆ ክርስቶስ አገናኘው። አገልጋዮች መላእክትም ከሰዎች ጋር ዳግመኛ ግንኙነት ሊኖራቸው ቻለ፡፡ ደካማና ረዳተቢስ የሆነውንና በኃጢአት የወደቀውን ሰው ክርስቶስ ከዘላለማዊው የኃይል ምንጭ ጋር አገናኘው::ክየመ 18.2

    በምድር ያሉትን ልጆቹን እግዚአብሔር የሚወድበት ፍቅር ከሞት የበረታ ፍቅር ነው።ክየመ 19.1

    ሰዎች በኃጢአት ለወደቀው ሰብዓዊ ዘር ብቸኛ የተስፋና የእርዳታ ምንጭ የሆነውን ችላ ብለው ለማምጣት የሚያልሙት ዕድገትም ሆነ የሰብዓዊውን ፍጡር ባህርይ ለማሻሻል የሚደረገው ጥረት ሁሉ ከንቱ ነው፡፡ «በጎ ስጦታና ፍጹም በረከት ሁሉ» (ያዕ. 1:17) ከእግዚአብሔር ናቸው፡፡ከእርሱ ውጪ ማንም በእውነት የከበረን ባህሪ ማግኘት አይችልም፡፡ወደእግዚአብሔር ለመድረስ የምንችልበት ብቸኛው መንገድ ደግሞ ክርስቶስ ነው። «መንገዱ እኔው ነኝ፤ እውነትና ህይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም» በማለት ስለ እራሱ ይናገራል (ዮሐ. 14፡6)።ክየመ 19.2

    በምድር ያሉትን ልጆቹን እግዚአብሔር የሚወድበት ፍቅር ከሞት የበረታ ፍቅር ነው። ልጁን ለእኛ መስዋእት እንዲሆን በመስጠት መላውን ሰማይ በአንድ ስጦታ አጠቃልሎ ሰጥቶናል፡፡ የአዳኙ ህይወት፣ ሞት ትንሳኤና አማላጅነት፣ እንዲሁም የመላእክት አገልግሎት፣ የመንፈስ ቅዱስ ተማጽኖ፣ አብ ከላይ ሆኖ መሥራቱ እነዚህ ሁሉ የማያቋርጡ ሰማያዊ ጥረቶች በኃጢአት ለወደቀው ለሰው ልጅ ደኅንነት በኣንድነት የሚሠሩ ናቸው።ክየመ 19.3

    ለእኛ ሲል ስለ ተከፈለው አስደናቂ መስዋዕት ዘወትር እናስብ! ሰማይ የጠፉትን ዳግም የራሱ ለማድረግና መኖሪያቸው እንደገና በአብ ዘንድ እንዲሆን የሚሠራውን የማያቋርጥ ሥራና የሚያፈሰውን ጉልበት በመመልከት አድናቆታችንን ለመግለጽ እንጣር፡፡ ከዚህ የሚበልጥ ኀይል የትም አይገኝም፤ የሚጠብቀን ሽልማት፣ በሰማይ ያለው ደስታ ከመላእክት ጋር የሚኖረን ህብረት፣ የእግዚአብሔር አብና የልጁ የፍቅር ህብረት፣ ለዘላለም ለሚዘልቅ ነገር ጉልበታችንን ማፍሰስ መቻል፣ እነዚህ ሁሉ ከልባዊ ፍቅር የሚመነጨውን አገልግሎታችንን ለፈጣሪያችንና ለአዳኛችን እንድንሰጥ ግድ የሚሉን ጠንካራ ማደፋፈሪያዎች አይደሉምን?ክየመ 19.4

    በሌላ በኩል ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈው፣ እግዚአብሔር በኃጢአት ላይ የሚሰጠውን ፍርድ የሚያሳየው፣ አይቀሬውን ቅጣት፣ የባህርያችንን ማሽቆልቆል እንዲሁም የመጨረሻውን ዘላለማዊ ጥፋትና ሰይጣንን ከማገልገል እንድንቆጠብ ለማስጠንቀቅ ነው::ክየመ 20.1

    ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ምህረት አጥብቀን መመልከት አይገባንም? ለመሆኑ እርሱ ከዚህ በላይ ምን ማድረግ ይችላል? በአስደናቂ ፍቅሩ ከወደደን ከዚህ አምላክ ጋር እራሳችንን በቀጥተኛ ግንኙነት ላይ እናስቀምጥ።ወደ እርሱ አምሳል እንለወጥ ዘንድ የተዘጋጀልንን መንገድ ለመጠቀም በመትጋት ከአገልጋይ መላእክቱ ጋር ባለን ህብረት በመደሰት ከአብና ከወልድ ጋር የሰመረ ግንኙነት ይኑረን፡፡ክየመ 20.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents