Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ቀደምት ጽሑፎች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    8—የእምነታችን መፈተን

    በዚህ የፈተና ወቅት ልንበረታታና እርስ በርሳችን ልንጽናና ይገባል፡፡ ዛሬ የሰይጣን ፈተናዎች ከመቼOም ጊዜ በላይ የላቁ ናቸው ምክንያቱም እርሱ ያለው ጊዜ አጭር መሆኑንና እያንዳንዱ ጉዳይ በህይወት ወይም በሞት ውሳኔ እንደሚጠናቀቅ ያውቃል፡፡ ጊዜው ተስፋ የሚቆረጥበትና በፈተና ውስጥ የሚሰጠምበት አይደለም፡፡ በከንቱ ነገሮች መነሁለላችንን ተቋቁመን ሙሉ ለሙሉ በኃያሉ የያዕቆብ አምላክ መታመን ይኖርብናል: ሊገጥሙን ለሚችሉ ፈተናዎች ሁሉ---ጸጋው በቂ መሆኑን ጌታ አሳይቶኛል፡፡ ምንም እንኳ ፈተናዎች ከመቼውም ይልቅ ከፍተኛ ቢሆኑም ነገር ግን እግዚአብሔርን ሙሉ ለሙሉ የምንታመነው እስከሆነ ድረስ ለእያንዳንዱ ፈተና በጸጋው ባለ ድል እንሆናለን፡፡ EWAmh 30.1

    የሚገጥሙንን ውጣ ውረዶች ተቋቁመን በሰይጣን ፈተና ላይ ድል የምንጎናጾፍ ከሆነ በእምነታችን ዙሪያ የሚመጡትንም ፈተናዎች እንዲሁ በማለፍ ከወርቅ ይልቅ የከበርን—ቀጣዩን ፈተና ለመቋቋም ጠንካራና የተሻለ ዝግጅት ያለን እንናለን: ነገር ግን ቁልቁል የምንሰጥምና ለሰይጣን ፈተናዎች መንገድ የምንከፍት ከሆነ እየተዳከምን በመሄድ በፈተናው ድል አንቀዳጅም… ለቀጣዩም ፈተና በቂ ዝግጅት አይኖረንም:፡፡ በዚህ መልኩ የሰይጣን ፈቃድ ምርኮኛ እስክንሆን እየጫጨን እንሄዳለን፡፡ መላውን የእግዚአብሔር የጦር ትጥቅ ዕቃ ለብሰን በማንኛውም ወቅት ከጨለማው ኃይል ሊነሳ ለሚችል ውዝግብ ዝግጁ ልንሆን የግድ ነው፡፡ ፈተና ሲገጥመን ወደ አግዚአብሔር በመሄድ በጸሎት ከአርሱ ጋር እንፋለም፡፡ እርሱ የምናሸንፍበትንና የጠላትን ኃይል የምንሰባብርበትን ጸጋና ብርታት ይሰጠናል እንጂ ባዶአችንን አይተወንም፡፡ እነዚህን ነገሮች በእውነተኛ ብርሃናቸው ማየት ስትችሉ እንደ የሱስ መልካም ወታደር አስቸጋሪውን ሁኔታ ሁሉ የምታልፉ ትሆናላችሁ እስራኤልም በእግዚአብሔር በመጠንከር በአምላካዊው ገናና ኃይል ወደ ፊት ይተማል። EWAmh 30.2

    እግዚአብሔር ሕዝቡን ለማንጻት በማሰብ ይጠጡት ዘንድ የሰጣቸው መራራ ጽዋ መኖሩን አሳይቶኛል፡፡ ይህ የሚጨለጠው ጽዋ መራራ ቢሆንም ነገር ግን ሕዝቡ በማጉረምረምና በቅሬታ ይበልጥ መራራ ሊያደርገው ይችላል:: ነገር ግን ጽዋውን የሚቀበሉ ሁሉ ይህ የመጀመሪያው ጽዋ በልብ ላይ የታለመለትን ውጤት ስለማያመጣ ሌላ የሚጎነጩተመድኃኒተሊኖር የግድ ነው፡፡ ደግሞም ሁለተኛውም እንዲሁ በሥራው ላይ ውጤት ካላመጣ ያ የታለመው ውጤት አስኪመጣ ወይም ጭራሹኑ የጎደፉና ልባቸው የረከ እስኪሆኑ ድረስ አሁንም በተደጋጋሚ ሌላ ሊወስዱ የግድ ነው:: ይህ መራራ ጽዋ በትዕትሥት በልብ ጽናትና በጸሎት ጣፋጭ ሊሆን እንደሚችል ተመልክቼአለሁ:: ይህ ሲሆን በሚቀበሉት ልብ ላይ የታለመለትን ውጤት ያመጣልእግዚአብሔርም ይከራል ከፍ ከፍም ይላል፡፡ ክርስትናን መከል፣ ከእግዚአብሔር አዎንታን ማግኘትና የእርሱ ንበረተመን ቀል ነር :ይደ/ም: ጌታ ህይወታቸው ከሥራቸው ጋር አብሮ የማይሄደውን ወቅታዊውን እውነታ ተቀብለናል የሚሉ ሰዎችን አሳይቶኛል: እነዚህ ሰዎች እጅግ የወ ረደ ደረጃ ያለው ኃይማተኛነት የነበራቸውና ከመጽሐፍ ቅዱሳዊውም ቅድስና እንዲሁ በእጅጉ የራቁ ናቸው:: አንዳንዶቹ ከንቱና ተገቢ ባልሆነ ንግግር የተጠመዱ ሲሆኑ ሌሎች ደግሞ እራሳቸውን ከፍ በማድረግ የሚመጻደቁ ናቸው:: እራሳችንን እያስደሰትን፣ እንደ ዓለማዊ እየኖርንና እየታየን፣ የዓለምን ደስታ የግላችን እያደረግንና ዙሪያችንን በዓለማውያን ጥቅም ተከብበን ከክርስቶስ ጋር በክብር ልንግሥ አንችልም:: EWAmh 30.3

    ወደፊት የእርሱ ክብር ወራሾች እንድንሆን የምንፈልግ ከነ ዛሬ በዚህ ምድር የክርስቶስ ሥቃይ ተካፋዮች ልንሆን ይገባል:: እግዚአብሔርን ለማስደሰት በመፈለግና የከበረው አምላካዊ ነገር ወደፊት እንዲገሰግስ በማድረግ ፋንታ የራሳችንን ፍላጎት የምናሳድድና እራሳችንን እንዴት በተሻለ ማስደስት እንዳለብን የምናስብ ከሆነ እግዚአብሔርንም ሆነ እንወደዋለን የምንለውን የተቀደሰ ነር እናዋርዳለን: ለእግዚአብሔር ለመሥራት የቀረን ጊዜ አጭር ነው:: ተብታትነውና ተጎድተው ለሚገኘ ት የየሱስ መንጋዎች ደኅንነተን መስዋዕት አድርገን የምናቀርበው ማንኛውም ነገር እጅግ የከበረ ሊሆንብን ይገባም አሁን እራሳቸውን መሥዋዕት አድርገው በማቅረብ ከእግዚአብሔር ጋር ኪዳን የሚገቡ ሁሉ የከበረውን ሽልማተሊጋሩና አዲሱን መንግሥት ከለዘላም አስከ ዘላለም የራሳቸው ሊያደርጉ በቅርቡ በሰማያዊው ቤታቸው ይሰባሰባሉ፡፡ EWAmh 31.1

    ለጌታ የተቀደሰ ህይወት እንር:: ቅንና ትሁት የየሱስ ተከታዮች እንደመሆናችን ይህ አኗኗራችን በሥርዓት በተቀመረ ህይወትና ፈሪሃ እግዚአብሔር ባለው ንግግራችን ይታይ: በጨለማ የተዋጠው የመከራውና የሥቃዩ ምሽት ሲመጣ ለእግዚአብሔር ለመሥራት እጅግ የዘየን እንዳንሆን አሁን ቀኑ እያለቀ ባለበተበዚህ ወቅት ልንሠራ የግድ ነው: የሱስ ከመቅደሱ ከመውጣቱ አስቀድሞ ለእስራኤል መተላለፍ ይቅርታውን በመስጠት ይጋርደን ዘንድ አሁን በቅዱስ መቅደሱ ሆኖ መስዋዕታችንን፣ ጸሎታችንንና የኃጢአት ኑዛአችንን እየተቀበለ ይገኛል: የሱስ መቅደሱን ለቅቆ ሲወጣ ቅዱስና ጻድቅ የሆኑት ኃአታቸው ስeተወደላቸው አሁንም ቅዱስና ጻድቅ ሆነው በመቅረት በህያው አምላክ ማኅተም ይታተማሉ፡፡ ነገር ግን ቀድስና የጎደላቸው ኃጥአን—ቅድስና የጎደላቸውና ኃጢአተኞች እንደሆኑ ይቀራሉ፡፡ ለዚህ መንስዔው እነርሱ የሚያቀርቧቸውን መስዋዕቶኙ፣ ጸሎትና የኃጢአት ኑዛ በመቀል ወደ አባቱ ዙፋን የሚያደርሰው ካኅን በመቅደሱ ውሰጥ ስለማይኖር ነው:: በመሆኑም ነፍሳትን ከሚመጣው የቁጣ ማዕበል የመታደጉ ሥራ የሱስ የሰማያዊውን ቤተመቅደስ ቅድስተቅዱሳን ለቀቆ ከመውጣቱ አስቀድሞ መደረጉ የግድ ነው:: EWAmh 31.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents