Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ቀደምት ጽሑፎች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    23—የወንጌል ሥርዓት

    የወንጌል ሥርዓት በጣም በሚያስፈራ አኳኋን ቸል የተባለ መሆኑን ጌታ አሳይቶኛል: (በየአብያተክርስቲያናቱ ይገኙ የነበሩ አድቬንቲስቶች በመጀመሪያ ላይ ሌላ ቤተክርስቲያን መመስረት እንዳለባቸው የሚያውቁት ነገር አልነበረም:: ነገር ግን ከ1844 ዓ.ም. በኋላ ታላቅ ግራ መጋባት በመከሰቱ አብዛኞቹ አድቬንቲስቶች ማንኛውንም ድርጅት አጥብቀው ይቃወሙ ነበር ለዚህ ምክንያታቸው የክርስትና ድርጅቶች ፍጹም ከሆነው የወንጌል ነጻነት ጋር ስምሙ አይደሉም የሚል ነበር: የኤለን 2ይት ምስክርነትና ሥራዎች ምን ጊዜም ቢሆን አክራሪነትን ይቃወሙ ነበር በእርሷ የተሰጡ መመሪያዎችን መሰረት በማድረግ የድርጅት መኖር በተወሰነ መልኩ የነበረውን ግራ መጋባት እንደሚቀርፍ ታምኖበት ነበር) ልማዳዊው አሠራር ሊወገድ ቢገባውም ነገር ግን ይህ ሲሆን ሥርዓትን ጠብቆ መንቀሳቀስ ቸል ሊባል አይገባም፡፡ በሰማይ ሥርዓት አለ፡፡ ክርስቶስ በዚህ ምድር በነበረበት ጊዜ በቤተክርስቲያን ሥርዓት እንደነበር ሁሉ ከእርሱ ዕርገትም በኋላ ይኸው ሥርዓት በሐዋርያቱ ዘንድ በጥብቅ ይተገበር ነበር፡፡ እንዲሁም አሁን አግዚአብሔር ልጆቹን ወደ እምነት አንድነት እያመጣ ባለበት በእነዚ የመጨረሻ ቀናት ሥርዓት ከመቼውም ጊዜ በላቀ ጉልህ ጠቀሜታ አለው፡፡ እግዚአብሔር ልጆቹን ወደ አንድነት ሲያመጣ ሳለ ሰይጣንና የእርሱ ክፉ መላእክት ይህን አንድነት ለመከላከልና ለማጥፋት በእጅጉ ተግተው እየሠሩ ነው፡፡ በዚህ የተነሳ ምናልባትም ይንከባከቧቸው ዘንድ እግዚአብሔር በቤታቸው ለሰጣቸው ለጥቂቶቹ ያልታመኑና ቤተሰባቸውን እንኳ ማስተዳደር የሚሳናቸው፤ ሥርዓት የሌላቸው ወይም ጥበብ የሚጎድላቸውና ፍርድ መስጠት የማይችሉ ሰዎች--መንጋውን ለማስተዳደር እራሳቸውን ብቁ አድርገው በመቁጠር ወደ ሥራው ለመግባት ተቻኩለዋል፡፡ ከእምነታችን ጋር ትውውቅ ያላደረጉ ሰዎች እነዚህ ብቁነን ባዮች የሚፈጽሟቸውን አያሌ በስህተት የተሞሉ እንቅስቃሴዎች በመመልከት ሌ ሎቹም መልእክትኞች እንደነርሱ ራሳቸውን የላኩ ናቸው ብለው ሁሉንም በአንድ ይፈርጇቸዋል፡፡ በዚህ የተነሳ አምላካዊው መርኅ ትችት ላይ በመውደቁ ታማኝ ሊሆኖ ይችሉ የነበሩ ብዙዎች እውነትን በማራቅ ነገሩ አንዲህ ነው ወይ? በማለት እንዲጠይቁ ሆነዋል፡፡ EWAmh 73.1

    ቅድስና የጎደለው ህይወት የሚመሩና ወቅታዊውን እውነት ለማስተማር ብቃት የሚጎድላቸው ሰዎች ወደ መስኩ የሚገቡት በቤተክርስቲያን ወይም በአጠቃላይ በወንድሞች እውቀና ሳይሰጣቸው በመሆኑ ውጤቱ ግራ መጋባትና መከፋፈል ይሆናል፡፡ አንዳንዶች የእውነት ንድፈ ሃሳብ ስላላቸው ብቻ ክርክር ማቅረብ ቢችሉም ነገር ግን የመንፈሳዊነት፣ የፍርድና የተሞክሮ ባለቤት አይደሉም፡፡ ሌሎች መከራከር ባይችሉም ነገር ግን ጥሩ ጸሎታቸውን ተከትሎ ጥቂት ወንድሞች ስለሚያዳምጧቸውና በየጊዜው አስደሳች ማደፋፈሪያ ስለሚሰጧቸው ያለ በቂ ተሞክሮና ፍርድ እግዚአብሔር ብቁ አድርጎ ሳይመርጣቸው በመስኩ ለመሰማራት ተገፋፍተዋል፡፡ እነዚህ ሰዎች ከፍ ከፍ እየተደረጉ በሄዱ ቁጥር መንፈሳዊ ኩራት ይመጣና የመስኩ ሠራተኞች እንደሆኑ አድርገው በማሰብ ይታለላሉ፡፡ እራሳቸውን የማያውቁት እነዚህ ሰዎች ፍትህና ርትዕን ኣያስተውሉም! ማገናዘብ የሚችሉበት ትዕግሥት የላቸውም፤ በመታበይ ይናገራሉ EWAmh 73.2

    እንዲሁም ከአምላካዊው ቃል ሊያ ረጋግጡ የማይችሏቸውን አያሌ ነገሮች ይደሰኩራሉ፡፡ ይህን ሁሉ የሚያውቀው አምላክ በእንደነዚህ ዓይነቶቹ አደገኛ ወቅቶች ያገለግሉት ዘንድ ጥሪ አያደርግላቸወም፡፡ ወንድሞች እነዚን እርሱ ያልጠራቸውን በመስኩ እንዲሰማሩ ከመገፋፋት ሊጠነቀቁ ይገባል፡፡ እነዚህ በእግዚአብሔር ያልተጠሩ ሰዎች በአጠቃላይ ሲታዩ ተጠርተናል የሚል ብርቱ በራስ መተማመን ያላቸውና የእነርሱ አገለግሎት በእጅጉ አስፈላጊ እንደሆነ የሚያምኑ ናቸው፡፡ ለአገልግሎት ወደ መስክ ሲወጡ ይህ ነው የሚባል መልካም ተጽእኖ አያሳድሩም፡፡ ሆኖም በአንዳንድ ስፍራዎች ስኬት ማግኘታቸው በእርግጥ እነርሱም ሆኑ ሌሎች በእግዚአብሔር እንደተጠሩ እንዲያስቡ መንስዔ ይሆናል፡፡ የእግዚአብሔር መላእክት የወቅታዊውን እውነት አስተውሎ ታማኝ በሆኑ ልጆቹ ልቦና ውስጥ ለማስረጽ እየተንቀሳቀሱ እንደመሆናቸው ሰዎች በአገልግሎት ክንውን ማግኘታቸው በእግዚአብሔር ለመጠራታቸው አዎንታዊ ማስረጃ መሆን አይችልም፡፡ ምንም እንኳ እነዚህ እራሳቸውን የላኩ ሰዎች እግዚአብሔር ባላስቀመጣቸው ስፍራ እራሳቸውን አስቀምጠው መምራን ነን ቢሉ፤ እነርሱ የሚናገሩትን ተከትሎ ነፍሳት እውነትን መቀበላቸው በእግዚአብሔር ለመጠራታቸው መረጃ መሆን አይችልም፡፡ መልእክቱን ከእነርሱ የሚቀበሉ ነፍሳት ወደ ፈተናና ግዞት እንደሚመጡ አድርገው ይቀበሉታል፡፡ ሆኖም ኋላ ላይ እነዚህ ሰዎች በእግዚአብሔር ጉባዔ ቆመው እንዳልነበር ይረዳሉ፡፡ ጠማማ ሰዎች እውነትን በመናገራቸው አንዳንዶች ቢቀበሉም እንኳ ነገር ግን ሁናቴው እነዚህን የተናገሩትን ይበልጥ ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርቡ አያደርጋቸውም: በስህተት ውስጥ ያሉ ሰዎች አሁንም ያሉት በስህተት ውስጥ ነው፡፡ እነዚህ ሰዎች በእግዚአብሔር በተወደዱት ዘንድ የሰነዘሩትን ማታለልና በቤተክርስቲያን ያመጡትን ውዥንብር ያህል ቅጣታቸውም እንደዚያው መጠን የከበደ ይሆናል፡፡ ኃጢአታቸው በእግዚአብሔር አስፈሪ ቁጣ ቀን ይገለጣል እንጂ ተሸፍኖ አይቀርም:: EWAmh 74.1

    እነዚህ እራሳቸውን የላኩ መልእክትኞች ለሥራው መርገም ናቸው፡፡ ታማኝ ነፍሳት እነዚህ ሰዎች አምላካዊውን አቅጣጫ ይዘው ወደፊት እያመሩ መሆኑንና ከቤተክርስቲያን ጋር ህብረት እንዳላቸው አድርገው በማሰብ ድንጋጌና ደንቦችን ተከትለው ይመሩና ያስተዳድሩ ዘንድ በእነርሱ ላይ መተማመን ያደርጋሉ በእጃቸው ለመጠመቅም ፈቃደኝነታቸውን ይገልጻሉ፡፡ ነገር ግን ብርሃን በሚመጣ ጊዜ እነዚህ ሰዎች እነርሱ እንዳሰቧቸውና እንዳስተዋሏቸው በእግዚአብሔር የተጠሩና የተመረጡ መልእክትኞች አለመሆናቸውን ሲያስተውሉ ከእነርሱ የተቀበሏቸውን እውነቶች ሁሉ ዳግመኛ ሊማሩ እንደሚገባ ይሰማቸዋል፤ ሁናቴው ፈተናና ጥርጣሬ ውስጥ ይጥላቸዋል ጠላት በመላው ተሞክሮአቸው ላይ ግራ መጋባትና መደናገር እንዲከሰትባቸው አድርጎአል፡፡ በዚህም እግዚአብሔር እየመራቸው ይሁን አይሁን እርግጠኛ ስለማይሆኑ ዳግመኛ እንደ አዲስ ተጠምቀው እስኪጀምሩ ድረስ በሚገኙበት ሁኔታ እርካታ አይኖራቸውም:፡፡ የእግዚአብሔር መልእክትኞች ወደ አዲስ መስክ በመሰማራት ፋንታ ወደነዚህ አጉል ተጽእኖ ስር የወደቁ ነፍሳት መሄድ በእጅጉ አድካሚ ሥራ ነው: እነዚህ ሰዎች ህያው በሆነው እውነትና ሙት በሆነው መሃል የሚቆሙ እንደመሆናቸው ለተልዕኮአቸው፣ ታማኝ ለሆኑበት ነገርና እግዚአብሔር ተቆጣጣሪ አድርጎ በሾማቸው በመንጋዎቹ ላይ ከሚያሳድሩት ተጽእኖ---ስህተት የሆነውን ነገር ሳይሸፋፍኑ በግልጽ መናገራቸው የግድ ይሆናል EWAmh 75.1

    እውነትን ተቀብለው በእንዲህ ያለው ምስቅልቅል ወስጥ የገቡ ነፍሳት ሳይጠሩ እንደተጠሩ በሆኑ ጣልቃ ገቦች እጅ ባይወድቁ ኖሮ ጌታ ለትሁታኑ ያዘጋጀላቸውን ትክክለኛውን እውነት ባገኙ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ዐይኖች በእንቁዎቹ ላይ ስለነበር በማስተዋል የሚመሯቸውን የተጠሩትንና የተመ ረጡትን መልእክትኞቹን ወደ እነርሱ በመራ ነበር፡፡ የእውነት ብርሃን ወደነዚህ ነፍሳት በማብራት የእነርሱን እውነተኛ ሁናቴ በገለጠላቸው ነበር፡፡ ይህ ሲሆን እውነትን በማስተዋል ይቀበሉት ነበር፤ በውበቱና ንጽህናውም እርካታ ያገኙ ነበር፡፡ የእውነት ብርቱ ውጤት ሲሰማቸው ጠንካራና ቅዱስ ተጽእኖ ማሳረፍ ይችሉ ነበር EWAmh 75.2

    እግዚአብሔር ሳይጠራቸው ወደ ሥራው የገቡ ሰዎችን አደጋ በድጋሚ ተመለከትኩ፡፡ ምናልባትም እነዚህ ሰዎች ስኬት ቢያገኙ በማንኛ ውም ዘርፍ ክህሉት እንደሚያንሳቸው ለመገመት ይቻላል፡፡ የሚያደርጉትን ጥበብ የለሽና ማመዛዘን የጎደለው እንቅስቃሴ ተከትሎ አንዳንድ የከበሩ ነፍሳት ሰዎች ሊደረስባቸው ወደ ማይችል ስፍራ ተነድተው ይሄዳሉ፡፡ ቤተክርስቲያን ለእነዚህ ኃላፊነት ሊሰማትና ህይወታቸውን፣ ሙያቸውንና በአጠቃላይ መምህራን ነን በሚሉባቸው ዘርፎች ዙሪያ በአንክሮና በጥንቃቄ ማየት እንዳለባት ተመልክቻለሁ፡፡ እግዚአብሔር እነርሱን ስለ መጥራቱ ስህተት የሌለው ማስረጃ የማያቀርቡና ይህን ጥሪ የማይቀበሉ ከሆነ «ሐዘንና ዋይታው» በራሳቸው ላይ ይሆናል፡፡ በመሆኑም እነዚህ ስዎች እንደ መምህራን በቤተክርስቲያን እውቅና ያልተቸራቸው መሆኑ ይፋ ሊደረግ ይገባል፡፡ ቤተክርስቲያን በዚህ ጉዳይ ግልጽነት የተሞላው አካሄድ በመከተል ማድረግ የምትችለው ብቸኛው ነገር ሸክሙን ለራሳቸው መተው ነው፡፡EWAmh 75.3

    ይህ በመንጋው ላይ ግራ መጋባትና መደናገር የሚፈጥር ጠላት የሚገባበት በር መዘጋት እንደሚችል ተመልክቻለሁ፡፡: ይህ በር እንዴት መዘጋት እንደሚችል መልአኩን ጠይቄው ነበር እርሱም «ቤተክርስቲያን ፈጥና ወደ አምላካዊው ቃል በማምራት በተዘነጋውና ቸል በተባለው የወንጌል ሥርዓት ላይ መመስረት ይኖርባታል፡፡» በማለት መለሰልኝ፡፡ ይህ ቤተክርስቲያንን ወደ እምነት አንድነት ለመመለስ መተኪያ የማይገኝለት ነው፡፡ በሐዋርያት ዘመን ቤተክርስቲያን በሐሰተኛ መምህራን የመታለል አደጋ ላይ ወድቃ እንደነበር ተመልክቻለሁ፡፡ ይህን ለማስወገድ የገዛ ቤተሰባቸውን በሚገባ ማስተዳደር የሚችሉ፣ በቤተሰባቸው ሥርዓትና ደንብ የሚያስከብሩና በጨለማ ውስጥ ላሉት እውነትን መንገር የሚችሉ ሰዎችን ወንደሞች መርጠው ነበር: ከዚያም በእነዚህ ሰዎች አገልግሎት ዙሪያ እግዚአብሔር ከተጠየቀ በኋላ እንደ ቤተክርስቲያን አሠራርና መንፈስ ቅዱስ ሃሳብ እጅ ተጭኖባቸው ለሥራው ተለዩ፡፡ እነዚህ ሰዎች ተልእኮአቸውን ከእግዚአብሔር ከተቀበሉና ከቤተክርስቲያን ይሁንታ ካገኙ በኋላ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቁና የጌታን ቤት በሥርዓት እያስተዳደሩ ጉዞአቸውን በመግፋት የእርሱ ሥቃይና ሞት በተወደዱት የእግዚአብሔር ልጆች አእምሮ ውስጥ ዘወትር እየታደሰ ይኖር ዘንድ የአዳኙ ን የተሰበረ አካልና የፈሰሰ ደም አርማ ለቅዱሳኑ ያበረክቱላቸው ነበር፡፡ EWAmh 76.1

    ከሐዋርያት ዘመን ይልቅ ዛሬ ከሐሰተኛ መምህራን አስተምህሮ እንዳልተጠበቅን ተመልክቻለሁ:: ችግሩን ለመግታት እነርሱ እንዳደረጉት በመንጋው ውስጥ ሰላም፣ ስምምነት፣መጣጣምና ህብረት ለማምጣት የሚያስችሉ ለየት ያሉ አሠራሮችን ልንከተል ይገባል፡፡ ተገቢው ተሞክሮና ቀና አመለካከት ያላቸው ወንድሞች በአንድ ላይ ተሰባስበው መንፈስ ቅዱስ ይመራቸው ዘንድ በመፍቀድ እጆቻቸውን በእነዚህ ተልዕኮአቸውን ከእግዚአብሔር በቀበለ ላይ ጭነው ብርቱ ጸሎት ሊጸልዩላቸውና ሙሉ ለሙሉ ለሥራው ለይተው ሊያቀርቧቸው ይገባል:: ይህ ድርጊት መልእክትኞቹ ድንቅ የሆነውን ሰዎች ጆሮ ያልደረሰ መልእክት ይዘው ወደ ፊት ይገሰግሱ ዘንድ የቤተክርስቲያን ድጋፍና ፈቃድ ለመኖሩ አመላካች ይሆናል፡፡ EWAmh 76.2

    ቀደም ብሎ ሲከተሉት በነበረው ስህተት መንስዔ አእምሮአቸው ለተዳከመ፣ ፍርዳቸው ለተዛባባቸው፣ እራሳቸውን ፍጹምና መንፈሳዊ አድርገው ይቆጥሩ ለነበሩና በራሳቸውም ሆነ በሥራው ላይ ሐፍረት ላመጡ--- እግዚአብሔር ለተከበሩ መንጋዎቹ ጥንቃቄ ያደርጉ ዘንድ አደራ አይሰጣቸውም: ምንም እንኳ አሁን ከስህተት እንደጸዱ ሆነው ነጻነት ሊሰማቸው ቢችልና ይህን የመጨረሻ መልእክት ይዘው ለመገስገስ ብቃት ያላቸው ቢመስሉም እግዚአብሔር ግን አይቀበላቸውም: በስህተት ውስጥ በነበሩበት ወቅት አእምሮአቸው በተሳሳተአቅጣጫ ጥቅም ላይ በመዋሉና በመዳከሙ የከበሩትን ነፍሳት በእነርሱ አደራ ስር አይሰጥም፡፡ ታላቅና ቅዱስ የሆነው ቀናተኛ አምላክ የራሱን እውነት አንግበው የሚጓዙ ቅዱስ ሰዎች ይኖሩታል፡፡ በሲና ተራራ ላይ በእግዚአብሔር የተነገረውን ሕግ እና ሕጉን በጥንቃቄ የሚጠብቁ ቅዱስ ሰዎች ብቻቸውን ለሌሎች በማስተማር ያከብሩታል: EWAmh 77.1

    እውነትን የሚያስተምሩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የፍርድ ሰዎች ሊሆኑ ይገባል፡፡ ተቃውሞን መቋቋም የሚችሉና በቀላሉ ስሜታቸው የማይነካ መሆንም ይጠበቅባቸዋል፡፡ ያለበለዚያ ግን እውነትን የሚቃወሙ ሰዎች ከመልእክታቸው ላይ መዝዘው በመውሰድ የሚያቀርቡት ተቃውሞ የከፋ ሊሆን ይችላል፡፡ መልእክቱን የሚያሰራጩ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ተቃውሞዎቹን በእውነት ብርሃን ላይ ተመርተው በእርጋታና በትህትና ለማስወገድ ዝግጅት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ተቃዋሚዎች የእግዚአብሔር አገልጋዮች ገንፍለው የቁጣ ተፈጥሮአቸው እንዲወጣ በማድ ረግ ትእዛዛቶቹን መጠበቅ አለባቸው ብለው የሚያስተምሩት መምህራን መራራ መንፈስ የተጸናወታቸው ናቸው ብለው ስማቸውን ለማጥፋት ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋሉ፡፡ ለሚመጡት ተቃውሞዎች በትዕግሥት፣ በፍርድና በቅንነት ዝግጅት ማድረግ እንዳለብን ተመልክቻለሁ፡፡ ተቃውሞዎቹ የቱንም ያህል ክብደት ቢኖራቸው፤ እነርሱን ማስወገድ ወይም አዎንታዊ ማረጋገጫ ን በማቅረብ ተቃዋሚውን መምታትና ጠንካራ መንፈስ ማሳየት ሳይሆን ነገር ግን ለተቃውሞዎቹ የራሳቸውን ክብደት በመስጠት ብርሃን በላያቸው እንዲፈነጥቅና የእውነት ኃይል እንዲገለጥ በማድረግ ስህተቶቹን እንዲያስወግዳቸው መፍቀድ ይገባል፡፡ ይህ ሁናቴ ጥሩ ግንዛቤ እንዲፈጠር Iማድረግ ለእውነት ታማኝ የሆኑ ተቃዋሚዎች ተታልለው እንደነበር እንዲገነቡና፤ ትእዛቱን ጠባቂዎች እነርሱ እንዳስቧቸው ዓይነት ህዝቦች አለመሆናቸውን እንዲያምኑ ይረዳቸዋል:: EWAmh 77.2

    እራሳቸውን የሕያው እግዚአብሔር አገልጋዮች አድርገው የሚቆጥሩ ፤ የሁሉም አገልጋዮች ለመሆን ፈቃደኞች ሊሆኑ ይገባል፡፡ በወንድሞች ላይ ከፍ ከፍ በማለት ፋንታ ደግና ትሑት መንፈስ መላበስ ይኖርባቸዋል፡፡ ቢሳሳቱ ስህተቶቻቸውን ሙሉ ለሙሉ ለመናዘዝ ዝግጁ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ መልእክትኛው ንስሐ በመግባቱ መልካም አርhያ ይሆናል እንጂ ቤተክርስቲያን በእርሱ ላይ ያላት መተማመን እንዲቀንስ አያደርግም:: የንስሐ መንፈስ በቤተክርስቲያን ሲበረታታ በውጤቱ ጣፋጭ አንድነት ይመጣል፡፡ መምህራን ለመሆን የሚፈቅዱ ነፍሳትን ለየሱስና ለመጽሐፍ ቅዱሳዊው እውነት ማሸነፍ ይችሉ ዘንድ የቅድስና፣ የቅንነት፣ እራስን የማዋረድና ርኅራኄ የተሞላውን መንፈስ ማንጸባረቅ ይኖርባቸዋል፡፡ የክርስቶስ አገልጋይ በአነጋገሩም ሆነ በድርጊቱ ንጽሕና ሊኖረው ይገባል፡፡ የሚያነቃቁና በእግዚአብሔር ቅድስና የተሞሉ ቃላት ተሽክሞ መሄዱ ምን ጊዜም በአእምሮው ሊታወሰው ይገባል፡፡ እንዲሁም መንጋው ለእርሱ አደራ መሰጠቱን ዘወትር በማስታወስ የሱስ ወደ አባቱ እንደሚማልድልን እነርሱም ወደ የሱስ ይዞአቸው በመቅረብ ልመናውን ሊያቀርብ ይገባል: ወደ ጥንታውያኑ የእስራኤል ልጆች ተወስጄ እንድመለከት ተደረግኩ፡፡ የቤተመቅደሱ አገልጋዮች ይፈጽሟቸው የነበሩ ሥርዓቶች ከእግዚአብሔር ጋር ቅርብ ግንኙነት እንዲኖራቸው መንስዔ ስለነበሩ ምን ያህል ንጹህና ቅዱስ መሆን እንደነበረባቸው ተመለከትኩ፡፡ አገልግሎት የሚሰጡ……ቅዱስ፣ ንጹህና ያለ ነቀፋ መሆን ነበረባቸው፡፡ ያለበለዚያ ግን እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል፡፡ እግዚአብሔር አልተቀየረም፤ እርሱ ዛሬም እንደቀድሞው ቅዱስና ንጹህ ነው፡፡ የየሱስ አገልጋዮች የሚሆኑ ሁሉ የግል ተሞክሮና ጥልቅ ቅድስና ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡ ይህ ሲሆን በማንኛውም ጊዜና ቦታ ቅዱስ ተጽእኖ ማሳደር ይችላሉ፡፡ EWAmh 78.1

    ክፍተት ካገኙ መልእክትኞች የሚወጡበት ጊዜው አሁን መሆኑንና እግዚአብሔር አብሯቸው በመውጣት አንዳንዶች ይሰሙ ዘንድ ልባቸውን እንደሚከፍት ተመልክቻለሁ፡፡ ወደ አዳዲስ ስፍራዎች ሊገባ የግድ እንደመሆኑ ይህ ገቢራዊ ሲሆን መልእክትኞች ሁለት ሁለት ሆነው እጅ ለእጅ ተያይዘው ሊሰማሩ ይገባል፡፡ እንዲህ ያለው ዕቅድ ተግባር ላይ ውሎ ነበር፡፡ ወንድሞች ሁለት ሁለት በመሆን ከፍተኛ ተቃውሞ ወዳለባቸውና ብዙ ሥራ ሊሠራባቸው ተገቢ ወደሆኑ በጨለማ ወደ ተዋጡ ስፍራዎች መሰማራት ሲጀምሩ በተባበረ ጥረትና ጠንካራ እምነት እውነትን ለእነዚያ በጨለማ ላሉት መመስከር ይችላሉ፡፡ በዚህ መልኩ አያሌ ስፍራዎችን በመጎብኘት ክንውን ማግኘት የሚችሉ ከሆነ ተለያይተው በመሰማራት ቶሉ ቶሎ እየተገናኙ እርስ በርስ በእምነት እየተጽናኑና አንዱ የሌላውን ክንድ እየደገፈ መጓዝ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪ በተከፈቱላቸው የአገልግሎት መስኮች ለቦታው የትኞቹ ዓይነት መንፈሳዊ ስጦታዎቻቸው በእጅጉ አስፈላጊ እንደሆኑ ለይተው በመመልከት ወደ ሰዎች ልብ በስኬታማነት ለመድረስ በሚያስችሏቸው መንገዶች ዙሪያ አንዱ የሌላውን ምክር ይቀበል፡፡ መልእክትኞቹ ዳግመኛ ሲለያዩ ተቃውሞውንና ጨለማውን ለመጋፈጥ ወኔና ኃይላቸው ስለሚታደስ እየጠፉ ያሉተን ነፍሳት ያድኑ ዘንድ ከልብ በሚቀጣጠል ስሜት ይሠራሉ፡፡ EWAmh 78.2

    የእግዚአብሔር አገልጋዮች ነፍሳትን በአዳዲስ ስፍራዎች መፈለግ እንጂ ተመሳሳይ ስፍራ ደጋግመው መመላለስ እንደሌለባቸው ተመልክቻ ለሁ፡፡ አንዴ በእውነት ላይ የተመሰረቱት ነፍሳት መጠነ ሰፊ አገልግሎተይሰጣቸው ዘንድ መጠየቅ የለባቸውም፤ ይልቁንም በራሳቸው መቆም መቻ ልና ሌሎችን ማበረታታት የሚጠበቅባቸው ሲሆን፧ የእግዚአብሔር መልእክትኞች ደግሞ በጽልመት የተዋጡና በብቸኝነት የሚንከላወሱ ስፍራ ዎችን በመጎብኘት ለሌሎች እንዳደረጉት ሁሉ ለእነዚህም ወቅታዊው ን እውነትን የማሰራጨት ኃላፊነት ለባቸው፡፡ EWAmh 79.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents