Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ቀደምት ጽሑፎች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    61—ስፕሪችዋሊዝም

    የስህተት አስተምህሮ አካል የሆነው የመነጠቅ ምንነት ተገልጾልኝ ነበር፡፡ ሰይጣን በየሱስ ያንቀላፉ ዘመዶቻችንንም ሆነ ጓደኞቻችንን አካላዊ አቋምም ሆነ ገጽታ አስመስሎ የማቅረብ ኃይል እንዳለው ተመልክቻለሁ: እነዚህ ወዳጆቻችን በህይወት በነበሩ ጊዜ በተደጋጋሚ ይናገሯቸው የነበሩ ቃላቶችን በራሳቸው ዓይነት የድምጽ ቃና እንደሚናገሩ አድርጎ ያቀርባል፡፡ ይህን ሁሉ የሚያደርገው ዓለምን ለማሳትና ወጥመዱ ውስጥ ለመክተት ነው፡፡ EWAmh 193.1

    ቅዱሳን በወቅታዊው እውነት ዙሪያ መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት ያደረገ ጥንቃቄ የተሞላው ማስተዋል ሊኖራቸው እንደሚገባ ተመልክቻለሁ፡፡ ዲያብሎሳዊው መናፍስት ተወዳጅ ዘመዶቻቸውን ወይም ጓደኞቻቸውን በመምሰል ከፊታቸው በመገለጽ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያልተጻፉ አስተምህሮ ዎችን ሊነግሯቸው ስለሚችሉ ሙታን የሚገኙበትን ሁናቴ ማስተዋላቸው የግድ ይሆናል፡፡ ድጋፍ ያገኙ ዘንድ በተቻላቸው ኃይል በመሥራት ለተናገሩት ማረጋገጫ ተአምራት ያደርጋሉ፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሙታን አንዳችም እንደማያውቁ በማስተዋልና የሞቱትን መስለው የሚታዩት ዲያብሎሳዊ መናፍስት መሆናቸውን በማወቅ እነዚህን መናፍስት ለመቋቋም የሚያስችላቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት በመጨበጥ ዝግጅት ሊያደርጉ ይገባል፡፡ EWAmh 193.2

    አመክኖዎቻችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እንደመሆናቸው የተስፋችንን መስ ረት በሚገባ መርምረን ልናውቅ ይገባል፡፡ ይህ የስህተት አስተምህሮ ወደፊት እየተስፋፋ ስለሚሄድ ፊት ለፊት የምንጋፈጥበት ጊዜ ይመጣል፡፡ በመሆኑም ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እስካላደረግን ድረስ በወጥመዱ ውስጥ በመውደቅ መታለል ሊደርስብን ይችላል፡፡ ነገር ግን ከፊታችን ላለው አስቸጋሪ ሁናቴ በየግላችን ማድረግ የምንችለውን ካደረግን እግዚአብሔርም እንዲሁ በእርሱ በኩል ያለውን በመሥራት ኃያል ክንዱ ይጠብቀናል፡፡ በቅርቡ ታማኝ ነፍሳትን ከሰይጣን የሐሰት ተአምራቶች ከብበው የሚጠብቁ በክብር የተሞሉ መላእክትን ይልካል፡፡ EWAmh 193.3

    ይህ የሐሰት አስተምህሮ ምን ያህል በፍጥነት እየተሰራጨእንደነበር ተመልቻለሁ:: በፊቴ በመብረቅ ፍጥነት የሚበሩ ባቡሮችን ተመልክቼ ነበር፡፡ መልአኩ በአንክሮ እንድመለከት ስላዘዘኝ ዐይኖቼን በባቡሩ ላይ ተከልኳቸው መላወ ዓለም በባቡሩ ተሳፍሮ የሚሄድ ይመስል ነበር፡፡ ተሳፋሪዎቹ በሙሉ ጥሩ ቁመናና ክብር ያለው የሚመስለውን መሪ በኣክብሮት ይመለከቱ እንነበር መልአኩ አሳየኝ፡፡ ባየሁት ነገር ግራ በመጋባት ይህ ሰው ማን እንደሆነ መልአኩን ጠየቅኩት፡፡ እርሱም ሲመልስልኝ «ይህ በብርሃን መልአክ አምሳያ የሚሠራው ሰይጣን ነው፡፡ መላውን ዓለም በግዞቱ ስር አውሏል፡፡ በህዝቡ ላይ ኩነኔ ሊያመጣ የሚችል ጠንካራ ማታለያ በመቅረቡ ሐሰትን እንዲያምኑ ሆነዋል፡፡ በሥልጣን ተዋረዱ ከሰይጣን በመቀጠል የሚገኘው ወኪሉ መሐንዲስ ሲሆኑ ሌሎቹም ወኪሎች በተለያዩ ኃላፊነቶች ይሠራሉ፡፡ እርሱ በፈለጋቸው ጊዜ ሰዎችን ወደ ዘላለማዊ ጥፋት ለመምራት በመብረቅ ፍጥነት እየበረሩ ይሰማራሉ፡፡” EWAmh 193.4

    በባቡሩ ሳይሳፈሩ የቀሩ እንዳሉ መልአኩን ጠየቅኩት፡፡ እርሱም በተቃራኒ አቅጣጫ በጠባብ መንገድ ይጓዝ የነበረ አንድ አነስተኛ መንጋ አሳየኝ፡፡ ሁሉም በእውነት ላይ ጥብቅ ህብረት ያላቸው ይመስላሉ፡፡ ይህ አነስተኛ መንጋ በብዙ መከራና ውዝግብ መሃል ያለፈ በሚመስል መልኩ ሽክም ይታይበታል፡፡ ጸሐይ ከጀርባቸው ወጥታ ገጽታቸው ላይ ጥላ አጥልቶ ወደ ድል የተቃረቡ አሸናፊዎች መስለው ይታያሉ፡፡ EWAmh 194.1

    ዓለም የሰይጣንን ወጥመድ ለይቶ የሚያውቅበት ዕድል በጌታ እንደተሰጠው ተመልክቼ ነበር፡፡ በከበረውና በእርኩሱ መሃል አንዳችም ልዩነት እንደሌለ ተደርጎ መቀመጡ ብቻውን ለክርስቲያኖች እንደ በቂ መረጃ ነበር፡፡ አሁን አካሉ በስብሶ ወደ ትቢያ የተቀየረውና በሺሁ ዓመት መጨረሻ በሁለተኛው ትንሳኤ የተዘጋጀለትን የሞት ዋጋ ሊቀበል የሚነሳው ቶማስ ፔይን በሰማይ እንደሚገኝና በዚያ እንደ ከበረ ተደርጎ በሰይጣን ቀርቦ ነበር፡፡ ይህ ሰው በአንድ ስፍራ ላይ ሆኖ እያስተማረ እያለ በሌላም ቦታ እያስተማ ረ አድርጎ ያቀርበው የነበረው ሰይጣን በምድር ላይ የሚችለውን ያህል ተጠቅሞበት ሲያበቃ አሁን ደግሞ በሰማይ በእጅጉ ከብሮ እንደሚገኝ ያስመስላል፡፡ የቶማስ ፔይንን ህይወት፣ ሞትና የስህተት አስተምህሮ በታላቅ ፍርሃት የተመለከቱ አንዳንዶች እግዚአብሔርንና ሕጎቹን ያዋረደውን በእጅጉ የከፋው የዚህን ሰው አስተምህሮ እንደተቀበሉ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ EWAmh 194.2

    የሐሰት ሁሉ አባት የሆነው ዲያብሎስ መላእክቱን ልኮ የሐዋርያቱን ገጽታ ተላብሰው እንዲናገሩ በማድረግ በምድር ላይ ሳሉ በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው የጻፏቸው መልእክቶች እርስ በርሳቸው እንደሚጋጩ አድርገው እንደሚያቀርቡ በማስመሰል ዓለምን የማሳወርና የማታለል ሥራ ይሠራል እነዚህ ሐሰት የሚናገሩ መላእክት ሐዋርያቱ የራሳቸውን አስተምህሮ የተበ ረዙና የተከለሱ ናቸው ብለው እንደሚናገሩ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ ሰይጣን በእግዚአብሔር ቃል ላይ ጥርጣሬ በመፍጠር የክርስትናን ስም የተሸከሙትንም ሆነ መላውን ዓለም ጥርጣሬ ውስጥ በመጣሉ ደስ ይሰኛል ቅዱሱ መጽሐፍ ሰይጣናዊውን ዕቅድ በቀጥታ የሚያከሽፍ በመሆኑ ሰዎች የዚህን መልእክት ለኮታዊነት ይጠራጠሩ ዘንድ ይመራ ዋል፡፡ በመቀጠል ከሃዲው ቶማስ ፔይን በሞተጊዜ በታላቅ መስተንግዶ ስማይ እንደገባና አሁን በምድር ላይ ይጠላቸው ከነበሩ ሐዋርያት ጋር ሕብረት ፈጥሮ ዓለምን በማስተማሩ ሥራ እንደተጠመደ በማቀናበር ያቀርባል፡፡ EWAmh 194.3

    ስይጣን እያንዳንዱ መላእክት የሚጫወተውን ገጸ ባህሪ ይሰጠዋል፡፡ ሁሉም አጭበርባሪ፣ ቀጣፊና አታላይ ይሆኑ ዘንድ ትእዛዝ ይቀበላሉ፡፡ አንዳንዶች የሐዋርያቱን ገጸ ባህሪ በመውረስ እንደ እነርሱ እንዲናገሩ መመሪ ያ ሲሰጥ ሌሎች ደግሞ በምድራዊ ህይወታቸው ከሃዲና ክፉ የነበሩ፣ እግዚአብሔርን ተራግመው የሞቱ ሰዎችን ገጸ ባህሪ በመውረስ አሁን ግን በጣም ኃይማኖተኞች ሆነው ይቀርባሉ፡፡ በዚህ መልኩ እጅግ ቅዱስ በሆኑት ሐዋርያትና በእርጉም ከሃዲዎች መሃል አንዳችም ልዩነት የለም፡፡ ሰይጣን ሁለቱንም ቡድኖች ያዘጋጀው ለተመሳሳይ ዓላማ ነው፡፡ የእርሱ ዕቅድ ይስመርለት እንጂ ማናቸውንም እንዲናገሩ ቢያደርግ ደንታ የለውም፡፡ ፔይን በምድር ላይ ሳለ ለሠራው ሥራ እገዛ በማድረጉ ረገድ ሰይጣን ከጎኑ ስለ ነበር እርሱ ይጠቀማቸው የነበሩትን ቃላትም ሆነ ዓላማውን በሚገባ ያራመደለትን የዚህን ታማኝ አገልጋዩን የእጅ ጽሑፍ በሚገባ ያውቃል፡፡ አብዛኞቹ የፔይን ጽሑፎች በሰይጣን አቀባይነት የተጻፉ በመሆናቸው እነዚህኑ ቃላት ለመላእክቱ በቃል እየነገረ እንዲጽፉ በማድረግ ከቶማስ ፔይን ብዕር እንደወጡ አድርጎ ማስመሰል ለእርሱ ቀላል ነው፡፡ ይህ የረቀቀ የሰይጣን ሥራ ነው፡፡ ይህ ሁሉ አሁን በህይወት ከሌሉ ሐዋርያት ፣ ከቅዱሳንና ከክፉ ሰዎች አንደበት እንደወጣ ተደርጎ የሚቀርበው አስተምህሮ ቀጥተኛው ምንጭ ሰይጣናዊው ግዛት ነው፡፡ EWAmh 195.1

    እግዚአብሔርን ፍጽም በሆነ መልኩ ይጠላ የነበረውና ለሰይጣን ተወዳጅ የነበረው ፔይን አሁን ከቅዱሳን ሐዋርያትና መላእክት ጋር በክብር እንደሚገኝ ሆኖ የመቅረቡ ተጨባጭ እውነታ የሰይጣንን ጭምብል ከሁሉም አእምሮ ውስጥ በማስወገድ በጽልመት የተሞላውን ምስጢራዊ ሥራ ለማጋለጥ በቂ ይሆናል፡፡ እርሱ ለዓለምም ሆነ ለከሐዲዎች እንዲህ በማለት ይናገራል «የቱንም ያህል ክፋት ቢኖራችሁ፣ በእግዚአብሔር ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ብታምኑ ወይም ባታምኑ፣ ደስ እንዳላችሁ ኑሩ፧ ሰማይ ቤ ታችሁ ነው፡፡ ቶማስ ፔይንን በሰማይ እስከኖረና በዚያ እስከ ከበረ ድረስ ሁሉም በዚያ ይሆናሉ፡፡» ይህ አባባል ሉም ፈቃዳቸው እስከ ሆነ ድረስ ሰማይን ማየት እንደሚችሉ ያሳያል፡፡ አሁን ሰይጣን ከወደቀበት ጊዜ አንስቶ እየሠራ ያለውን ሥራ እንደ ቶማስ ፔይን ባሉ ግለሰቦች አማካኝነት በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ እርሱ ኃይሉን ተጠቅሞ የሐሰት ተአምራቶችን በማድረግና የክርስቲያኖችን ተስፋ በመናድ ወደ ሰማይ የሚወስደው ጠባብ መንገድ ላይ እያራች ያለችውን ጸሐይ እያጠፋ ይገኛል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት መጻፉን በማስተባበልና ከታሪክ መጽሐፍነት በዘለለ ፋይዳ እንደሌለው አድርጎ በማቅረብ---መንፈሳዊ መገለጥ ብሎ በሚጠራው አስተምህሮ እየተካው ይገኛል፡፡ EWAmh 195.2

    መንፈሳዊ መገለጦች ሙሉ በሙሉ ለእርሱ አገልግሎት የዋሉና በቁጥጥሩ ስር ያሉ በመሆናቸው ዓለምን እርሱ በፈለገው መንገድ ሊያሳምንባቸው ይችላል፡፡ ሰይጣን በእርሱና ተከታዮቹ ላይ የሚፈርደውን መጽሐፍ ዳግመኛ እንዲያጠላበት የሚያደርግ ሲሆን የሚፈልገውም ይህ እንዲሆን ነው:: የዓለም አዳኝ የሆነው ጌታ ከተራ ስው የዘለለ ማንነት እንዲኖረው ስለማይሻ የየሱስን መቃብር ይጠብቅ የነበረው የሮም ወታደር ቀሳውስቱና ሽማግሌዎቹ በአፉ ላይ ያስቀመጡለትን ሐሰት እንደነዛ ሁሉ በመንፈሳዊ መገለጥ የተታለሉ ምስኪኖችም ይህንኑ በመድገም ስለ አዳኛችን አንዳችም ተአምራዊ ውልደት፣ ሞት እንዲሁም ትንሳኤ እንደሌለ ለማሳየት ይሞክራሉ፡፡ የሱስ እንዳይታይ ከኋላቸው ከሸፈኑት በኋላ የዓለምን ትኩረት ወደ ራሳቸው በመሳብ የሚሠሯቸው ተአምራቶችና የሐሰት ድንቃድንቆች የሱስ ከሠራቸው ሥራዎች ሁሉ የላቁ እንደሆኑ ይለፍፋሉ፡፡ ይህ ሲሆን በስሜት ውስጥ በመዘፈቅ በሰይጣን ወጥመድ ውስጥ የወደቀው ዓለም በደኅንነት ውስጥ እንዳለ ሆኖ ስለሚሰማው ሰባቱ መቅሰፍቶች እውኪወርዱ ድረስ አስፈሪውን ስህተት ለይቶ አይገነዘብም: EWAmh 196.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents