Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ቀደምት ጽሑፎች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    40—የክርስቶስ ስቅለት

    የእግዚአብሔር ልጅ በሰዎች ይሰቀል ዘንድ በእጃቸው ተላልፎ ተሰጠ፡፡ ያሸናፊነት ኸት እያሰሙ ውዱን አዳኝ እንዲወገድ አደረጉ፡፡ እርሱ በደ ረሰበት ድብደባ፣ በፈሰሰው ደም እንዲሁም በድካምና ህመም ብዛት ዝሎ ሳለ፤ ብዙም ሳይቆይ የሚሰቀልበትን ከባድ መስቀል እንዲሸከም ተደርጎ ነበር፡፡ የሱስ ከነበረው ሸክም ብዛት ዝሎ ነበር፡፡ መስቀሉ ሦስት ጊዜ በትከሻው ላይ ቢደረግም ነገር ግን ሦስተጊዜ ዝሎ ነበር፡፡ ክርስቶስን መቀበሉን በይፋ ያላስታወቀ ነገር ግን ተከታዩ የነበረን አንድ ሰው ያዙና መስቀሉን አሸከሙት፡፡ እርሱም መስቀሉን የሱስ እስከሚሰቀልበት ስፍራ ድ ረስ ተሸክሞ ሄደ፡፡ መላእክት ከስፍራው በላይ ባለው ሰማይ ይሰፉ ነበር፡፡ ብዛት ያላቸው የየሱስ ደቀ መዛሙርት በኃዘንና በመራር ለቅሶ ተከትለውት ወደ ቀራንዬ አመሩ ከጥቂት ቀናት በፊት የሱስ በታላቅ ክብር ወደ የሩሳሌ ም ሲገባ ልብሶቻቸውን አንጥፈውና የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው እየጮኹ «ሆሳእና በአርያም ክብር ይሁን!» እያሉ መከተላቸውን አስታወሱ፡፡ በዚያን ወቅት እርሱ መንግሥቱን በመውሰድ በመላው እስራኤል እንደሚነግሥ አስበው ነበር፡፡ አሁን ግን ያ ሁሉ ትዕይነት ተቀየረ! ይሆናል ብለው ተስፋ አድረገውት የነበረው ነገር--ብን ብሎ ጠፋ! አሁን ልባቸው በሐሴት ተሞልቶና አስደሳች ተስፋዎችን ሰንቀው ሳይሆን ነገር ግን በፍርሃት ተሞልተውና በተስፋ መቁረጥ እየተንከላወሱ በዝግታ ሊሞት ያለውንና ውርደት የደ ረሰበትን ትሑቱን የሱስ ተከተሉት፡፡ EWAmh 122.1

    በዚያ ስፍራ የየሱስ እናት ነበረች ልቧ ምን ያህል በኃዘን እንደተወጋ ከአፍቃሪ እናት ውጪ ማንም ሊረዳው አይችልም፡፡ እርሷም እንደ ደቀ መዛሙርቱ ክርስቶስ አስደናቂ ተአምራት በማድረግ እራሱን ከገዳዮቹ ያድናል ብላ ተስፋ ከማድረግ ውጪ በመስቀል ላይ ተቸንክሮ ሥቃይ ይደርስበታል ብቻ አልጠበቀችም: ሆኖም ወደዚያ የሚወስደው አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቆ የሱስ በመስቀል ላይ እንዲጋደም ተደርጎአል፡፡: መዶሻና ምስማሮች መጥተዋል፡፡ ይህን የተመለከቱት የደቀ መዛሙርቶቹም ልቦች ዝለዋል፡፡ የየሱስ እናት ልትቋቋመው ከምትችለው በላይ በሚመስል ከፍተኛ ኃዘን ውስጥ በመዘፈቅ ጎንበስ ብላለች:: ሆኖም አዳኙ በመስቀል ላይ ከመቸንከሩ አስቀድሞ፤ ለስላሳ በሆኑት በእጁና እግሩ አጥንቶችና ጡንቻዎች ውስጥ ቀድዶ የሚገባውን የምስማር ድምጽ እንዳትሰማ ደቀ መዛሙርቱ ይዘው ከአሰቃቂው ትዕይንት ዘወር አደረጓት፡፡ የሱስ ከሥቃይ ድምጽ ውጪ አንዳተም ማንጎራጎር አላሰማም ነበር፡፡ ፊቱ ገርጥቶአል፣ ትላልቅ የላብ ጠብታዎች በቅንድቡ ላይ ነበሩ፡፡ የእግዚአብሔር ልጅ እያለፈ በነበረበት ሥቃይ ሰይጣን ቢከብርም ነገር ግን የደኅንነትን እቅድ ለማጨናገፍ ያደ ረገው ጥረት ከንቱ በመሆን የዚህን ዓለም ግዛቱን አጥቶአል-በመጨረሻ መጥፋቱም የተረጋገጠ ሆኗል፡፡ EWAmh 122.2

    መስቀሉ መሬት ላይ እንደተጋደመ የሱስን ቸንክረው ከጨረሱ በኋላ መስቀሉን በተዘጋጀው የመትከያ ስፍራ ውስጥ ለመክተት በብርቱ ኃይል ሲያነሱት የየሱስ ሥጋ በመቀደድ የማያባራ ሥቃይ ተፈጠረበት፡፡ የየሱስን ሞት በተቻለ መጠን አስነዋሪ ለማድረግ በማሰብ በጎንና በጎኑ ሁለት ሌቦች እንዲስቀሉ ተደርጎ ነበር፡፡ ሌቦቹ የተቸነከሩት በብዙ ኃይልና ጉልበት ሲሆን ነገር ግን የሱስ ያለ ምንም ትግል እራሱን በትህትና አሳልፎ ከመስጠት በቀር፤ እጆቹን በመስቀሉ ላይ እንዲዘረጋ ማንም አላስገደደውም ሌቦቹ የሰቀሏቸውን ሰዎች ሲሳደቡና ሲራገሙ አዳኙ ግን በብዙ የህመም ስሜት «አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው» በማለት ለጠላቶቹ ጸለየ፡፡ ክርስቶስ ያለፈበት ጎዳና የአካላዊ ሥቃይ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን የዓለም ኃጢአት በሙሉ በላዩ ላይ ነበር:: EWAmh 123.1

    የሱስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሳለ በዚያ ያልፉ የነበሩ በኃይል እየተሳደቡና ለንጉሥ ሰላምታ እንደሚሰጡ በማጎንበስ «ቤተመቅደስን አፍርስህ በሦስት ቀን ውስጥ የምተሠራው፤ እስቲ ራስህን አድን! የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ በል ከመስቀል ውረድ!» በማለት ያላግጡበት ነበር፡፡ ‹‹የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ» የተሰኘውን ኃረግ ሰይጣን የሱስን በምድረበዳ በፈተነው ጊዜ ተጠቅሞበታል፡፡ የካኅናት አለቆች «ሌሎችን አዳነ፧ እራሱን ግን ማዳን አይችልም! የእስራኤል ንጉሥ ከሆነ አሁን ከመስቀል ይውረድ እኛም እናምንበታለን» በማለት በየሱስ ላይ ያሾፉ ነበር እነዚህ የኃይማኖት መሪ ዎች «የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ እራሱን ያድን” በማለት ሲዘብቱበት የታዘቡ በስፍራው ይሰፍፉ የነበሩ መላእክት ሊያድኑት ተመኝተው የነበ ረ ቢሆንም ነገር ግን ያን እንዲያደርጉ አልተፈቀደላቸውም:፡፡ ምክንያቱም የእርሱ ተልዕኮ ዓላማ ገና ፍጻሜ አላገኘም ነበር EWAmh 123.2

    የሱስ በመስቀል ላይ በቆየባቸው በእነዚያ ረጅም የህማም ሰዓታት ውስጥ ሆኖ እናቱን አልረሳትም ነበር፡፡ ማርያም ከልጇ እራቅ ብላ መቆየት ስላልሆነላት ወደዚህ አስፈሪ ትዕይንተተመልሳ መጥታለች፡፡ የሱስ በመጨረሻ ላይ የሰጠው ትምህርት ስለ ሰብዓዊ ርኀራኄ ነበር፡፡ የሱስ ልቧ በሐዘን ወደ ተሰበረው እናቱ ተመለከተና የሚወደውን ደቀ መዝሙር ዮሐንስን አየው:፡፡ ከዚያም እናቱን «አንቺ ሴት ሆይ ልጅሽ ይኸው! አላት»፡፡ ዮሐንስንም «እናትህ ይህችው’ አለ» ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዮሐንስ ወደ ቤ ቱ ወሰዳት፡፡ EWAmh 123.3

    የሱስ በደረሰበት ህማም ተጠማ፡፡ ከዚያም ከሐሞት ጋር የተቀላቀለ የወይን ጠጅ እንዲጠጣው ሰጡት እርሱ ግን ቀምሶ ሊጠጣው አልፈቀደም መላእክት የተወዳጁ አዛዣቸው ህማም መመልከት ከሚችሉት በላይ ሲሆን ፊታቸውን ሸፈኑ፡፡ ጸሐይ ይህን አስፈሪ ትዕይንት አላይም አለች የሱስ በገዳዮቹ ልብ ውስጥ ፍርሃት የለቀቀውን ቃል ድምጹን ከፍ አድርጎ «ተፈጸመ” ሲል ጮኸ፡፡ ከዚያም የቤተመቅደሱ መጋረጃ ከላይ ወደ ታች ተቀደደ፡፡: ምድር ተናወጠች፤ ዐለቶችም ተሰነጣጠቁ፣ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ፡፡ የሱስ በሞተጊዜ የደቀ መዛሙርቱ የመጨረሻው ተስፋቸው የተሟጠጠ መሰለ:፡፡ አብዛኞቹ ተከታዮቹ ሥቃዩን፣ ሞቱንና የእነርሱ የኃዘን ጽዋ መሙላቱን ተመልክተው ነበር፡፡ EWAmh 124.1

    ሰይጣን የፈጸመውን ድርጊት ያህል ሳይከብር ቀረ፡፡ እርሱ የደኅንነትን እቅድ ለማሰናከል ተስፋ ኣድርጎ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን አምላካዊው እቅድ በጥልቅ መሰረት ላይ የተመሰረተስለነበር ያን ማድረግ አልተቻለውም፡፡ አሁን በክርስቶስ ሞት ምክንያት እርሱ ራሱ በመጨረሻ ላይ መሞት እንዳለበትና መንግሥቱ ለየሱስ እንደሚሰጥ አውቆአል:: ሰይጣን ከመላእክቱ ጋር ጉባዔ ላይ ተቀመጠ፡፡ በእግዚአብሔር ልጅ ላይ አንዳችም ድል ሳይቀዳጅ በመቅረቱ ከዚህ በኋላ ከቀድሞው በላቀ ተከታዮቹን ለማሳት ቁርጥ ሃሳባቸው አደረጉ፡፡ ሰዎች በክርስቶስ መሰዋዕትነት የተገዛላቸውን ደኅንነት እንዳይቀበሉ በሚችሉት. አቅም መከልከል ነበረባቸው:: ሰይጣን በዚህ መልኩ ለራሱ ጥቅም በመንቀሳቀስ አሁንም ሰዎችን ከየሱስ እያራቀ ከእግዚአብሔር መንግሥት በተቃራኒ መሥራት ይችላል፡፡ በክርስቶስ የቀረበላቸውን ደኅንነት ለመቀበል ፈቃደኛ ያልሆኑ በገዛ ኃጢአታቸው መቀጮ ሲሰቃዩ ነገር ግን እነዚያ በክርስቶስ ደም የተዋጁ በስተመጨረሻ ኃጢአታቸው ተጠራርጎ በመጀመሪያው የኃጢአት ጠንሳሽ ላይ ይውላል፡፡ እርሱ ቅጣታቸውን ይሸከም ዘንድ የግድ ነው፡፡ EWAmh 124.2

    የክርስቶስ ህይወት አንዳችም ምድራዊ ሐብት፣ ክብር ወይም ታይታ አልነበረበትም፡፡: በእርሱ ዘንድ የነበረው ትህትናና እራስን መካድ በቀሳውስቱና ሽማግሌዎች ዘንድ ይስተዋል ከነበረው ኩራትና እራስ ወዳድነት ጋር ፈጽሞ የማይነጻጸር ነበር፡፡ የእርሱ እንከን የለሽ ንጽህና በኃጢአታቸው ላይ ያለማቋረጥ ወቀሳ ይሰነዝር ነበር፡፡ እርሱ ትሑት፣ እንከን የለሽና በንጽህና የተሞላ በመሆኑ ቢንቁትም ነገር ግን እነዚህ የናቁት ሁሉ አንድ ቀን በሰማይ ታላቅ ሆኖና ማንም ሊስተካከለው በማይችል በአባቱ ክብር ይመለከቱታል። EWAmh 124.3

    የሰስ ፍርድ በሚጥበት አዳራሽ ውስጥ በነረ ጊዜ ዙሪያውን ደሙን በተጠሙ ጠላቶቹ ተከብቦ ነበር እነዚያ ልባቸው አብልጦ የደነደነና «ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን” እያሉ ይጮኹ የነበሩ ሁሉ በክብር የተሞላ ንጉሥ ሆኖ ይመለከቱታል፡፡ የታረደውና ሕያው ሆኖ የሚኖረው ኃያል ገዥ የድል መዝሙር በሚዘምሩ የሰማይ ሰራዊት ታጅቦ ዳግመኛ በምድር ይለለጻል:: EWAmh 125.1

    ደሃ፣ ደካማና ችጋረኛው ስው በክብር ንጉሥ ፊት ላይ ተፋ፡፡ በአመጸኞች ዘንድ ያስተጋባ በነበረው ጭካኔ የተሞላው ውስጥ አሳፋሪ ስድብ ይሰማ ነበር: መላውን ሰማይ ባስደነቀ መልኩ ያንቋሸሹት፣ የመቱት እንዲሁም ማንኛውንም ዓይነት የጭካኔ ተግባር የፈጸሙበት እነዚህ ሕዝቦች ያን የቀድሞውን ፊት እንደ ቀትር ጸሐይ የሚያበራ ሆኖ ሲመለከቱት ከፊቱ የሚሰወሩበትን መሸሸጊያ ያገኙ ዘንድ ይማጸናሉ፡፡ በዚህን ወቅት እንደ ቀድሞው ጭካኔ የተሞላው የድል ጩኸት ሳይሆን ነገር ግን ስለ እርሱ ዋይ ወይ ይላሉ፡፡ EWAmh 125.2

    የሱስ በመስቀል ላይ የተቸነከሩ የእጆቹ ጠባሳ ያሳያል የእነዚህ ጭካኔ የተሞላባቸው ድርጊት ምልክቶች ለዘላለም ከእርሱ ጋር የሚኖሩ ይሆናሉ፡፡ እያንዳንዱ ምስማር ያሳረፈው ጠባሳ አስደናቂውን የሰው ልጅ ደኅንነት ታሪ ክና የተከፈለውን የከበረ ዋጋ ይናገራል፡፡ የህይወትን ጌታ ጎን በጦር የወጉ ጦሩ የወጋውን ጠባሳ በመመልከት ለሠሩት ሥራ በጥልቅ ኃዘን ያነባሉ፡፡ EWAmh 125.3

    የየሱስ ገዳዮች በመስቀሉ አናት ላይ «የአይሁድ ንጉሥ” በሚል የተጻፈውን በመመልከታቸው በእጅጉ ተበሳጭተው እንዳልነበር አሁን ግን ከእነ ሙሉ ክብሩና ንጉሣዊ ኃይሉ ለመመልከት ይገደዳሉ፡፡ በልብሱና በጭኑ ላይ «የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ» በሚል የተጻፉትን ሕያው ቃላት ይመለከታሉ፡፡ እርሱ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሳለ «አይተን እናምን ዘንድ ይህ ክርስቶስ ይህ የእስራኤል ንጉሥ አስቲ ከመስቀል ይውረድ» እያሉ ያሾፉበት ነበር: ሆኖም በዚያን ጊዜ ከእነ ንጉሣዊ ኃይሉና ሥልጣኑ ሲመለከቱት በእርግጥም የእስራኤል ንጉሥ ለመሆኑ የማንንም ምስክርነት አይሹም፤ ይልቁንም በንጉሣዊ ግርማውና ወደር በማይገኝለት ክብሩ ግራ በመጋባት በአርግጥም «በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ” መሆኑን ለመቀበል ይገደዳሉ፡፡ EWAmh 125.4

    የምድር መናወጥ፣ የዐለቶች መሰነጣጠቅ፣ የምድር በጨለማ መዋጥና የሱስ ሲሞት በታላቅ ድምጽ «ተፈጸመ!» ሲል መጮኹ ጠላቶቹን ረብሾአል፤ ገዳዮቹንም አርበትብቶአል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ በእነዚህ ተገልጠው በተመለከቷቸው ነገሮች ቢደነቁም ነገር ግን ተስፋቸው ከስሞ ነበር፡፡ አይሁዳውያኑ እነርሱንም ጭምር እንዳያጠፏቸው ብርቱ ስጋት አደረባቸ:: ይህ በእግዚአብሔር ልጅ ላይ የታው የከፋ ጥላቻ በእርሱ ብቻ እንደማያበቃ ተሰምቷቸው ነበር ደቀ መዛሙርቱ ለደረሰባቸው ተስፋ መቁ ረጥ አነቡ፡፡ የሱስ ይነግሣል ብለው ተስፋ አድርገው የነበረ ቢሆንም ነገር ግን ይህ ተስፋቸው ከእርሱ ጋር አብሮ ሞተ፡፡ ከደረሰባቸው ኃዘንና ተስፋ መቁረጥ የተነሳ አታሏቸው እንደሆነ ጥርጣሬ ገባቸው፡፡ እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ እናቱም በመሲህነቱ ላይ የነበራት እምነት ዋለለ EWAmh 125.5

    ደቀ መዛሙርቱ በየሱስ ላይ የነበራቸውን ተስፋ ቢቆርጡም ለእርሱ የነበ ው ፍቅር ግን እንዳለ ነበር በመሆኑም አካሉን ወስደው በክብር ለመቅበር የተመኙ ቢሆንም እንዴት ሊያገኙት እንደሚችሉ ግን እርግጠኞች አልነበሩም፡፡ የhርማትያሱ ሐብታምና በአይሁድ ሸንጎ ብርቱ ተጽእኖ የነበ ረው የየሱስ እውነተኛ ደቀ መዝሙር ዮሴፍ በድፍረት በግል ወደ ጲላጦስ በመሄድ የአዳኙን በድን ይሰጠው ዘንድ ለመነው፡፡ ዮሴፍ ከአይሁድ ጥላቻ የተነሳ በግልጽ ለመሄድ አልደፈረም ነበር አይሁድ የክርስቶስ በድን በክብር እንዳያርፍ ለማድረግ ያላስለሰ ጥረት እንድሚያደርጉ ደቀ መዛሙርቱ ፍራቻ ነበራቸው:፡፡ ጲላጦስ ለተጠየቀው እሺታውን በመግለጹ ደቀ መዛሙርቱ የወደመው ተስፋቸው ባስከተው ጥልቅ ኃዘን እንደተሞሉ ህይወት ዐልባውን የየሱስ በድን ከመስቀል ላይ አወረዱ:፡፡ ከዚያም የየሱስን አካል በንጹህ የበፍታ ጨርቅ በጥንቃቄ ከከፈኑት በኋላ አዲስ በተዘጋጀው ከዐለት በተፈለፈለው የዮሴፍ መቃብር ውስጥ አኖሩት፡፡EWAmh 126.1

    ክርስቶስ በምድር ይመላለስ በነበረ ጊዜ ለእርሱ ታማኝ ተከታይ የነበሩ ሴቶች በድኑ በመቃብር ውስጥ አርፎ ትልቅ ድንጋይ ተንከባሎ የመቃብሩን በር እስኪዘጋ ድረስ ይመለከቱ ነበር እንጂ አልሄዱም: ምናልባትም ጠላቶቹ አካሉን ለማግኘት ሙከራ ሊያደርጉ ይችላሉ---በሚል: ነገር ግን በዚህ ዙሪያ ፍርሃት ሊያድርባቸው አይገባም ነበር፡፡ ምክንያቱም የክብር ንጉሥ ከሚገኝበት የእሥር ቤቱ ነጻ የሚሆንበትን ትእዛዝ በመቀበል የበኩላቸውን ድርሻ ያበረክቱ ዘንድ ፧ የመላእክት ሠራዊት የሱስ ያረፈበትን ስፍራ ሊነገር በማይቻል ብርቱ ፍላጎትና ጽናት ይጠብቁ፡፡ EWAmh 126.2

    የክርስቶስ ገዳዮች ከሙታን ተነስቶ እንዳያመልጣቸው ፍራቻ ነበ ረባቸው፡፡ በዚህ የተነሳ መቃብሩ እስከ ሦስተኛው ቀን ድረስ እንዲጠበቅ ትእዛዝ ይሰጥ ዘንድ ጲላጦስን ጠየቁት፡፡ ጥያቄአቸው ተቀባይነት በማግኘቱ የመቃብሩን በር በማኅተም አሽገው ጠባቂ አቆሙበት፡፡ ይህን በማድረጋቸው ደቀ መዛሙርቱ ኣስከሬኑን ሰርቀው ለሕዝቡ ተነስቶአል ብለው ከማስወራት መከላከል እንደሚችሉም አምነዋል፡፡ EWAmh 126.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents