Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ቀደምት ጽሑፎች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    55—የሁለተኛው መልአክ መልእክት

    አብያተክርስቲያናቱ የመጀመሪያውን መልአክ መልእክት ለመቀበል እምቢተኝነታቸውን በገለጹ ጊዜ ሰማያዊውን ብርሃን በመቃወም እራሳቸውን ከአምላካዊው ድጋፍና ምሪት አገለሉ፡፡ እነዚህ ሕዝቦች በገዛ ብርታታቸው በመታመን የመጀመሪያውን መልእክት በመቃወማቸው የሁለተኛውን መልአክ መልክት መመልከት በማይችሉበት ሁናቴ ውስጥ እራሳቸውን ዘፈቁ:: ነገር ግን «ባቢሎን ወደቀች» የተሰኘውን መልእክት የተቀበሉና ጭቆና የደረሰባቸው የእግዚአብሔር ተወዳጆች ቤተክርስቲያንን ትተው ወጡ፡፡ EWAmh 173.1

    በሁለተኛው መልአክ መልእክት መገባደጃ አካባቢ በእግዚአብሔር ሕዝቦች ላይ ከሰማይ የተላከ ታላቅ ብርሃን አንጸባርቆ ተመለከትኩ፡፡ የብርሃኑ ጨረር እንደ ጸሐይ ያንጸባርቅ ነበር፡፡ ከዚያም «ሙሽራው እየመጣ ነው፧ ወጥታችሁ ተቀበሉት!» የሚል የመላአክት ድምጽ ሰማሁ፡፡ EWAmh 173.2

    ይህ ለሁለተኛው መልአክ መልእክት ኃይል የሚሰጥ የእኩለ ሌሊቱ ጩኸት ነበር መላእክት ተስፋ ቆርጠው የነበሩትን ቅዱሳን ለማበረታታትና ከፊታቸው ለነበረው ታላቅ ሥራ ለማዘጋጀት ከሰማይ ተላኩ፡፡ ከፍ ያለ ችሎታ የነበራቸው ይህን መልእክትለመቀበል የመጀመሪያዎቹ አልነበሩም:፡፡ መላእክት ትሑታንና ለእምነታቸው ቀናኢ ወደ ነበሩት በመላአክ ጩኸቱን በኃይል ያስተጋቡ ዘንድ ኃይል ስጧቸው «ሙሽራው እየመጣ ነው፧ ወጥታችሁ ተቀበሉት!» በጩኸቱ ተሳታፊ የሆኑት በመንፈስ ቅዱስ ኃይል መልእክቱን በፍጥነት በማስተጋባት ተስፋ ቆርጠው የነበሩ ወንድሞቻቸውን አበረታቱ፡፡ ሥራው በሰው ጥበብና ዕውቀት ሳይሆን ነገር ግን በእግዚአብሔር ኃይል በመከናወኑ ጩኸቱን የሚሰሙ ቅዱሳን ሳያመነቱ ይቀላቀሉ ነበር: ይህን መልእክት በመጀመሪያ የተቀበሉት በጣም መንፈሳውን ሰዎች ሲሆኑ ነገር ግን ቀደም ብለው በሥራው ተሳታፊ የነበሩ መልእክቱን ተቀብለው «ሙሽራው እየመጣ ነው ወጥታችሁ ተቀበሉት! ብለው ጩኸቱን ለማስተጋባት የመጨረሻዎቹ ነበሩ፡፡ EWAmh 173.3

    ከሁለተኛው መልአክ መልእክት ቀደም ብሎ ብርሃን በእያንዳንዱ የምድሪቱ ክፍል በመሰጠቱ በጩኸቱ በሺህ የሚቆጠሩ ልቦች ቀለጡ:፡፡ መልእክቱን ይጠባበቁ የነበሩ የእግዚአብሔር ሕዝቦች ሙሉ ለሙሉ እስኪነሳሱ ድረስ ጩኸቱ ከከተማ ወደ ከተማ እንዲሁም ከመንደር ወደ መንደር ተሰራጨ፡፡ መልእክቱ በብዙ ቤተክርስቲያኖች አንዲሰጥ ባለመፈቀዱ ሕያው ምስክር የነበራቸው ብዙዎች የወደቁትን ቤተክርስቲያናት እየተዉ ወጡ፡፡ በእኩለ ሌሊቱ ጩኸት አስደናቂ ሥራ ተሠርቶአል፡፡ መልእክቱ የእያንዳንዱን ልብ የሚመረምርና አማኞች ሕያው የሆነውን ተሞክሮ ለራሳቸው እንዲፈልጉ የሚመራ ነበር፡፡ እነዚህ ህዝቦች እያንዳንዱ ሰው እራሱን ችሎ ከመቆም ውጪ አንዱ በሌላው ላይ መመርኮ ዝ እንደማይችል ያውቁ ነበር፡፡ EWAmh 173.4

    ቅዱሳኑ ጾም ጸሎት እያደረጉ የጌታቸውን መገለጥ በጉጉት ይጠባበቁ ነበር፡፡ ከፍተኛ አኃዝ የነበራቸው ህዝቦች በሰይጣን መንፈስ በመመራት ለመልእክቱ ያሳዩትን ተቃውሞ ተከትሎ አንዳንድ ኃጢአተኞች መጪውን ጊዜ በፍርሃት እንዲመለከቱ ሆነው ነበር፡፡ የመልእክቱ ተቃዋሚዎች «ቀኑን ወይም ሰዓቱን» ማንም አያውቀውም እያሉ በተደጋጋሚ በመናገር ያሾፉ ነበር፡፡ ተቃዋሚዎች በሰይጣን መሰናከያ ላይ ተጣብቀው ይቀሩ ዘንድ ክፉ መላእክት ልቦቻቸውን በማደንደን እያንዳንዱን ከሰማይ የሚላክ ጨረር እንዲቃወሙ አደረጓቸው፡፡ ክርስቶስን እንሻለን የሚሉ ብዙዎች በመልእክቱ ድርሻ አልነበራቸውም፡፡ መልእክቱን በተቀበሉት ህይወት የተመለከቱት አምላካዊ ክብር፣ ትህትና እና ጥልቅ እራስን አሳልፎ መስጠት እንዲሁም ተጨባጭነት ያላቸው መጠነ ሰፊ መረጃዎች እውነትን እንዲቀበሉ መንስዔ ቢሆኗቸውም ነገር ግን ባለመለወጣቸው ለጌታቸው ዳግም ምጽአት ዝግጁ አልነበሩም፡፡ EWAmh 174.1

    በቅዱሳኑ ላይ ቅድስና የተሞላው ብርቱነት አርፎባቸው ነበር፡፡ በያሉበት በጸሎት ጸንቶ የመቆም መንፈስም ይስተዋልባቸው ነበር፡፡ መልእክቱን የተቀበሉ ልቦች ከደኅንነት ምንጭ ከፍ ያለውን አቅርቦት ይቀበሉ ዘንድ መላእክት እነርሱን በመንካትና ዐይኖቻቸውን ከምድራዊው ነገር አንስተው ከፍ ያለውን ነገር እንዲመለከቱ በመርዳት ውጤቱን ጥልቅ በሆነ ፍላጎት ይከታተሉ ነበር የእግዚአብሔር ሕዝቦች በአምላካቸው ዘንድ ተቀባይነት አግኝተዋል፡፡ የየሱስ አምሳል በእነርሱ በመንጸባረቁ ይህ ጌታቸው በደስታ ይመለከታቸው ነበር፡፡ እነዚህ ወገኖች ሙሉ ለሙሉ በመለየትና መስዋዕትነት በመክፈል የማይሞተውን አካል ለብሰው ለመቀየር ተስፋ አድርገው ነበር፡፡ ነገር ግን ያስቡት ሳይሆን በመቅረቱ ከፍተኛ ኃዘንና ተስፋ መቁረጥ ደረሰባቸው:: ጌታ በዳግም ምጽአቱ ተገልጦ ያድነናል ብለው ተስፋ ያደረጉት ጊዜ በማለፉ አሁንም የሚገኙት በምድር ላይ ሆነ:፡፡ እነዚህ ሕዝቦች ለሰማይ ጥልቅ የሆነ ፍቅር በማሳየት ጣፋጭ በሆነ ተስፋ የማይሞቱ ሆነው እንደሚለወጡ ተስፋ ቢያደርጉም ነገር ግን ተስፋቸው እውን አልሆነም:: EWAmh 174.2

    መልእክቱን ባልተቀበሉ በብዙዎች ላይ የነበረው ፍርሃት በአንድ ጊዜ ሊወገድ ባለመቻሉ ወዲያውኑ ተስፋ በቆረጡት ላይ ድል ማግኘት አልቻሎም:: ነበር: ነገር ግን በእነርሱ ላይ አንዳችም ዓይነት አምላካዊ ቁጣ ሲወርድ ባለመስተዋሉ እነዚህ ሕዝቦች ተሰምቶአቸው ከነበረው ፍርሃት በማገገም ዳግመኛ በማሾፍ ተግባራቸው ገፉበተ፡፡ የእግዚአብሔር ሕዝቦች አሁንም ተፈተኑ፡፡ ዓለም ተሳለቀባቸው፣ አፌዘባቸው:: የየሱስን ዳግም ምጽኣት ያለአንዳች ጥርጣሬ የተቀበሉ---በመቃብር ያሉ ጻድቃን ሲነሱ፣ በህይወት ያሉ ጻድቃን ሲቀየሩና አምላካዊውን መንግሥት ለዘላለም ሲወርሱ ለማየት በመመኘት በክርስቶስ የመቃብር ስፍራ ተገኝተው ጌታዬን ወስደውታል የት እንዳኖሩትም አላውቅም” እንዳሉት ደቀ መዛሙርት ዓይነት ስሜት ተሰምቷ ቸው ነበር: EWAmh 174.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents