Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ቀደምት ጽሑፎች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    14—መልዕክተኞቹ

    ጌታ በየስፍራው ተበታትነው የሚገኙትን ገና ወደ ወቅታዊው እውነት ብርሃን ያልመጡ ዕንቁዎችን ሁናቴና የሚያሻቸውን ነገር በተደጋጋሚ በራእይ ሰጥቶኛል፡፡ መልእክትኞቹ ለእነዚህ ወገኖች ብርሃን ይሰጡ ዘንድ በተቻላቸው ፍጥነት ወደ እነርሱ መገስገስ ነበረባቸው ብዙዎች በዙሪያችን ያሉ የሚፈልጉት ብቸኛ ነገር ቢኖር ጭፍን አመለካከታቸው እንዲወገድላቸውና አሁን የምንገኝበት በቃሉ ላይ ያለን አቋም ግልጽ ሆኖ እንዲቀርብላቸው ነው፡፡ ይህ ከሆነ ወቅታዊውን እውነት በደስታ ይቀበላሉ፡፡ መልእክትኞች ለነፍሳት ተገቢውን ዋጋ በመስጠት ሊፈልጓቸው ይገባል፡፡ ህይወታቸው በጽኑ መርኅና በሥቃይ መንፈስ የተሞላ ሲሆን የከበረውና ብዙውን ጊዜ ይቆስል የነበረው የክርስቶስ ተጽእኖ ያርፍባቸዋል: ምድራዊውን ፍላጎትና ምቾት ወደ ጎን በማለት---የእነዚህ ሰዎች ተቀዳሚ ዓላማ ሊሆን የሚገባው ወቅታዊው እውነት ወደ ፊት እንዲገሰግስ ማድረግና የጠፉትን ነፍሳት ማዳን ነው፡፡ EWAmh 43.1

    መልእክትኞቹ ታላቅ ሽልማት ይጠብቃቸዋል፡፡: እነዚያ በመጨረሻ ላይ በእነርሱ መልእክት የዳኑት ነፍሳትም ዘውዶቻቸውን በአናቶቻቸው ላይ በመድፋት ከዘላለም እስከ ዘላለም እንደ ከዋክብት እያበሩ ይኖራሉ፡፡ ነፍሳት ከዚህ እውነት ጋር በፍቅር በመውደቅ ቅድስናን በማግኘታቸው፣ በበጉ ደም ታጥበው ለእግዚአብሔር የተዋጁና ሊገመት የማይችል ባለጸጋ ሆኑ መልእክትኞቹ እውነትን ከነንጽህናውና ከነውበቱ በማቅረብ ማድረግ ይችሉ የበሩትን ሁሉ በማድረጋቸው እነሆ ፍጻሜ ለሌለው ዘመን በቅድስናቸው ሐሴት እያደረጉ ይኖራሉ፡፡ EWAmh 43.2

    የመንጋው እረኞች መጽሐፍ ቅዱስ ይደግፏቸዋል ብለው የሚያስቧቸውንና አስፈላጊ ያሏቸውን አዳዲስ እውነቶች ከመደገፋቸው አስቀድሞበነጥቦቹ ላይ መተማመን ያላቸውን፣ሁሉንም መልእክቶች ሲሰጡ አብረው የነበሩትንና በወቅታዊው እውነት ዙሪያ ጠንካራ አቋም ያላቸውን ሊያማክሩ እንደሚገባ ተመልክቻለሁ፡፡ ይህ ሲሆን እረኞች ፍጹም ውህደት ይኖራቸዋል---የእነርሱ ህብረት ቤተክርስቲያኒቱን ዘልቆ የሚሰማ ይሆናል፡፡ ይህ ኣካሄድ ቅሬታ ሊፈጥር የሚችለውን መከፋፈል በማስወገድ በከበረው መንጋ መሃል የመከፋፈልና ያለ እረኛ የሚበተንን መንጋ አደጋ ያስቀራል:፡፡ EWAmh 43.3

    እንዲሁም እግዚአብሔር ለሥራው የሚጠቀማቸው መልእክትኞች እንደነበሩት ነገር ግን ዝግጁ እንዳልነበሩ ተመልክቻለሁ:፡፡ እነርሱ እንደ እግዚአብሔር መልእክትኝነታቸው በመንጋው ላይ መልካም ተጽእኖ ለማሳደር የማይችሉ፣ በእጅጉ የቀለሉና የሥራው ክብደት ያልተሰማቸው እንዲሁም ነፍሳት ያላቸውን ዋጋ ያላስተዋሉ ነበሩ፡፡ መልአኩ «እናንት የጌታን መልእክት የምትሸከሙ ንጹህ ሁኑ፤ እናንት የጌታን መልእክት የምትሸከሙ ንጹህ ሁኑ» በማለት ተናገረ: እነርሱ እራሳቸውን ሙሉ ለሙሉ ለእግዚአብሔር ካልሰጡና አሁን ተበታትነው ለሚገኙት መንጋዎች እየተሰጠ ያለው የምህረት መልእክት አስፈላጊነትና ክብደት ካልገባቸው በቀር ክንውን ቢኖራቸውም እንኳ በእጅጉ አነስተኛ ነው ለሥራው በእግዚአብሔር ያልተጠሩ አንዳንዶች መልእክቱን ይዘው ለመሄድ በእጅጉ ፈቃደኞች ናቸው:፡፡ ነገር ግን የሥራውና የአንዲህ ዓይነቱ ኃላፊነት ክብደት ቢሰማቸው ወደ ኋላ በመመለስ ከሐዋርያው ጋር «ለእነዚህ ነገሮች ብቁ የሆነው ማን ነው?” ብለው በጠየቁ ነበር እነዚህ ሰዎች ሥራውን ይዘው ወደፊት ለመገስገስ ፈቃደኞች የሆኑበት አንዱ ምክንያት እግዚአብሔር የኃላፊነቱን ሸክም በላያቸው ባለማኖሩ ነው፡፡ የመጀመሪያውንና የሁለተኛውን መልአክ መልእክት የሰበኩ ሁሉ የሦስተኛውን ላይሰብኩ ይችላሉ፡፡ መልእክቱን ሙሉ ለሙሉ ከተጠማጠሙበት በኋላ እንኳ አንዳንዶች ብዙ ስህተትና ግራ መጋባት ውስጥ ገብተዋል፡፡ በዚህም የራሳቸውን ነፍስ ከማዳን ውጪ ሌ ሎችን መምራት ቢጀምሩ ለእነዚህ ሰዎች መውደቅ መንስኤ ይሆናሉ፡፡ እንዲሁም ቀደም ባለው ጊዜ በአክራሪነቱ ጎራ ጠልቀው ተጉዘው የነበሩ አንዳንዶች አሁን እግዚአብሔር ሳይልካቸው እነርሱ ግን የፊተኞች እንደሚሆኑ ተመልክቻለሁ፡፡ እነዚህ ሰዎች ካለፈው ስህተታቸው ሳይጠሩና ስህተቱን ከእውነት ጋር ቀላቅለው እንደያዙ የእግዚአብሔርን መንጋ ለመመገብ ያስባሉ፡፡ እናም ይህን ሁሉ አልፈው ወደፊት መግፋት ቢችሉ መንጋው---ታማሚ፣ ጥፋትና ሞት የሚከተለው ይሆናል እነርሱ ከስህተቶቻቸው ሁሉ ነጻ እስኪሆኑ ካልጠሩና ካልተለዩ ጭራሹኑ ወደ ሰማያዊው መንግሥት ላይገቡ ይችላሉ፡፡ መልእክትኞቹ በእውነት ውስጥ ከሚገኙት ውጪ በጥራዝ ነጠቅ ስህተቶችና በአክራሪነት ጎራ ውስጥ የነበሩትን ለመዳኘት የሚያስችላቸው በራስ መተማመን ላይኖራቸው ይችላል፡፡ እንዲሁም አንዳንዶች እራሳቸውን በእግዚአብሔር ፊት ማቅረብ ከመቻላቸው አስቀድመው ብዙ መማርና መሥራት ሲኖርባቸው ነገር ግን ገና ወቅታዊውን እውነት ተቀብለናል እንዳሉ በችኮላ ወደ ሥራው ይገቡ ዘንድ በብዙዎች ጉትጎታ ይደረግባቸዋል፡፡ EWAmh 43.4

    ሁሉም ዓይነት አክራሪነት በማንኛውም ጊዜ ገና እንዳቆጠቆጠ በጥንቃቄ የሚጠባበቁና የሚመረምሩ መልእክትኞችን አስፈላጊነት ተመልክቼ ነበር EWAmh 44.1

    ሰይጣን በማንኛውም አቅጣጫ እየገፋ ይገኛል፡፡ ተግተን ካልተጠባበቅንና እርሱ የሚጠቀምባቸውን መሣሪያዎችና ወጥመዶች 0ይኖቻችንን ከፍተን ካልተመለከትን እንዲሁም የእግዚአብሔርን የጦር ትጥቅ ካልለበስን፤ ከክፉው የሚሰነዘረው ፍላጻ ይጎዳናል፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ አያሌ የከበሩ እውነቶችን ብናገኝም ነገር ግን አሁን ለመንጋው የሚያሻው «ወቅታዊ እውነት» ነው፡፡ ከወቅታዊው እውነት አስፈላጊ ነጥቦች አፈትልከው በመውጣት መንጋውን በአንድነት ለምራትና ነፍስን ለመቀደስ በማያስችሉ ያልተቀመሩ ርዕሰ ነጥቦች ስር የመተዳደርን አደጋ በአገልጋዮች ላይ ተመልቻለሁ:: EWAmh 45.1

    ነገር ግን እንደ---መቅደሱ እና 2300 ቀናት እንዲሁም የእግዚአብሔር ትእዛዛትና የየሱስ እምነት---ርዕሰ ነጥቦች ያለፈውን የዳግም ምጽአቱን እንቅስቃሴ ለመግለጽ፣ የአሁኑን አቋማችንን ለማሳየት፣ ጥርጣሬ ለገባቸው እምነታቸውን ለማጽናትና በክብር ለተሞላው የወደፊቱ ማንነት ማረጋገጫ ለመስጠት ያስችሉ ዘንድ ፍጹም ሆነው የተቀመሩ ናቸው:: በተደጋጋሚ ያየኋቸው እነዚህ ነገሮች መልእክትኞች ሊጸኑባቸው የሚገቡ ዐበይት ርዕሰ ነጥቦች ናቸው፡፡ EWAmh 45.2

    የተመረጡት የጌታ መልእክትኞች እያንዳንዱ እንቅፋት ከመንገዳቸው እስኪወገድ የሚጠብቁ ከሆነ ብዙዎቹ እነዚያን ተበታትነው የሚገኙ መንጋ ዎች ፍለጋ ሊወጡ አይችሉም: እነርሱን ከተግባራቸው ለማስቀረት ሰይጣን አያሌ መቃወሚያዎች ሊያቀርብላቸው ይችላል: ሆኖም ለእርሱ ክብርና ለእነርሱ መልካም እስከሆነ ድረስ---ለራሱ ሥራ የጠራቸውን ጌታ በማመን በእምነት ሊወጡ ይገባል፡፡ ይህን ሲያደርጉ መንገዱን በፊታቸው ወለል አድርጎ ይከፍተዋል፡፡ ታላቁ መምህርና ምሳሌያችን የሱስ ጎኑን የሚያሳ ረፍበት ስፍራ እንኳ አልነበረውም፡፡ ህይወቱ በከባድ ሥራ፣ ሐዘንና ሥቃይ የተሞላው---እርሱ እራሱን ለእኛ ´ሰጠን፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ይታረቁና ከክርስቶስ ጋር በክብር ይነግሡ ዘንድ ልመናቸውን በማቅረብ ተስፋ ለሚያደርጉ ሁሉ በዚህ ምድር የእርሱ ሥቃይ ተካፋይ እንደሚሆኑ መጠበቅ ይኖርባቸዋል «በእንባ የሚዘሩ በእልልታ ያጭዳሉ፡፡ ዘር ቋጥረው እያለቀሱ የተሰማሩ፧ ነዶአቸውን ተሸክመው እልል እያሉ ይመለሳሉ” (መዝ. 126:5-6):: EWAmh 45.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents