Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ቀደምት ጽሑፎች - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    15—የአውሬው ምልክት

    ሰኔ 27 / 1850 ዓ.ም. በተመለከትኩት ራእይ መልአኩ «ጊዜው እያበቃ እንደመሆኑ የተወዳጁን የየሱስ ገጽታ እያንጸባረቃችሁ ነውን?» በማለት ጠየቀ፡፡ ከዚያም ወደ ምድር እንድመለከት ሆንኩና ዘግይተው የሦስቱን መላእክት መልእክት የተቀበሉት ሊያደርጉ ይገባቸው ስለነበረው ዝግጅት ተመለከትኩ፡፡ በመቀጠል መልአኩ «ተዘጋጁ፣ ተዘጋጁ፣ ተዘጋጁ፡፡ ከዚ5 ቀደም ሞታችሁ የማታውቁትን ታላቅ ሞት ለዓለም መሞት ይኖርባችኋል” አለ፡፡ እነዚህ ሕዝቦች ሊሠሯቸው የሚገቡ ታላላቅ ሥራዎች እንደነበሩ ተመለከትን፡፡ ነገር ግን የነበራቸው ጊዚ በእጅጉ አነስተኛ ነበር EWAmh 46.1

    ከዚያም መጠለያ በሌላቸው ላይ ሰባቱ የመጨረሻ መቅሰፍቶች በቅርቡ እንደሚወርዱባቸው ብመለከትም ዓለም እነዚህን መቅሰፍቶች ሊዘንቡ ካሉ ታላላቅ የዝናብ ጠብታዎች አግዝፎ አልተመለከታቸውም ነበር፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣ የሆነውን አስፈሪውን የሰባቱን መቅሰፍቶች ትዕይንት በጽናት የምመለከትበት ድፍረት ተሰጠኝ፡፡ የእግዚአብሔር ቁጣ በእጅጉ አስፈሪ መሆኑን በመመልከት እርሱ በቁጣ እጁን ወደፊት ወይም ወደ ላይ ቢዘረጋ መላው የምድር ሕዝቦች ከዚህ ቀደም እንዳልነበሩ ይሆናሉ ወይም በማይድኑ ቁስሎችና መቅሰፍቶች ይመታሉ፡፡ በዚህም በእነዚህ አሰቃቂ ነገሮች ከመጥፋት ውጪ አንዳችም መዳኛ አያገኙም፡፡ ፍርሃት ስለያዘኝ ፊቴን በመልአኩ ላይ ደፍቼ ይህን በእጅጉ አስፈሪ ትዕይንት ከእኔ እንዲያስወገድ ወይም እንዲሸሸግ ለመንኩት፡፡ በመቀጠል ቃሉ እግዚአብሔርን በማያምኑና ለአውሬውና ለምስሉ ለሚሰግዱ የአውሬውን ምልክት በግንባሮቻቸውና በእጆቻቸው ላይ በሚቀበለት ላይ ይወርዳሉ በማለት ከተናገራቸው ከእነዚህ መቅሰፍቶቹ እንዴት ማምለጥ እንደሚገባ ለማወቅ የሚረዳንን---ከዚህ በፊት አስተውዬው የማላውቀውን የእግዚአብሔርን ቃል በጥንቃቄ የመመርመር አስፈላጊነት ተረዳሁ: እንደነዚህ ዓይነት በእጅጉ አስፈሪ ማስጠንቀቂያዎችና ኩነኔዎች ቀርበው ሳለ ማንም ቢሆን የእግዚአብሔርን ሕግ መተላለፉና ቅዱስ ሰንበቱን መርገጡ ለእኔ በጣም አስገራሚ ነበር፡፡ EWAmh 46.2

    ጳጳሳዊው ሥርዓት ሰንበትን ከሳምንቱ ሰባተኛ ቀን ወደ ሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ቀይሮታል፡፡ ሥርዓቱ ሰው ፈጣሪውን እንዲያስታውስ የተሰጠውን ብቸኛ ትእዛዝ ለመቀየር በማሰብ ይህንኑ አደረገ የሥርዓቱ ቁንጮ ከአስርቱ ትእዛዛት አንዱ የሆነውን ትእዛዝ በመቀየር በዚህም እራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ለማድረግ ወይም ከእግዚአብሔር በላይ ከፍ ከፍ ለማለት አሰበ፡፡ ጌታ የማይለወጥ በመሆኑ ሕጉም እንዲሁ ዘላለማዊና የማይለዋወጥ ነው፡፡ ነገር ግን ጳጳሳዊው ሥርዓት ፍጹም የሆነውን ሕጉን፣ የቅድስናውን መርኅ፣ አምላካዊውን ፍትሕና በጎነት ለመለወጥ በማሰብ እራሱን ከእግዚአብሔር በላይ ከፍ ከፍ አደረገ፡፡ የእግዚአብሔርን የተቀደሰ ቀን ከእግሮቹ ሥር በመረጋገጥ በዚህ ዕለት ምትክ ከስድስቱ የሥራ ቀናት አንዱ የሆነውን ቀን በገዛ ሥልጣኑ ሰየመ:፡፡ መንግሥታት ሁሉ አውሬውን በመከተል በየሳምንቱ በእግዚኣብሔር የተቀደስ ጊዜ ላይ ዝርፊያ ፈጸሙ፡፡ ጳጳሳዊው ሥርዓት በእግዚአብሔር ቅዱስ ትእዛዝ ላይ ጥሰት ቢፈጽምም ነገር ግን ይህ ጥሰት በእግዚአብሔር ሕዝቦች አማካኝነት ሙሉ ለሙሉ ወደ ቀድሞ ስፍራው የሚመለስበት ጊዜ እንደሚመጣ ተመልቻለሁ፡፡ EWAmh 46.3

    ተበታትነው የሚገኙትን ሕዝቦቹን እግዚአብሔር ስለ ምህረቱ ሲል ይሰበስባቸው ዘንድ ልመናዬን በመላእኩ ፊት አቀረብኩ፡፡ መቅሰፍቶቹ መው ረድ በጀመሩበት ወቅት ቅዱሱን የሰንበት ቀን መሻራቸውን የገፉበት እነዚህ ሰዎች hመጣው አደጋ ለማምለጥ ሰበብ ይሰጡ ዘንድ አፎቻቸውን አይከፍቱም፡፡ መቅሰፍቶቹ እየወረዱ እያሉ የእነዚህ ሰዎች አፎች ይዘጋሉ፡፡ EWAmh 47.1

    ከዚያም ታላቁ ሕግ አውጪ በአምላካዊው ሕግ ላይ ሲያላግጡ ‹‹እርግማን፣ «ሸክም» በማለት ሲጠሩት የነበሩት ሁሉ ፍትሕ ያገኙ ዘንድ ይጠይቃል፡፡ እንደ ብረት ጠንካራ የሆነው የዚህ ሕግ ተፈጥሮአዊ ምንነት በሚሰማቸው ጊዜ መግለጫዎቹ ግልጽ ሆነው ይታዩአቸዋል፡፡ በዚህን ወቅት የእግዚአብሔር ቃል «ቅዱስ፣ ጻድቅና በጎ» በማለት በሚጠራው አምላካዊ ሕግ ላይ በማላገጥ የሠሩትን ኃጢአት ይገነዘባሉ፡፡ ከዚያም የሰማይን ክብርና ለታማኞቹ የተዘጋጀውን ማለቂያ የሌለውን ሐብት ተመለከትኩ፡፡ በዚህ ስፍራ ማንኛውም ነገር ተወዳጅና በግርማ የተሞላ ነው፡፡ መላእክት ተወዳጅ መዝሙር ይዘምራሉ፧ ከዚያም አብረቅራቂ ዘውዶቻቸውን ከአናቶቻቸው ላይ በማንሳት በተወዳጁ የሱስ እግር ስር ይጥሏቸውና ግሩም ጣዕም ባለው ድምጽ «ክብር ይሁን---ሐሌሉያ!” ይላሉ፡፡ እኔም በዚህ ለበጉ በሚቀርብ የምስጋናና የክብር ዝማሬ እነርሱን በመቀላቀል ለእርሱ ምስጋና ላቀርብ አፌን በከፈትኩ ቀጥር በቃላት ልገልጸው የማይቻ ለኝ የክብሩ ስሜት ዙሪያዬን ይከበኝ ነበር፡፡ ሁኔታው ከአእምሮ በላይ በሆነ ዘላለማዊ ክብር የተሞላ ነበር፡፡ መልአኩ «እግዚአብሔርን የሚወዱ ፣ የእርሱን ትእዛዛት የሚጠብቁና እስከ መጨረሻው ታማኝ ሆነው የሚጸኑት ትሩፋን በእርሱ ክብር ደስ ይሰኛሉ ከየሱስ ጋር ለዘላለም ይሆናሉ፣ ከቅዱሳን መላእክትም ጋራ ይዘምራሉ፡፡” በማለት ሲናገር ሰማሁ:: ከዚያም ዐይኖቼ ከእርሱ ክብር ላይ ተነስተው በምድር ወዳሉተትሩፋን ላይ እንዲያርፉ ሆነ: መልአኩም ትሩፋኑን እንዲህ አላቸው ከሰባቱ ሙቅሰፍቶች ተነጥላችሁ ትተርፋላችሁ? እግዚአብሔርን ለሚወዱትና ስለ እርሱ ሥቃይን ለመቀበል ፈቃደኞች ለሆኑ ሁሉ ወዳዘጋጀው ወደ ክብሩ በመግባት በዚያ በመሆናችሁ ደስ ትሰኛላችሁ? ይህ ምርጫችሁ ከሆነ ህያው ተሆኑ ዘንድ ልትሞቱ የግድ ነው:: ተጋጁ፣ ተዘጋጁ፣ ተዚጋጁ:: :ሁን ካችሁ የላቀ ታላቅ ዝግጅት ልታደርጉ ይገባችኋል: ምድሪቱን ባዶዋን ሊያስቀርና ኃጢአተኞኙን ሊያጠፋ የጌታ ቀን በታላቅ ቁጣ ይመጣልና:: ንብረትንም ሆነ ሁሉንም ነር ሕያው መስዋዕት አድርጋችሁ በመሰዊያው ላይ ጣሉ፡፡ ወደ ክብሩ ለመግባት ይህን ሁሉ ማድረግ ይጠይቃል: ሀብታችሁን ሌባ ሊሰርቀው ወይም ዝገተሊበላው በማይችለው በሰማይ አከማቹ:: በሰማይ የክብሩ ተካፋዮች ከሆናችሁ ክርስቶስ በዚህ ምድር የደረሰበት ሥቃይ ተካፋይ ልትሆኑ የግድ ነው:: EWAmh 47.2

    ሰማይን በሥቃይ የምናገኘው ከሆነ ልንገባበት የምንችልበት ርካሽ ስፍራ ነው፡፡ ዕለት ዕለት እራሳችንን በመካድ በእኛ ምትክ የሱስና የእርሱ ክብር ብቻ ያለማቋረጥ እንዲታይ ማድረግ ይኖርብናል ዘግይተው እውነትን የያዙ ሰዎች ለክርስቶስ መሰቃየት ማለት ምን ማለት እንደሆነ ሊያውቁ እንደሚገባ ተመልክቼአለሁ፡፡ እነዚህ ሰዎች አስተዋይና የተሰበሩ ይሆኑ ዘንድ የሚያልፉባቸው አስቸጋሪ ፈተናዎች ይኖራሉ:: በዚህም የነጹና ለሰማይ ገጣሚ በመሆን የሕያው እግዚአብሔርን ማኅተም ይቀበላሉ—የመከራውን ወቅት በማለፍ ንሡን ከነሙሉ ውበቱ ይመለከቱታል—እግዚአብሔር፣ ንጹሃንና ቅዱሳን መላእክት በሚኖሩበት ስፍራ እነርሱም ይኖራሉ:፡፡EWAmh 48.1

    ክብሩን መውረስ እንችል ዘንድ ምን መሆን እንደሚገባን እየተመለከትኩ በመሃል እጅግ የከበረውን ነገር እንወርስ ዘንድ የሱስ ምን ያህል እንደተሰቃየ አየሁ፡፡ የሱስ እኛን ለማበልጸግ የደረሰበትን ድህነትና ሥቃይ በመገንዘብ በፈተና እንዳንወድቅ ነገር ግን በትዕግሥትና በደስታ በመቋቋም ጸንተን እንድንቆም በክርስቶስ ሥቃይ እንጠመቅ ዘንድ ጸለይኩ፡፡ መልአኩ «እራሳችሁን በመካድ ወደፊት ልትገግሱ ይገባል» በማለት ሲናገር ሰማሁ፡፡ አንዳንዶቻችን እውነትን ለማግኘትና ደረጃ በደረጃ ወደፊት እንዲራመድ የማድረግ ጊዜ ነበረን:፡፡ ይህ እኛ ወደፊት ይዘነው የተጓዝነው እያንዳንዱ እርምጃ ቀጣዩን እንቅስቃሴ ወደፊት እናስኬድ ዘንድ ብርታት ሆኖን ነበር፡፡ አሁን ግን ጊዜው እየተሟጠጠ ስለነበር እኛ ለዓመታት ስንማራቸው የነበሩትን ነገሮች እነርሱ በጥቂት በወራት ሊማሯቸው ያስፈልጋል ደግሞም እነዚህ ሰዎች አያሌ ሊማሩ የማያስፈልጓቸው እንዲሁም ደግመው መማር የሚኖርባቸው ነገሮች ይኖራሉ:፡፡ የአውሬውን ምልክትና የእርሱ የሆነውን ምስል የማይቀበሉ አዋጁ ሲወጣ የሚሉትን ነገር አሁኑኑ--- በጭራሽ ለአውሬው ድርጅት አንሰግድም በማለት ሊወስኑ የግድ ነው:: EWAmh 48.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents