Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የአድቬንቲስት ቤት - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ አምስት—ኃይለኛው የክርስ ቲያን ምሥክርነት

  ወደር የሌላቸው አገልጋዮች ከክርስቲያን ቤት ይወጣሉ፦ የጌታ አገልጋዮች ከቤት ውጭ ለሚያደርጉት አገልግሎት በሚገባ የሚዘጋጁት በክርስቲያን ቤተሰብ ውስጥ ነው። ይህ የሚሆነው ፈሪሐ-እግዚአብሔር ባለበት፤ እግዚአብሔር በሚወደድበትና በሚመለክበት ታማኝነት እንደ ሁለንተናዊ ተፈጥሮ በሆነበት፤ ለቤተሰብ ሃላፊነቶች አቅመ-ቢስ፣ ግድ-የለሽና ትኩረተ-ቢስ መሆን በማይፈቀድበት፤ የዕለት ተዕለት ተግባራትን በታማኝነት ለማከናወን በፀጥታ ከእግዚአብሔር ጋር ያለው የአንድነት ጊዜ አስፈላጊ መሆኑ በሚታመንበት ቤት ውስጥ ነው።1Manuscript 114, 1897.AHAmh 17.1

  የቤተሰብ ኃላፊነት በትክክለኛው መንፈስ ከተተገበረ ለጌታ በቋሚነትና በጥንቁቅነት ልንሠራለት የሚያስችለንን ልምድ ልናካብትበት የምንችል መሆኑ ሊታወስ ይገባል። ከተፈጥሮአዊ ስሜቱ ጋር ሊጣጣም ባይችል እንኳ አንድ ሕያው አገልጋይ ክርስቲያን በታማኝነት የዕለት ተዕለት ሥራዎቹን ምንም ሳያስቀር ከማከናወን፤ በደስታ መስቀሉን ከመሸከም የበለጠ ሌላ ምን ሊያደርግ ይችላል!2Signs of the Times, Sept. 1898.AHAmh 17.2

  ለክርስቶስ የምንሠራው ሥራ የሚጀምረው ከቤተሰብ ጋር በቤት ውስጥ ነው….ከዚህ የበለጠ አስፈላጊ የሆነ የአገልግሎት መስክ የለም….AHAmh 17.3

  በብዙዎች ዘንድ የቤት የሥራ መስክ በአሳፋሪ ሁኔታ ችላ ተብሎአል። መለኮታዊ ምንጭን በመፍትሔነት በማቅረብ የክፋትን አሠራር ለማስተካከል ጊዜው አሁን ነው።3Testimonies for the Church, Vol. 6, pp. 429, 430.AHAmh 17.4

  በወጣቶች ላይ የተጫነው ከፍተኛ ኃላፊነት በራሳቸው ቤት ውስጥ ሲሆን፤ ይህም እናትን፣ አባትን፣ ወንድምንና እህትን በፍቅርና በእውነተኛ መሻት መባረክ ነው። ለሌሎች በማድረግና በመንከባከብ እራስን-መካድንና እራስ-መርሳትን ሊያሳዩ ይችላሉ…. እህት እንዴት ዓይነት ተጽዕኖ ማሳደር ትችላለች! ትክክልም ከሆነች የወንድሞችዋን ባህርይ ልትለውጥና ልትቀርጽ ትችላለች። ፀሎትዋ፣ ጨዋነትዋና ፍቅርዋ በቤተሰብ ውስጥ ብዙ ሥራ ሊሠራ ይችላል።4Id., Vol. 3, pp. 80, 81.AHAmh 17.5

  በቤተሰብ ውስጥ ክርስቶስን የተቀበሉ ሁሉ ፀጋው ያደረገላቸውን ማሳየት አለባቸው። “ለተቀበሉት ሁሉ ግን ሥልጣንን ሰጣቸው የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ በስሙ የሚያምኑ።” በእውነትና በክርስቶስ ያመነ ክርስቲያን እራስን በማወቅ ሥልጣን ይሞላል፤ ተጽዕኖውም በቤተሰቡ ሁሉ ይታወቃል። ይህም በቤት ውስጥ ያሉ የቤተሰብ አባላትን ባህርይ ለማስተካከል የሚያመች ነው።5Manuscript 140, 1897.AHAmh 17.6

  ከሃዲው ሊቃወመው የማይችለው ክርክር፦ ሥርዓት ያለው የክርስቲያን ቤት ቤተሰብ የክርስቲያን ኃይማኖትን ዕውነታ በማሳየት ረገድ እምነት የለሹ ሊክደው የማይችል ከባድ የመከራከሪያ ነጥብ ነው። ልጆቻቸውን የሚለውጥ ተጽዕኖ በቤተሰቡ ውስጥ በሥራ ላይ እንዳለ፤ የአብርሃም አባት ከእነርሱ ጋር እንደሆነ ሁሉም ማየት ይችላሉ። የክርስቲያኖች ቤት በትክክለኛ ኃይማኖት የተቀረጸ ከሆነ ለመልካም ነገር ታላቅ ተጽዕኖ ይፈጥራል። በርግጥም “የዓለም ብርሃን” ይሆናል።6Patriarchs and Prophets, p. 144.AHAmh 17.7

  ልጆች የመጽሐፍ ቅዱስን መመሪያ ሊያስፋፉ ይገባል፦ ወላጆቻቸውን ይረዱ ዘንድ ጠቃሚ መሆንን የሚወዱ በደንብ የተማሩ ልጆች የመልካም ሐሳብን እውቀትና የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያን ለሚጎዳኟቸው ሁሉ ያሰራጫሉ።7Letter 28, 1890.AHAmh 18.1

  የራሳችን ቤት መሆን የሚገባውን ሲሆን ልጆቻችን እግዚአብሔር ለሌሎች እንዲያደርጉት የሚጠይቃቸውን ኃላፊነት በግድ-የለሽነትና በስንፍና እንዲተውት አንፈቅድላቸውም። የጌታ ውርስ እንደ መሆናቸው መጠን በተመደቡበት ቦታ ሥራውን ሊሠሩ የሠለጠኑ ይሆናሉ። ከእንደዚህ ዓይነቱ ቤት እውቀት ለጎደላቸው የሚገልፅ፤ የእውቀት ምንጭ ወደ ሆነው የሚመራቸው የብርሃን ነፀብራቅ ይወጣል። ለእግዚአብሔርና ለእርሱ እውነት ኃይል የሚሆን ተጽዕኖ ይመነጫል።8Testimonies for the Church, Vol. 6, p.430.AHAmh 18.2

  በሌላ በምንም ዓይነት መንገድ ሊደረሱ የማይችሉ ወላጆች ብዙ ጊዜ በልጆቻቸው አማካይነት ሊገኙ ይችላሉ።9Id., Vol. 4, p. 70.AHAmh 18.3

  ደስተኛ ቤተሰብ የጎረቤት ብርሃን ይሆናል፦ ብዙ ደስተኛ ወላጆች በበለጠ ደግሞ ደስተኛ ክርስቲያኖች ያስፈልጉናል። እራሳችን በራሳችን በጣም ለጉመን የምንኖር ነን። ብዙ ጊዜ ደጋግና አበረታች የሆኑ ቃላትንና አስደሳች ፈገግታዎቻችንን ከልጆቻችን እንዲሁም ከተጨቆኑና ተስፋ ከቆረጡ ሁሉ እንደብቃቸዋለን። ወላጆች ሆይ! ብርሃን ተሸካሚዎችና ብርሃን ሰጪዎች ትሆኑ ዘንድ አደራ ተጥሎባችኋል። በቤታችሁ የብርሃን ነፀብራቅ በመሆን ልጆቻችሁ ሊጓዙበት የተገባውን መንገድ አፍኩ። እንዲህም ስታደርጉ መብራታችሁ ብርሃን ለሌላቸው ይደርሳል።10Review and Herald, Jan. 29, 1901.AHAmh 18.4

  ከእያንዳንዱ የክርስቲያን ቤት ቅዱስ መብራት ሊንፀባረቅ ይገባል። ፍቅር በተግባር ሊገለጽና አሳቢ ደግነቱና ገራምነቱ እንዲሁም ራስ-ወዳድ ያልሆነ ለጋስነቱ በሁሉም የቤተሰብ ግንኙነት ወደ ውጭ ሊፈስና ሊታይ ይገባዋል። ይህ መርሆ የሚተገበርባቸው ቤቶች አሉ - እግዚአብሔር የሚመለክባቸውና እውነተኛ ፍቅር የነገሠባቸው ቤቶች። በእነዚህ ቤቶች ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች የጧት ማታ ፀሎት እንደ ጣፋጭ እጣን ወደ እግዚአብሔር ይወጣል፤ ምህረቱና በረከቱ በለመኑት ሁሉ ላይ እንደ ጠዋት ጤዛ ይወርዳል።11Patriarchs and Prophets, p.144.AHAmh 18.5

  የቤተሰብ ህብረት ውጤት፦ የመጀመሪያው የክርስቲያኖች ሥራ በቤት ውስጥ ህብረት መፍጠር ነው። የሚቀጥለው ሥራም በቅርብና በሩቅ ላሉ ጎረቤቶቻቸው መድረስ ነው። ብርሃን የተቀበሉ እነርሱ ቦግ ያለ ጮራቸውን ወደ ፊት ሊያበሩ ይገባቸዋል። በክርስቶስ ጣፋጭ የሆነው ንግግራቸው ለሌሎች ነፍሳት የሕይወት ሽታ ይሁንላቸው።12Manuscript 11, 1901.AHAmh 18.6

  የቤተሰብ አባላት በቤት ውስጥ ሥራቸው ፈጽሞ የተባበሩ እንደሆነ - እናት፣ አባት፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ከቤት ውጭ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ ለሌሎች የሚያነቃቃና የሚያግዝ ይሆናል።13Letter 189, 1903.AHAmh 19.1

  መልካም ወንዶች ከሊቃውንት ይልቅ ይፈለጋሉ፦ የቤተሰብና የቤተክርስቲያን ደስታ በቤት ተጽዕኖ ይወሰናል። የዘለዓለማዊ ፍላጎቶቻችን በዚህ ምድር ሕይወት በትክክል በምናከናውናቸው ኃላፊነቶች ይወሰናሉ። ዓለማችን ለቤታቸው በረከት የሚሆኑ ጥሩ ወንዶች የሚያስፈልጉዋትን ያህል ታላላቅ አዕምሮ ያላቸውን ሰዎች አትፈልግም።14Testimonies for the Church, Vol. 4, p. 522.AHAmh 19.2

  በሮችን ሊዘጉ የሚችሉ ስህተቶችን አስወግዱ፦ ኃይማኖት በቤት ውስጥ ሲገለጽ ተጽዕኖው በቤተ-ክርስቲያንና በአካባቢው ይታያል። አንዳንድ ክርስቲያን ነን ብለው የሚናገሩ ሰዎች ግን የቤት ውስጥ ችግራቸውን ለጎረቤት ይዘረዝራሉ። ሰዎች ከንፈራቸውን እንዲመጥጡላቸው እንደሚፈልጉ ሁሉ ብሶታቸውን ያብተከተካሉ። ችግሮቻችንን ለሌሎች ጆሮ ማፍሰስ ግን ትልቅ ስህተት ነው፤ በተለይ ደግሞ ቅሬታዎቻችን የራሳችን ፈጠራ ሲሆኑና በኃይማኖት-የለሽነታችን እንዲሁም ግድፈት ባለው ባህርያችን ምክንያት ሲፈጠሩ የባሰ አሳዛኝ ይሆናሉ። እነዚያ የግል ብሶታቸውን በሌሎች ፊት ለመዘርጋት የሚወጡ ሰዎች፣ በቤታቸው ቢቀሩና ቢፀልዩ፣ የተጣመመ ፈቃዳቸውን ለእግዚአብሔር ቢያስረክቡ፤ በቋጥኙ ላይ ቢወድቁና ቢሰባበሩ፤ ለእኔነታቸው ቢሞቱ ይሻላቸዋል፤ የሱስ የክብር ዕቃ አድርጎ እንደገና ይሠራቸዋልና።15Signs of the Times, Nov. 14, 1892.AHAmh 19.3

  ትህትና ማጣታችሁ፣ ነጭናጫነታችሁ፣ ሻካራነታችሁና ግድ-የለሽ አነጋገራችሁ ጥሩ ስማችሁን ሊያበላሹ ይችላሉ። ይህም የሌሎችን ልብ በር በመዝጋት ሁለተኛ ልትደርሷቸው ለማትችሉበት ደረጃ ያበቃችኋል።16Testimonies for the Church, Vol. 5, p. 335.AHAmh 19.4

  የቤት ክርስትና በውጭ ያንፀባርቃል፦ ቤታችን ሊሆን የተገባውን - በሰማይ ያለውን ቤት ተምሣሌት - ለማድረግ ስንለፋ ወሰኑ በሰፋ ክልል ውስጥ መሥራት እንድንችል ያዘጋጀናል። ለእርስ በእርሳችን ከምናደርገው ትህትና የተሞላበት መከባበር የምናገኘው ተሞክሮ የትክክለኛ ኃይማኖት መርሆዎችን መማር ለሚያስፈልጋቸው ልቦች እንዴት እንደምናደርስ ያሳውቀናል። ሁሉም በተለይ ደግሞ ወጣት የሆኑ የጌታ ቤተሰብ አባላት በጥንቃቄ ይጠበቁ ዘንድ ቤተ-ክርስቲያን ልታገኝ የምትችለው ልምድ ያካበተ መንፈሳዊ ኃይል ሁሉ ያስፈልጋታል። በቤት የሚተገበረው እውነት በማያዳላ ሁኔታ እራሱን ለውጭ ያሳያል። ክርስትናን በቤቱ የሚኖር እርሱ በሁሉም ቦታ ብሩህና የሚያንፀባርቅ ብርሃን ይሆናል።17Signs of the Times, Sept. 1, 1898.AHAmh 19.5

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents