Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የአድቬንቲስት ቤት - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First

  ምዕራፍ ስድሳ አራት—የንግድ ሥራ ታማኝነት

  መጽሐፍ ቅዱስ የንግድ ሥራ መርሆዎች ምንጭ ነው፡- አስፈላጊው ዝግጅት ይደርግ ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስ ምክር የማይለግስበት ምንም አይነት ሕጋዊ ሥራ የለም። የታታሪነት፣ የታማኝነት፣ የቆጣቢነት፣ የመጠን አዋቂነትና የንጽህና መርሆዎቹ የሥኬት ምስጢራቱ ናቸው። በምሣሌ መጽሐፍ የተቀመጡት እነዚህ መመሪያዎች የተግባራዊ ጥበብ ቅርሶች ናቸው። ነጋዴው፣ አርቲስቱ ወይም በማንኛውም የሥራ ዘርፍ ያለ ሥራ አስኪያጅ ለራሱም ሆነ ለሠራተኞቹ በጠቢቡ ሰው ከተነገሩት ምሳሌዎች የተሻለ ከየት ያገኛል?፡-AHAmh 285.1

  “በውኑ በሥራው የጨከነን ሰው አይተኻልን በነገሥታት ፊት ይቆማል፣AHAmh 285.2

  በተዋረዱም ሰዎች ፊት አይቆምም።”AHAmh 285.3

  “በድካምም ሁሉ ልምላሜ ያገኛል። ብዙ ነገር በሚናገር ከንፈር ግን ድህነትAHAmh 285.4

  ብቻ አለ።”AHAmh 285.5

  “ታካች ሰው ይሻል አንዳችም አያገኝም።”AHAmh 285.6

  “ሆዳምና ዘካሪ ችግረኛ ይሆናልና። የእንቅልፍም ብዛት [የተቦጫጨቀ] ጨርቅAHAmh 285.7

  ያለብሳል”….AHAmh 285.8

  ቃሉ አጉልቶና ደጋግሞ የሚናገረውን ማስጠንቀቂያ ቢሰማ ስንቱ ሰው ከገንዘብAHAmh 285.9

  ኪሳራና ጥፋት በዳነ ነበር፡-AHAmh 285.10

  “ባለፀጋ ለመሆን ግን የሚቸኩል ሳይቀጸፍ አይቀርም።”AHAmh 285.11

  “በችኮላ የምትከማች ትጎድላለች፣ ጥቂት በጥቂት የተከማቸች ግን ትበዛለች።”AHAmh 285.12

  “ባሰተኛ መላስ ከብት የሚያከማች እርሱ ጥፉ ነው፣ ወደ ሞትም ወጽመድAHAmh 285.13

  ይወድቃል።”AHAmh 285.14

  “ተበዳሪም ያበዳሪ ባሪያ ነው።”AHAmh 285.15

  “ለማያውቀው የሚዋስ ክፉ መከራ ይቀበላል፣ ከመዋስ ግን የሚጠነቀቅ የታመነAHAmh 285.16

  ይሆናል።”AHAmh 285.17

  ስምንተኛው ሕግ ስርቆትንና ዝርፊያን… ያወግዛል፤ እጅግ ጥቃቅን በሆኑ የሕይወት ጉዳዮች ዝርዝር ሁሉ ወለም ዘለም የማይል ታማኝነትን ይጠይቃል፤ በንግድ ማታለልን ይከለክላል፤ እዳንና ደሞዝን በአግባቡ መክፈልን ይጠይቃል።AHAmh 285.18

  አዕምሮና ባህርይ በሸፍጥ ምክንያት ያሽቆለቁላሉ፡- [ቅጥፈትን የሚናገር ወይም የሚያጭበረብር] እርሱ ለራሱ ያለውን ክብር ያጣል። እግዚአብሔር እንደሚያየውና እያንዳንዱን የሥራ (የንግድ) ግብይት እንደሚያውቅ፤ ቅዱስ መላእክት ሐሳቡን እንደሚመዝኑ፤ የሚናገረውን እንደሚያዳምጡ፤ በሰፈረውም ቁና እንደሚከፈለው አያስተውልም። የሚሠራውን ስህተት ከሰውና ከመለኮታዊ ፍተሻ መደበቅ ቢችል ኖሮ እንኳን ጥፋቱን ራሱ ማወቁ፣ ንቃተ ህሊናውንና ባህርይውን የሚሸረሽር ይሆንበታል። አንድ ድርጊት ባህርይን አይቀይርም፤ ሆኖም የጥፋት ማገጃውን ይሰብረውና የሚቀጥለውን ስህተት ለመፈጸም ከበፊቱ የቀለለ ይሆናል፤ ከዚያም ሰውየው አመኔታ እስኪያጣ ድረስ በፈጠራ ወሬ የተካነ የንግድ ሥራ ቅጥፈትን ልማዱ ያደረገ ይሆናል። 3Testimonies for the Church, Vol. 5, p. 396.AHAmh 285.19

  በሰዎች ላይ ጥቃቅን ሸፍጥ ወይም ሰፋ ያለ ማጭበርበር ስንፈጽም በእግዚአብሔር ላይም እንዲሁ እናደርጋለን። የእምነተ-ጎዶሎነትን መንገድ የመከተል ዝንባሌአቸውን በመተግበር የሚጸኑ ሰዎች፣ የራሳቸውን ነፍስ አታለው ሰማይንና ዘለዓለማዊ ሕይወትን ያጣሉ። ለመናኛ ዓለማዊ ጥቅም ኃይማኖታቸውንና ክብራቸውን ይሸጣሉ። 4Review and Herald, Sept. 18, 1888.AHAmh 286.1

  ከእዳ ሽሹ፡- ብዙ ቤተሰቦች ድኃ የሆኑት ገንባቸውን እንደተቀበሉ ስለሚያጠፉት ነው። 5Counsels on Stewardship, p. 269.AHAmh 286.2

  አንድ ሰው ጉዳዩን ሲያካሂድ ዕዳ ውስጥ ሊዘፍቀው በማይችለው ሁኔታ እንደሆነ ማስተዋል አለበት። አንድ ሰው ዕዳ ውስጥ ሲገባ ሰይጣን ካጠመዳቸው መረቦች በአንዱ ውስጥ ይገባል። ገና ተሰርቶ ያልተገኘን ገንዘብ መውሰድና መጠቀም ማነቆ ነው። 6Letter 63, 1897.AHAmh 286.3

  ከአቅሙ በላይ ለሚኖር የተሰጠ ቃል፡- በዕዳ መያዝህ እምነትህን የሚያደክምና ተስፋ የሚያስቆርጥህ በመሆኑ በገንዘብ ምክንያት ውርደት ይመጣብህ ዘንድ አትፍቀድ። ስለ ዕዳህ ማሰቡ ራሱ አዕምሮ ሊያሳጣህ ይችላል። ወጪዎችህን በመቀነስ ይህንን የባህርይህን ጉድለት መሙላት አለብህ። በቆራጥ ውሳኔ በመጣር ይህንን ከአቅምህ በላይ የመኖር ጠባይህን በቁጥጥርህ ሥር ማድረግ አለብህ፤ ትችላለህም። 7Letter 48, 1888.AHAmh 286.4

  የእግዚብሔር አላማ ወቀሳ ሊደርስበት ይችላል፡- ዓለም ዝንፍ የማይል ታማኝነትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖች ነን ብለው ከሚናገሩ ሰዎች ቢጠብቅ የተገባው ነው። መዋጮውን በአግባቡ በማይከፍል ሰው ምክንያት ሁሉም ህዝቦቻችን የማያስተማምኑ እንደሆኑ የመቆጠር አደጋ አለባቸው። 8Testimonies for the Church, Vol. 5, p. 179.AHAmh 286.5

  እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ እየተመላለስን ነን የሚሉ እነርሱ፣ የሚናገሩትን እውነት የበለጠ ማራኪ ማድረግ እንጂ እሳቤ በጎደለው እንቅስቃሴያቸው እውነት ሙልጭ ተደርጎ እንዲሰደብ ምክንያት መሆን የለባቸውም። “ከእላንት ለአንዳችሁ ሌላ እዳ አይሁን።” ይላል ሐዋርያው። 9Id., pp. 181, 182.AHAmh 286.6

  ምክር በዕዳ ውስጥ ላሉ፡- ሌላ ተጨማሪ ዕዳ ውስጥ ላለመግባት ቁርጥ ውሳኔ አድርጉ። በዕዳ ውስጥ ከምትሆኑ እራሳችሁን አንድ ሺህ ነገሮች ብትነፍጉ ይሻላችኋል። እዳ ውስጥ መዘፈቅ የህይወታችሁ እርግማን ሆኖ ቆይቷል። ዕዳን ልክ እንደ ፈንጣጣ ሽሹት። AHAmh 286.7

  የተቀደሰ ቃል-ኪዳን ከእግዚብሔር ጋር በማድረግ፣ በበረከቱ ዕዳዎቻችሁን ሁሉ ከፍላችሁ ከዚያም በኋላ ቆሎ ቆርጥማችሁ ማደር ከቻላችሁ ከማንም ላለመበደር ወስኑ። የምግብ ጠረጴዛችሁን ስታሰናዱ ተጨማሪ ለሆኑ ነገሮች ሀያ አምስት ሳንቲም ማውጣት በጣም ቀላል መስሎ ይታያችኋል፤ ለሳንቲሞቹ ከተጠንቀቃችሁ ብሮቹ ለራሳቸው ይጠነቀቃሉ። ለዚህም ለዚያም የሚወጡ ሳንቲሞች ናቸው ሲደመሩ ብር የሚሞሉት። ቢያንስ በዕዳ ታጥራችሁ ሳላችሁ ለራሳችሁ ንፉግ ሁኑ…. አታቅማሙ፤ ተስፋ አትቁረጡ፤ ወደ ኋላም አትመለሱ። ምርጫችሁን ገድቡ፤ ፍላጎታችሁን ከማርካት ተቆጠቡ፤ የሳንቲም ፍርቃጫችሁን አጠራቅማችሁ ዕዳዎቻችሁን ክፈሉ። በምትችሉት ፍጥነት ከፍላችሁ ጨርሱ። እንደገና ነፃ ሰውና ከማንም ብድር የሌለባችሁ ስትሆኑ ያኔ ታላቅ ድል ትቀዳጃላችሁ። 10Counsels on Stewardship, p. 257.AHAmh 286.8

  ላልታደሉ ባለዕዳዎች አዘኔታ አሳይ፡- አንዳንዶች በዕዳ ውስጥ ቢገኙና በእርግጥም ግዴታቸውን መወጣት ቢያቅታቸው፣ ከአቅማቸው በላይ የሆነውን እንዲያደርጉ መገደድ የለባቸውም። ከእዳቸው ሊላቀቁበት የሚችሉበት እድል ሊመቻችላቸው ይገባል እንጂ የባሰ እዳቸውን መክፈል በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ እንዲሆኑ መደረግ የለባቸውም። ይህ ዓይነቱ አካሄድ [ከምድራዊ] ህግ አኳያ ትክክል እንደሆነ ቢታሰብም የእግዚብሔር ምህረትና ፍቅር ግን አይደለም። 11Manuscript 46, 1900.AHAmh 287.1

  በሁለቱም ጠርዞች ያለው አደጋ፡- አንዳንዶች ጥንቁቅ አይደሉም። ዕዳ ውስጥ መግባትን ማስቀረት እየቻሉ አያደርጉትም። ሌሎች ደግሞ ከመጠን በማለፍ የእምነት ጎዶሎነት የሚታይበት ጥንቃቄ ያደርጋሉ። የእግዚአብሔርን ሥራ የማጠናከርና የመገንባት ጥቅም ያለው ከሆነ የተፈጠሩትን ምቹ ሁኔታዎች በመጠቀም ገንዘባችንን ሥራ ላይ ማዋል እንችላለን። ሆኖም ከትክክለኞቹ መርሆዎቻችን ንቅንቅ ማለት የለብንም። 12Manuscript 20, 1891.AHAmh 287.2