Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የአድቬንቲስት ቤት - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First

  ክፍል 8—የተዋጣለት ቤተሰብ

  ምዕራፍ ሃያ ሰባት—የተቀደሰው ክበብ

  የቤተሰብ ክበብ ቅድስና፦ በእያንዳንዱ ቤተሰብ ሊጠበቅ የሚገባው የተቀደሰ ክበብ አለ። ወደዚያ የተቀደሰ ክበብ ውስጥ ይገባ ዘንድ መብት ያለው የለም። ባልና ሚስት ለእርስ በእርሳቸው ሁሉን በሁሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ሚስት ከባልዋ ደብቃ ለሌሎች የምታወራው ምሥጢር ሊኖራት አይገባም። ባልም ከሌሎች ጋር የሚያወያየው ከሚስቱ የደበቀው ምሥጢር ሊኖረው አይገባም። የሚስቱ ልብ ለባልየው፣ የባልየው ልብ ደግሞ ለሚስቱ የጥፋታቸው መቀበርያ ይሁን። የሌላኛውን ስሜት የሚጎዳ ቀልድ ማንኛቸውም ፈጽሞ መሸርደድ የለባቸውም። ባልም ሆነ ሚስት በቧልትም ሆነ በማንኛውም ሁኔታ ቅሬታቸውን ለሌሎች በመግለጽ አንዱ ሌላውን ማማረር ፈጽሞ የማይመከር ይሁን። ቢደጋገሙ ምንም ጉዳት እንደማያመጡ የታመኑት እነዚህ የጅል ቀልዶች በመጨረሻ እርስ በእርሳቸው እንዲወነጃጀሉ፣ ምን አልባትም እንዲለያዩ ምክንያት ይሆናሉ። በእያንዳንዱ ቤተሰብ ዙሪያ የተቀደሰ መከለያ መኖር እንዳለበት አይቻለሁ።1Manuscript 1, 1855.AHAmh 118.1

  የቤት ክበብ የተቀደሰ ሥፍራ፤ የሰማይ ምሣሌና ራሳችን የሚያንፀባርቅ መስታወት ተደርጎ መወሰድ አለበት። ትውውቆችና ጓደኞች ሊኖሩን ይችላሉ፤ በቤታችን ሕይወት ግን ጣልቃ ሊገቡ አይገባም። የሚያፍታታ፣ የሚያሳርፍና እምነት የሚጣልበት የቤተሰብ ግላዊነት ሊሰማን ይገባል።2Letter 17, 1895.AHAmh 118.2

  ምላስ ጆሮና ዓይን ይቀደሱ፦ የቤተሰቡ ክበብ አካል የሆኑ ሁሉ ምላሳቸውን፣ ጆሮአቸውን፣ ዐይናቸውንና እያንዳንዱን የሰውነታቸውን ክፍል እግዚአብሔር እንዲቀድስላቸው ይጸልዩ። ከርኩሰት ጋር መነካካት ቢፈጠር እንኳ በርኩስ ነገር መሸነፍ ግን አስፈላጊ አይደለም። ባህርያችን መልካም መዓዛ ይኖረው ዘንድ ክርስቶስ አስችሎታል….AHAmh 118.3

  በቤታቸው ክበብ ውስጥ ክርስቶስን የሚያዋርዱና ያለመልኩ መልክ የሚሰጡት ስንቶች ናቸው! ትዕግሥት፣ ራስን-መግዛት፣ ይቅር-ባይነት እንዲሁም እውነተኛ ፍቅር የማይገልጹ ስንቶች ናቸው! የክርስቶስን ፈቃድ፣ ሥራውንና ባህርይውን በመግለጽ ፈንታ የሚወዱትና የማይወዱት ዝርዝር ያላቸው፣ የራሳቸውን የተጣመመ ፍላጎት ለማንፀባረቅ ነፃነት የሚሰማቸው ብዙ ናቸው። የክርስቶስ ሕይወት በቸርነትና በፍቅር የተሞላ ነው፤ ወደ መለኮታዊ ባህርይው እያደግን ነው?3Manuscript 18, 1891.AHAmh 118.4

  ህብረት፣ ፍቅርና ሠላም፦ እናቶችና አባቶች በፀጋው ረዳትነት በራሳቸው ጠባይና በሕይወታቸው ልጆቻቸው እንዲያጎለብቱት የሚመኙትን ዓይነት መንፈስ እንዲያንፀባርቁ እንጂ በመካከላቸው አለመግባባት እንዳይፈጠር ሊወድዱትና ሊታዘዙት ባወጁለት በእግዚአብሔር ፊት ክቡር ቃል-ኪዳን ይግቡ።4Manuscript 38, 1895.AHAmh 118.5

  ወላጆች የጠብ መንፈስ ቀስ በቀስ ተንኳትቶ ወደ ቤታቸው እንዲገባ መፍቀድየለባቸውም። ይህ በባህርይ ላይ ተጽዕኖ እንዲያሳድሩ ከሚላኩ የሰይጣን ወኪሎች አንዱ ነው። የክርስቶስን ሕይወት የመራውን ደንብ በማስረጽ ወላጆች ፍጹም ህብረት እንዲኖር የሚጥሩ ከሆነ ጠብ ተባርሮ አንድነትና ፍቅር በቤት ውስጥ ይደላደላሉ፤ ወላጆችና ልጆች የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ተካፋይ ይሆናሉ።5Manuscript 53, 1912.AHAmh 119.1

  ባልና ሚስት የሚበቃቸውን የኑሮ ሸክም እንደተሸከሙና ሕይወታቸውን የሚያንኮታኩት ልዩነት በመካከላቸው ይንፀባረቅ ዘንድ መፍቀድ እንደማያስፈልጋቸው ያስታውሱ። ትንሽ የልዩነት ቀዳዳ የሚከፍቱ እነርሱ ሰይጣንን ወደ ቤታቸው ይጋብዛሉ። ልጆቻቸው የፈጣሪ እምነት የጎደላቸው እንዲሆኑ በማድረግ የሰይጣን ወኪሎች ኃላፊነታቸውን ይወጣሉ።6Letter 133, 1904.AHAmh 119.2

  በትዳር ሕይወት ፈተናዎች ቢያጋጥሟቸውም ባልና ሚስት ነፍሳቸውን በእግዚአብሔር ፍቅር ማያያዝ አለባቸው። አባት የልጆቹ እናት የሆነችውን ሚስቱን ሁሌም ቸርነት፣ ገርነትና ርኅራኄ የተገባት ሆና ይመልከታት።7Letter 198, 1901.AHAmh 119.3

  የቤተሰብ አንድነት ምሥጢር፦ የቤተሰብና የቤተ-ክርስቲያን መከፋፈልና መጣላት መንስኤው ከክርስቶስ መነጠላቸው ነው። ወደ ክርስቶስ መቅረብ ወደ እርስ በእርሳችን መጠጋጋት ነው። እነዚህ ነገሮች በገፍ የሚያስፈልጉን ቢሆኑም የቤተ-ክርስቲያንና የቤተሰብ እውነተኛ ህብረት ምሥጢር የተለየ የማስተዳደር ጥበብ (ዲፕሎማሲ) አስተዳደር ወይም ከሰው ተፈጥሮ በላይ የሆነ ችግሮችን ለማስወገድ የሚደረግ ጥረት አይደለም፤ ከክርስቶስ ጋር ያለው ህብረት እንጂ። AHAmh 119.4

  ከጠርዙ ወደ ዕምብርቱ የተሰመሩ ብዙ መስመሮች ያሉትን ክብ ቅርፅ ያለው ሥዕል በአዕምሮአችሁ ሳሉ። ከጠርዙ የሚነሱት መሥመሮች ወደ መሃል እየተጠጉ ሲሄዱ የበለጠ እየተቀራረቡ ይሄዳሉ።AHAmh 119.5

  የክርስቲያን ሕይወትም እንዲሁ ነው። ወደ ክርስቶስ የበለጠ ስንቀርብ እርስ በእርሳችን እየተጠጋጋን እንሄዳለን። በመልካም መስማማት ሕዝቦቹ አንድ ሲሆኑ እግዚአብሔር ይከብራል።8Letter 49, 1904.AHAmh 119.6

  አንዱ ሌላውን ያግዝ፦ የቤተሰብ ኩባንያ የተቀደሰ ማህበራዊ ስብስብ፣ እያንዳንዱ አባል የሥራ ድርሻ ያለውና አንዱ ሌላውን ሊረዳ የተገባው ድርጅት ነው። ልክ በትክክል እንደሚሠራ መሳሪያ የቤተሰቡ ሥራም በተናበበ ሁኔታ ሊከናወን ይገባዋል።9Manuscript 129, 1903.AHAmh 119.7

  እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ለቤተሰቡ ምቾት ሥርዓትና ደንበኛነት የሚያበረክተው ግላዊ የሆነ ኃላፊነት እንዳለበት አይዘንጋ። አንዱ የሌላውን ተቃራኒ አያድርግ። ሁሉም በህብረት ይራመዱ፤ አንዱ ሌላውን የሚያበረታታ መልካም ሥራ ይሥራ፤ መደናገርን በሚያስወግድ የተረጋጋና ለስላሳ አነጋገር ተወያዩ፤ ጨዋነትን፣ ራስ መግዛትንና ታጋሽነትን ተግብሩ፤ እያንዳንዱ ልጅ የእናቱን ሸክም ለማቅለል የተቻለውን ያድርግ….AHAmh 120.1

  እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ከሌሎቹ ጋር ህብረት ለመፍጠር የሚያስችለውን ኃላፊነቱን ይወቅ። ስድስት ዓመትና ከዚያ በላይ ያሉ ሁሉ ድርሻቸው የሆነውን የሕይወት ጭነት መሸከም እንደሚገባቸው ማወቅ ያስፈልጋቸዋል።10Testimonies for the Church, Vol. 2, pp. 699, 700.AHAmh 120.2

  የሚገጥም ውሳኔ፦ ለድርጊቶች ሁሉ የግብረ-ገብነት ጉልበት እሰጣቸው ዘንድ በቤትም ሆነ በየትኛውም ሥፍራ በፀጋ ማደግ ያስፈልገኛል። በቤት ውስጥ መንፈሴን፣ ድርጊቶቼን እንዲሁም ከአፌ የሚወጡትን ቃላት መቆጣጣር አለብኝ። በተገቢው መንገድ እንድማርና እንድሰለጥን፣ አድግ ዘንድ ላለኝ ልባዊ ጥረቴ ጊዜ መስጠት ይገባኛል። ለሌሎች ምሳሌ መሆን አለብኝ። የእግዚአብሔርን ቃል ቀንና ማታ ማሰላሰልና በሕይወቴም መተግበር አለብኝ። ያለፍርሃት ልጠቀመው የምችለው ጎራዴ የመንፈስ ቅዱስ ሰይፍ የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው።11Manuscript 13, 1891AHAmh 120.3