Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የአድቬንቲስት ቤት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First

    ክፍል ፭—ከትዳር መሠውያ ሥር

    ምዕራፍ አሥራ አምስት—የተረጋገጡ ተስፋዎች

    የእግዚአብሔር እቅድ ለባልና ለሚስት፦ አጋሩና ረዳቱ ከእርሱ ጋር አንድ ትሆን ዘንድ ልታደፋፍረው ልታበረታታውና ልታከብረው እርሱም ደግሞ ጠንካራ ረዳት ሊሆናት እግዚአብሔር ሴትን ከወንድ ሠራት። በተቀደሰ ዓላማ ወደ ጋብቻ የሚገቡ ሁሉ እግዚአብሔር ለእነርሱ ያለውን ዓላማ የሚተገብሩ ናቸው፤ ይኸውም ባልየው የሚስቱን ንጹህ ልባዊ ፍቅር ማግኘት፤ ሚስት ደግሞ የባልዋን ባህርይ መግራት፣ ማሻሻልና ሙሉነት መስጠት ነው። ክርስቶስ ይህንን ተቋም ሊሽር አልመጣም፤ ወደ መጀመሪያው ቅድስናውና ከፍታው ሊያድሰው እንጂ። የእግዚአብሔርን የግብረገብነት ምሣሌ በሰው ዘንድ ሊያድስ መጣ። ጋብቻንም በማጽደቅ ሥራውን ጀመረ።1Manuscript 16, 1899.AHAmh 62.1

    ሔዋንን ለአዳም ረዳት አድርጎ የሰጠ እርሱ፣ በሠርግ ቀን [በቃና ገሊላ] የመጀመሪያ ታምራቱን ፈፀመ። ዘመድ አዝማድና ጓደኞች በደስታ በተሰበሰቡበት የሠርግ አዳራሽ ውስጥ ክርስቶስ የሕዝብ አገልግሎቱን ጀመረ። ከዚያም እርሱ ያቋቋመው መሆኑን እውቅና በመስጠት ጋብቻን አፀደቀው። አባልነታቸው የሰማይ ቤተሰብ የሆነ የክብር ዘውድ የደፉ ልጆችን ያፈሩ ዘንድ ሴቶችና ወንዶች በተቀደሰ የጋብቻ ሕግ እንዲጋቡ እርሱ አዘዘ።2Ministry of Healing, p. 356.AHAmh 62.2

    የሱስ ደስተኛ ትዳር ይፈልጋል፦ ከክርስቶስ የሚመነጨው መለኮታዊ ፍቅር የሰውን ፍቅር ፈጽሞ አያጠፋውም፤ ያዋህደዋል እንጂ። ከመለኮታዊ ፍቅር የተነሣ የሰውኛ ፍቅር የጠራና የነፃ፣ ከፍ ከፍ ያለና የከበረ ይሆናል። ከመለኮታዊ ባህርይ ጋር ተጣምሮ ወደ ሰማይ እንዲያድግ ካልሠለጠነ በስተቀር የሰው ፍቅር የከበረ ፍሬ ያፈራ ዘንድ ፈጽሞ አይቻለውም። የሱስ ደስተኛ ትዳር - ደስተኛ የቤት ሕይወት - ማየት ይሻል።3Bible Echo, Sept. 4, 1899AHAmh 62.3

    ልክ እንደ ሌሎቹ የእግዚአብሔር መልካም ስጦታዎች የሰው ዘርን ለመጠበቅ የተሰጠ - ጋብቻ - በኃጢአት ምክንያት የተበላሸ ሆነ። ሆኖም ወደ ቀድሞው ንጽህናውና ውበቱ ይመለስ ዘንድ የወንጌሉ ዓላማ ነው….AHAmh 62.4

    እግዚአብሔር ባቀደው መሠረት ጋብቻ የሰው ዘር እንዲባረክና ከፍ ከፍ እንዲል ሚና የሚጫወት ይሆን ዘንድ የሚያስችለው የክርስቶስ ፀጋ ብቻ ነው። ምድር ላይ ያሉት ቤተሰቦች በህብረታቸው፣ በሠላማቸውና በፍቅራቸው የሰማይን ቤተሰብ እንዲወክሉ ነው። ይህ የተቀደሰ ግንኙነት ከእግዚአብሔር ሀሳብ አንፃር ሲታይ የህብረተሰቡ ሁኔታ አሳዛኝ ትችት የሚያቀርብበት ሆኗል። ሆኖም ጓደኝነትንና ደስታን ተስፋ ሲያደርጉ ሳለ የኑሮ መራራነትና ቅሬታ የተሰማቸው ሁሉ በክርስቶስ ወንጌል መጽናናትን ያገኛሉ።4Review and Herald, Dec. 10, 1908.AHAmh 62.5

    የደስታ ክብረ-በዓል፦ የሱስና ደቀ-መዛሙርቱ በቃና ወደ ነበረው የጋብቻ በዓል ተጠርተው እንደነበር ቃሉ ይናገራል። ክርስቲያኖች ለጋብቻ ሲጋበዙ በእንደዚህ ዓይነቱ የደስታ በዓል እንዳይገኙ ክርስቶስ የጣለው ማዕቀብ የለም። ክርስቶስ በዚህ በዓል በመገኘት የእርሱን ትእዛዛት በመጠበቅ ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ሊለን እንደሚገባ አስተምሯል። በሰማያዊ ህግ መሠረት የሚተገበሩ ከሆነ የሰው ዘር የሚያከብራቸው ኃጢአት የሌለባቸው ክብረ-በዓላት እንዳይኖሩ ክርስቶስ አልመከረም። በመገኘቱ ያከበረውን ስብሰባ ተከታዮቹ ቢገኙበት ትክክል ነው። ክርስቶስ ከዚህ ጋብቻ በኋላ ሌላ ብዙ የጋብቻ በዓላት ላይ ተሳትፏል፤ በመገኘቱና መመሪያውን በማሳወቅም ቀድሷቸዋል።5Manuscript 16, 1899.AHAmh 62.6

    ከልክ ያለፈ ትዕይንት፣ ገንዘብ አባካኝነትና ውካታ በጋብቻ ቀን አስፈላጊ አይደለም፦ የጋብቻ አከባበር የእዩኝ እዩኝ ዓይነት፣ የገንዘብ ብክነትና የራስ ፍላጎት እርካታ የሚተገበርበት በዓል ሆኗል። ነገር ግን የሚጋቡት ወገኖች በኃይማኖታዊ ደንብና ሥርዓት፣ ሁሉም ነገር በተደራጀ መልኩ ያለታይታና የገንዘብ ብክነት የሚፈፅሙት ከሆነ የዚህ ዘመን ጋብቻም እግዘአብሔርን የማያስደስትበት ምክንያት የለም።6Review and Herald, Sept. 25, 1888.AHAmh 63.1

    ተጋቢዎቹ ፍጹም የተዋጣላቸው ቢሆኑም እንኳን ትልቅ ሰልፍና ታይታ መፍጠር አስፈላጊ አይደለም።7Testimonies for the Church, Vol. 4, p. 515.AHAmh 63.2

    ሁልጊዜም በጣም አግባብነት የሌለው እንደሆነ የሚሰማኝ ነገር ቢኖር የጋብቻ ሥነሥርዓት ሌላ ዝግጅት ይመስል በውካታና በፌሽታ የተሞላ መሆኑ ነው። ይህ መሆን የለበትም፤ በታላቅ መረጋጋት ሊፈፀም የሚገባው በእግዚአብሔር በራሱ የተደነገገ ሥርዓት ነው። የትዳር ግንኙነት እዚህ ምድር ላይ ሲመሠረት ቤተሰቡ በላይ በሰማይ ያለው ቤተሰብ ሊሆነው ላለው መገለጫ ነው። ሁልጊዜም የእግዚአብሔር ክብር ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል።8Manuscript 170, 1905.AHAmh 63.3

    ጋብቻ በሚስስ ዋይት ቤት፦ ማክሰኞ ከጠዋቱ አምስት ሰዓት አካባቢ ሰፊው የምግብ ክፍላችን ለጋብቻው ሥነ-ሥርዓት ተዘጋጅቶ ነበር። አገልግሎቱን የሚመራው ወንድም ቢ(B) ነበር፤ በጥሩ ሁኔታ ተጠናቀቀ። ከጋብቻ ሥነ-ሥርዓቱ በኋላ እህት ዋይት ፀሎት ታድርግልን ተባለ። እግዚአብሔር የተለየ ነፃነት ሰጠኝ። ልቤ ለሰለሰ፤ በእግዚአብሔር መንፈስ ተሸነፈ። በዚህ ሥነ-ሥርዓት ፌዝና የሞኝነት አነጋገር አልነበረም። ማንኛውም ከጋብቻው የተገኘ ነገር ሁሉ ሞገስ የተላበሰና ቅዱስ ነበር፤ ሁሉም ነገር የላቀ ባህርይ ያለው፣ እጅግ የሚያስደንቅ ነበር። ጌታ ይህንን ጋብቻ ባረከው፤ ሁለቱም በወንጌል ሥራ መስክ ለመሰማራትና የጠፉትን ለማዳን ፍላጎታቸውን አንድ አድርገው አጣምረዋል። በእርሱ የተስፋ ቃል-ኪዳን ሙሉ በሙሉ ተደግፈው አብረውት በትህትና የሚራመዱ ከሆነ እግዚአብሔር በሥራቸው ይባርካቸዋል።9Manuscript 23, 1894.AHAmh 63.4

    የሁለት ነፍሳት ውህደት*ማስታወሻ፡- በ 1905 ኤ. ጂ. ዋይት በሳኒታሪም ካሊፎርኒያ(Sanitarium, California) በተፈጸመ የሰርግ ሥነ-ሥርዓት ላይ ተገኝታ የሰጠችው መግለጫ፡፡፦ ነፍሳትን በማዳን አገልግሎት ጥረታቸውን፣ ፍላጎታቸውን፣ ሐዘናቸውን፣ ፍቅራቸውንና ልፋታቸውን ሁሉ ሊያጣምሩ በፊታችሁ ለቆሙት ሰዎች፣ ይህ ጊዜ በታሪካቸው ውስጥ በጣም አስፈላጊው ነው። በጋብቻ ግንኙነት ውስጥ የሚወሰድ አስፈላጊ እርምጃ አለ፤ እርሱም የሁለት ነፍሳት ወደ አንድ ውህደት መምጣት ነው…. ባልና ሚስት በእርሱ ሥራ ተጣምረው በሙሉነትና በቅድስና ሥራውን ወደ ፊት ማራመዳቸው ከእግዚአብሔር ጋር የተስማማ ነው። ይህንን ደግሞ ማድረግ ይችላሉ። ይህ ዓይነቱ ጥምረት በሚኖርበት ቤት ውስጥ የእግዚአብሔር በረከት እንደ ሰማያዊ ነፀብራቅ ነው። ምክንያቱም ጋብቻ ባልና ሚስት በክርስቶስ ሥር ሆነው እርሱ እየተቆጣጠራቸውና መንፈሱ እየመራቸው በተቀደሰ አንድነት ይጣመሩ ዘንድ በራሱ ፈቃድ የፀደቀ ተቋም ስለሆነ ነው።AHAmh 63.5

    በምድር ላይ ካሉ ቦታዎች ሁሉ ይልቅ ቤት ደስታ የሚገኝበት ይሆን ዘንድ እግዚአብሔር ይፈልጋል። በሰማይ ያለው ቤት ትክክለኛ አምሳል እንዲሆን ይሻል። የትዳር ኃላፊነቶቻቸውን በመሸከም፣ ፍላጎታቸውን ከየሱስ ክርስቶስ ጋር በማጣመር፣ በክንዱና በመድንነቱ በመደገፍ ባልና ሚስት መላእክት ሊያሞግሱት የሚችሉት የትዳር ደስታ ተካፋይ ሊሆኑ ይችላሉ። ትዳር ጠቃሚነታቸውን ያጠናክረዋል እንጂ አይቀንሰውም። ያንን የትዳር ሕይወት፣ ለክርስቶስ ነፍሳትን የሚያሸንፉበት አገልግሎት ሊያደርጉት ይችላሉ። ስለማውቀው ነው የምናገረው፤ ምክንያቱም ባለቤቴና እኔ ተጋብተን ለሰላሳ ስድስት ዓመታት ስንቆይ ጌታ ሂዱ ያለን ቦታ ሁሉ ሄደናል። በትዳር እያለን በዚህ ጉዳይ ላይ የእግዚአብሔር የምሥጋና መልእክት እንዳለን እናውቃለን። ስለዚህ ከባድ ኃላፊነት ነው…. እናም በዚህ ሰዓት ወንድማችን ሆይ እጅህን እንይዛለን….እህታችን ሆይ እጅሽን እንይዛለን…. ተባብራችሁ የእግዚአብሔርን ሥራ እንድትሠሩ እናደፋፍራችኋለን። እላችኋለሁ፣ እግዚአብሔርን መካሪያችሁ አድርጉት፤ ተዋሃዱ፣ በአንድነት ተዋሃዱ።10Manuscript 170, 1905.AHAmh 64.1

    ምክር ለአዲስ ሙሽሮች፦ የተወደዳችሁ ወንድምና እህት፤ በዕድሜ-ልክ ቃል-ኪዳን ተጣምራችኋል። የትዳር ሕይወታችሁ ትምህርት ጀምሯል። ልክ አንድ ልጅ ትምህርት እንደሚማር ሁሉ የመጀመሪያው የትዳር ዓመት ባልና ሚስት የተለያየ ባህርያቸውን የሚማማሩበት ነው። ስለዚህ በዚህ በመጀመሪያው የትዳር ወቅታችሁ የወደፊት ደስታችሁን የሚያውክ ምንም ምዕራፍ አትክፈቱ….AHAmh 64.2

    ወንድሜ ሆይ የባለቤትህ ጊዜ፣ ጉልበትና ደስታ ከአንተው ጋር ታስረዋል፤ በእርስዋ ላይ ያለህ ተጽዕኖ የሕይወትህ ሽታ ለህይወትዋ፤ ወይም የሞትህ ሽታ ለሞትዋ ሊሆን ይችላል። ሕይወትዋን እንዳታበላሸው አጥብቀህ ተጠንቀቅ። እህቴ ሆይ ስለ ጋብቻ ሕይወት ኃላፊነቶች አሁን የመጀመሪያውን ተግባራዊ ትምህርት ልትማሪ ነው። እነዚህን ትምህርቶች ቀን በቀን በታማኝነት ልትማሪ እርግጠኛ ሁኚ…. ለራስ-ወዳድነት መንገድ እንዳትከፍቺ ሁልጊዜ ተጠንቀቂ። AHAmh 64.3

    በሕይወታችሁ ያለው የአብሮነት ፍቅራችሁ ለእርስ በእርስ ደስታችሁ ገባር ይሁን። አንዳችሁ ለሌላኛችሁ ደስታ ሲል ሊያገለግል ይገባል። እናንተን በተመለከተ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይህ ነው። እንደ አንድ ልትዋሃዱ የተገባ ቢሆንም አንተም ሆነ እርስዋ ግን ግላዊነታችሁን በሌላኛው ማጣት አይገባችሁም። እንዲህ ብላችሁ እግዚአብሔርን ጠይቁት፦ ትክክለኛው የቱ ነው? ትክክል ያልሆነውስ? የተፈጠርኩለትን ዓላማ እንዴት በተሻለ ሁኔታ ላሳካው እችላለሁ?11Testimonies for the Church, Vol. 7. P. 45.AHAmh 65.1

    በሰማያዊ ምሥክሮች ፊት ቃል መግባት፦ ትዳር በሚመሠርቱ ጥንዶች መካከል ፍፁም መስማማትና ፍቅር እንዲኖር እግዚአብሔር አዟል። ሙሽራውና ሙሺሪት በሰማያዊ ዓለም (heavenly universe) ነዋሪዎች ፊት እርስ በእርስ ሊፋቀሩ ቃል ይግቡ፤ እግዚአብሔር የሚፈልግባቸው ያ ነውና…. ሚስት ባልዋን ልታከብረውና ልታወድሰው ባል ደግሞ በበኩሉ ሊያፈቅራትና ሊንከባከባት ይገባል።12Bible Echo, Sept. 4, 1899.AHAmh 65.2

    ወንዶችና ሴቶች በትዳር ሕይወት መጀመሪያ፣ እራሳቸውን እንደገና በእግዚአብሔር ፊት ሊቀድሱ ይገባቸዋል።13Manuscript 70, 1903.AHAmh 65.3

    እግዚአብሔርን እንደሚፈራ ትዕዛዛቱንም እንደሚያከብር ጎልማሳ በሐሳብ፣ በንግግርና በሥራ መዝገብህን እንዳታበላሽ ለትዳርህ መሐላ ልክ እንደ ብረት ቀጥ ያልክ፣ ወለም-ዘለም የማትል፣ ሀቀኛ ሁን።14Letter 231, 1903.AHAmh 65.4