Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የአድቬንቲስት ቤት - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ምዕራፍ አርባ ሁለት—የእናት ጤንነትና ግላዊ ገጽታ

  የእናትን ጤና መንከባከብ ተገቢ ነው፦ የእናት ጉልበት በጥንቃቄ ሊጠበቅላት ይገባል። ውድ ጉልበትዋ በአድካሚ ሥራ እንዳያልቅ ጭንቀቶችዋና ሸክሞችዋ ሊቀነሱላት ይገባል። ብዙ ጊዜ ቤተሰቡ እንዲረዳው የሚጠበቅበትን፤ ለቤተሰቡ ደህንነት የሚያስፈልጉትን አካላዊ ሕጎች አባትና ባል አያውቃቸውም። የዕለት ጉርስ የማሸነፍ ሥራ ውስጥ ተጠምዶ፤ ወይም ብዙ ሀብት ለማከማቸት ሲፍገመገም በብዙ ችግርና ግራ መጋባት ተይዞ፤ ባለቤቱ ኃይል እጅግ በሚያስፈልጋት ወቅት ጉልበትዋን የሚያሟጥጠውን ሸክም በእርስዋ ላይ ያራግፋል፤ የተዝለፈለፈችና በሽተኛ ትሆናለች። 1Ministry of Healing, p. 373.AHAmh 175.1

  አላስፈላጊ ድካምን በማስቀረት ሕይወትዋን፣ ጤናዋንና እግዚአብሔር የሰጣትን ጉልበትዋን ጠብቃ ለማቆየት ብትጠቀምበት ለእርስዋም ሆነ ለቤተሰቧ ጥቅም ነው። ሁለንተናዊ የአካል ብቃትዋ ለታላቁ ሥራዋ ያስፈልጋታል። በቤት ውስጥ ያለ ሥራዋን በደስታና ልቅም ባለ ሁኔታ እንድታከናውን ኃይልዋ ይታደስ ዘንድ አካላዊ እንቅስቃሴ በማድረግ የተወሰነ ጊዜዋን ከቤት ውጪ ልታሳልፈው ይገባታል፤ የቤትዋ መብራትና በረከት ትሆናለች። 2Pacific Health Journal, June, 1890.AHAmh 175.2

  እናቶች ለጤና ተሐድሶ ሊቆሙ ይገባቸዋል፦ የእግዚአብሔር ፈቃድ ለሁሉም እናቶች ግልጽ በሆነ መልኩ ተቀምጧል፤ በመመሪያነትና በተምሣሌትነት የጤናን መሻሻል እንዲያስተባብሩ ይፈልጋል። እግዚአብሔር በልጆቻቸው ውስጥ ያስቀመጠውን አካላዊ ሕግ ላለመጣስ ይቻላቸው ዘንድ እግራቸውን በጠንካራ መርህ ላይ መትከል ይጠበቅባቸዋል። “በእውነተኛ ዓላማ በመቆም” በማያወላውል ሃቀኝነት ውስጥ ላሉ እናቶች ኃይልና ፀጋ ከሰማይ ይሰጣቸዋል፤ እራሳቸው በሚያጎለብቱት ቀና መንገድ እንዲሁም በልጆቻቸው ጨዋ ባህርይ ጉልበት ያገኛሉ። 3Good Health, Feb., 1880.AHAmh 175.3

  በምግብ እራሳቸውን ይቆጣጠሩ፦ እናት ከሁሉም የበለጠ እራስዋን መቆጣጠር ያስፈልጋታል። ይህንንም ለማሳካት አካላዊና አዕምሮአዊ መዛባት ከሚያመጡ ነገሮች አስቀድማ መጠንቀቅ ይገባታል። ሕይወትዋ በእግዚአብሔርና በጤና ሕግ መመራት አለበት። የምትበላው ምግብ አዕምሮዋና ባህርይዋ ላይ ተጽዕኖ ስላለው፣ በዚህ ረገድ በጣም ጥንቃቄ መውሰድ ይኖርባታል። ስሜትን የሚቀሰቅስ ሳይሆን አካልን የሚያበለጽግ፤ ነርቮችዋ የተረጋጉ፣ ጠባይዋም የሰከነ የሚያደርጉትን ምግቦቸ ትመገብ። እንዲህም ሲሆን የተለያየ ዝንባሌ ያላቸውን ልጆችዋን በትዕግሥት እንድትቆጣጠር፣ የማስተዳደር ሥራዋንም በጥንካሬ ሆኖም በፍቅር እንድታካሂደው ያስችላታል። 4Pacific Health Journal, May, 1890.AHAmh 175.4

  በማንኛውም ሁኔታ የብርሃን ጮራ ማንፀባረቅ ይገባታል፦ በምትጨነቅበትም ጊዜ ቢሆን እናት ስሜትዋንና ሕሊናዋን መቆጣጠር አለባት፤ ትችላለችም። በታመመችበት ጊዜ እንኳን እራስዋን ማሸነፍ ከቻለች፤ ደስተኛና ፍልቅልቅ ከሆነች፤ እችለዋለሁ ብላ አስባ የማታውቀውን ወከባ መታገስ ትችላለች። እናት አቅመቢስነትዋንና ጉድለትዋን ልጆችዋ እንዲያውቁ በማድረግ በመንፈስ ውድቀትዋ ሳቢያ ለጋና በቀላሉ ሊጎዳ የሚችለው አዕምሮአቸው ላይ ደመና እንዲያንዣብብ፣ ቤቱ መቃብር እንዲመስል፣ መኝታ ክፍልዋ ደግሞ በዓለም ካሉ ሥፍራዎች ሁሉ ቀፋፊው እንደሆነ እንዲሰማቸው ማድረግ የለባትም። የምንፈልገውን ነገር በምንፈጽምበት ጊዜ አዕምሮአችንና ነርቮቻችን ጤንነትና ጥንካሬን ያገኛሉ። በብዙ አቅጣጫ የፈቃዳችን ጉልበት ነርቮቻችንን የማረጋጋት አስተማማኝ ኃይል አለው። እናት በጠቆረ ግንባር ተኮሳትራ ልጆችዋ ሊያዩዋት አይገባም። 5Testimonies for the Church, Vol, 1, p. 387.AHAmh 176.1

  የባልዋንና የልጆችዋን ክብር መጠበቅ አለባት፦ እህቶች ሥራቸውን ሲሠሩ ወፍን(አሞራን) ከማሽላ ማሳ ለማባረር የተቀመጠ ምስል የሚያስመስላቸውን ልብስ መልበስ የለባቸውም። ለጎብኝዎች ወይም ለእንግዶች ታስቦ ከሚለበስ ልብስ ይልቅ ሰውነታቸውን የሚገጥም ጨዋነት የሚታይበት ልብስ በቤተሰቦቻቸው መካከል ቢለብሱ ልጆቻቸውንና ባሎቻቸውን የሚያስደስት ይሆናል። በቤት ሥራ ላይ እያሉ እንዲሁም ባሎቻቸውና ልጆቻቸው ብቻ የሚያዩአቸው ከሆነ ለአለባበሳቸው ግድ የሌላቸው፣ በእነርሱ ሕይወት ውስጥ ለማያገባው የውጭ ሰው ለመታየት ግን የሚሽቀረቀሩ ሴቶች አሉ። ከተራ ጓደኞችና ከእንግዶች ይልቅ የልጅና የባል ክብር የበለጠ ዋጋ አይሰጠውም? ከሌላው ሰው ሁሉ ይልቅ የልጆችዋና የባልዋ ደስታ ለእናትና ሚስት የተከበረና የተቀደሰ ይሁን። 6Id., pp. 464, 465.AHAmh 176.2

  የሚያምርባችሁን ልብስ ልበሱ፤ በልጆቻችሁ ዘንድ አክብሮት ይጨምርላችኋል። ልጆቻችሁ የሚስማማ ልብስ መልበሳቸውን ልብ በሉ። ወደ ዝርክርክነትና ንጽህና የጎደለው ልማድ እንዲዘፈቁ አትፍቀዱላቸው። 7Letter 47a, 1902.AHAmh 176.3

  በአካባቢው አመለካከት የታሰራችሁ አትሁኑ፦ አብዛኛውን ጊዜ እናቶች በልማዳቸው በአለባበሳቸውና በሚሰጡት አስተያየት ሁሉ ሌሎች ምን ይሉ ይሆን ብለው የመብከንከን በሽታ አለባቸው። የምን-ይሉኝ ባርያ አስኪሆኑ ድረስ ስለሌሎች ይጨነቃሉ። ለእግዚአብሔር ባለባቸው የኃላፊነት ሃሳብ ከመያዝ ይልቅ ፍርድ የሚጠብቃቸው ፍጡራን ጎረቤቶቻችን ምን ይሉ ይሆን በሚለው ሃሳብ ቁጥጥር ሥር ሲሆኑ አያሳዝንም? መሳለቂያ ከመሆን ለማምለጥ ስንል ከልማድ ጋር በመስማማት ብዙውን ጊዜ እውነትን መስዋዕት እናደርገዋለን….AHAmh 176.4

  እናት በይሉኝታ ትታሰር ዘንድ አይቻላትም፤ ልጆችዋን ለዚህ ሕይወትና ለሚመጣው ዓለም ማሠልጠን አለባትና። እናቶች ባላስፈላጊ መሽቆጥቆጥና እዩኝ እዩኝ በሚል ስሜት ልብስ መልበስ የለባቸውም። 8Review and Herald, March 31, 1891.AHAmh 176.5

  የጽዳትና የንጽህና ትምህርት መስጠት አለባችሁ፦ እናቶች የቆሸሸ ልብስ፣ ቤት ውስጥ የሚለብሱ ከሆነ ተመሳሳይ ድርጊት እንዲደግሙ መንገድ በመክፈት ልጆቻቸውን ዝርክርክነትና ቆሻሻን ያለመጸየፍ ልማድ ያስተምራሉ። ቤት ውስጥ እስከሆኑ ድረስ ምንም ዓይነት ልብስ፣ በቆሻሻ ብዛት አፈር የመሰለም ይሁን የተቀደደ በቂ ነው ብለው የሚያስቡ እናቶች ብዙ ናቸው። ሳይቆዩ ግን በቤተሰቡ ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ ያጣሉ። ልጆች የእናታቸውን የምን-ግዴ አለባበስ በንጽህና ከሚለብሱ ሌሎች ሴቶች ጋር በማወዳደር ለርስዋ ያላቸው ከበሬታ ይቀንሳል። እናቶች ሆይ የምትችሉትን ያህል ውብ ለመሆን ሞክሩ፤ እንከን የለሽ የስፌት መስመር በማውጣትና በማንቆጥቆጥ ሳይሆን ገጣሚና ንጹህ የሆነ ልብስ በመልበስ ይመርባችሁ። እንዲህም ሲሆን ለልጆቻችሁ የንጽህናና የጽዳት ቋሚ ትምህርት መስጠት ትችላላችሁ። የልጆችዋ ፍቅርና አክብሮት ለእናት ከምንም በላይ ዋጋ የምትሰጠው ሊሆን ይገባል። በሰውነትዋ ላይ የሚያርፍ ማንኛውም ነገር ጽዳትንና ሥርዓትን ያስተምር ዘንድ በአዕምሮአቸው ከንጽህና ጋር እንዲዛመድ መርዳት አለባት። ሃሳቦችን እንዳሉ የመቀበልና ሁሉም ነገር መልካም እንደሆነ አድርጎ መውሰድ የእያንዳንዱ ሕፃን ባህርይ ነው። ታዲያ ዓይናቸው በየቀኑ በቆሻሻ ልብስና በተዝረከረከ ክፍል እያረፈ እንዴት ነው የንጽህናንና የቅድስናን አስፈላጊነት በአእምሮአቸው ልትቀርጽ የምትችለው? እንዴት ነው ሁሉም ነገር ንጹህና ቅዱስ ከሆነበት ሰማይ የመጡትን እንግዶች [መላእክትን] እንደዚህ አይነት ቤት ውስጥ እንዲገቡ የምትጋብዛቸው? 9Christian Temperance and Bible Hygiene, pp. 143, 144.AHAmh 177.1

  ሥነ-ሥርዓትና ንጽህና የሰማይ ሕጎች ናቸው። ከመለኮታዊ አደረጃጀት ጋር ለመስማማት ንጹህና ማራኪ መሆን የእኛ ፋንታ ነው። 10Testimonies for the Church, Vol. 4, pp. 142, 143.AHAmh 177.2

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents