Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የአድቬንቲስት ቤት - Contents
 • Results
 • Related
 • Featured
No results found for: "".
 • Weighted Relevancy
 • Content Sequence
 • Relevancy
 • Earliest First
 • Latest First
  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents

  ክፍል 9—አባት-የቤት ማገር

  ምዕራፍ ሠላሳ አራት—የአባት ደረጃና ኃላፊነቶች

  ትክክለኛው የባል ትርጉም፦ ቤት የእግዚአብሔር ተቋም ነው። በቤተሰብ ክበብ አባት፣ እናትና ልጆች በዚህ ዓለም አንድ ተቋም ሆነው እንዲኖሩ የእግዚአብሔር እቅድ ነው። 1Manuscript 36, 1899.AHAmh 145.1

  ቤትን ደስተኛ የማድረጉ ሥራ ለእናት ብቻ የሚተው አይደለም። አባትም አስፈላጊ ድርሻ አለው። ባል በኃይለኛ የህብረት ሰንሰለት የቤተሰቡን አባላት የሚያቆራኝ፤ በጠንካራ፣ ልባዊ በሆነና በተሰጠ ፍቅር ጠፍሮ የሚይዝ የቤት ማሰሪያ ማገር ነው። 2Signs of the times, Sept 30, 1877.AHAmh 145.2

  ስሙ “የቤት ማገር (House-band)” ሲሆን የባል ትክክለኛ ትርጉም ነው። ሆኖም እጅግ ጥቂት ወንዶች ብቻ ኃላፊነታቸውን እንደሚያውቁ አይቻለሁ። 3 Testimonies for the Church, Vol. 1, p. 547.AHAmh 145.3

  የቤተሰብ ኩባንያ መሪ፦ ባልና አባት የቤተሰቡ ራስ ነው። እናት ለፍቅሩ፣ ለርኅራኄውና ልጆችን በማሠልጠን በኩል ዕርዳታ ፍለጋ ወደ እርሱ ትመለከታለች፤ ይህም ትክክል ነው። ልጆች የእርስዋ የሆኑትን ያህል የእርሱም ናቸውና የደህንነታቸው ጉዳይ በእኩል ይመለከተዋል። ልጆች ለድጋፍና ለምሪት ወደ አባታቸው ይመለከታሉ። አባት በቤተሰቡ ዙሪያ ስላለው ህብረት ተጽዕኖ እንዲሁም ሕይወት በአጠቃላይ ትክክለኛ ንድፈ-ሐሳብ ሊኖረው ይገባል። ከሁሉም በላይ ደግሞ የልጆቹን እግሮች በትክክለኛው ጎዳና መምራት ይችል ዘንድ በፈሪሃ-እግዚአብሔርና በፍቅሩ እንዲሁም በመለኮታዊ ቃል ትምህርት ቁጥጥር ሥር ሊሆን ይገባዋል….AHAmh 145.4

  ቤትን ደስተኛ በማድረግ ረገድ አባት የድርሻውን መወጣት አለበት። ምንም ዓይነት ችግርና የሥራ ድንግርግሮሽ ቢኖሩበት፣ እነዚህ ነገሮች በቤተሰቡ ላይ ጥላ እንዲያጠሉ መፍቀድ የለበትም። የሚያምር ፈገግታና አስደሳች ቃላት ይዞ ወደ ቤት መግባት አለበት። 4Ministry of Healing, pp. 390, 392.AHAmh 145.5

  ሕግ አርቃቂና ካህን፦ አባት የሁሉም ቤተሰብ አባላት ማዕከል ነው። ሕግ አርቃቂ ነው። ኮስታራ የወንድነት ባህርያቱን - ኃያልነት፣ ሐቀኝነት፣ ታማኝነት፣ ትዕግሥት፣ ጀግንነትና ትጋት እንዲሁም ተግባራዊ ጠቀሜታ- በሚያረጋግጥ መልኩ ሕግ አርቃቂ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ባል የጠዋትና የማታውን መሥዋዕት በእግዚአብሔር መሠውያ ላይ የሚያኖር የቤተሰቡ ካህን ነው። እንደ ቅስናውም በጠዋት በማታ አባት በራሱና በልጆቹ፣ በቀን ውስጥ ስለሚፈጽሙት ኃጢአቶች ለእግዚአብሔር መናዘዝ አለበት። ያስተዋላቸው ኃጢአቶች እንዲሁም ምሥጢራዊ የሆኑት የእግዚአብሔር ዐይን ብቻ ሊያያቸው የሚችለውን ጥፋቶች መናዘዝ አለበት። ይህ ሥርዓት እርሱ ሲኖር በራሱ፤ ቤት በማይኖርበት ጊዜ ደግሞ በሚስቱ በቀናኢነት ከተተገበረ ለቤተሰቡ በረከት ይሆናል። 5Testimonies for the Church, Vol. 2, p. 701.AHAmh 145.6

  አባት ለቤተሰቡ መለኮታዊ ሕግ ሰጪ ነው። ንጹህና ደግ ባህርያትን መመሥረት ይችሉ ዘንድ ቀጥተኛ የሆኑትን መመሪያዎች በልጆች ውስጥ ለመትከል፣ የእግዚአብሔርን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ የሚጥር እርሱ፣ ከአምላክ ጋር በአንድነት የሚሠራ ነው። መታዘዝ በሚያስችለው ኃይል ነፍሱን አስይዟታልና ልጆቹ የምድራዊ ወላጆቻቸውን ብቻ ሳይሆን ሰማያዊ አባታቸውንም ጭምር መታዘዝ ይችላሉ። 6Signs of the Times, Sept. 10, 1894.AHAmh 146.1

  አባት የተቀደሰውን አደራ መክዳት የለበትም። ወላጃዊ ሥልጣኑን በምንም ዓይነት አሳልፎ መስጠት አይገባውም። 7Letter 9, 1904.AHAmh 146.2

  ከእግዚአብሔር ጋር መራመድ፦ ባመነበት በመኖር አባት ልጆቹን ከእግዚአብሔር መንበረ መንግሥት ጋር ያቆራኛቸዋል። በራሱ ኃይል ባለመተማመን ረዳት የሌለውን ነፍሱን በየሱስ ላይ አስቀምጦ የልዑሉን ኃይል ይጠቀማል። ወንድሞች ሆይ ለቤተሰባችሁ ሌትና ቀን ፀልዩ፤ በመኝታ ክፍላችሁ ልባዊ ፀሎት ፀልዩ፤ በዕለት ሥራችሁም ስትጠመዱ ነፍሳችሁን ለእግዚአብሔር ቀና አድርጉ። ሔኖክ እንደዚያ ነበረ ከእግዚአብሔር ጋር የተራመደው። በዝምታ ሆኖም ልብን በሚነካ ሁኔታ ነፍስ የምትፀልየው ጸሎት እንደ ቅዱስ እጣን ወደ ፀጋው ዙፋን በመውጣት፣ በቤተ-መቅደሱ ውስጥ እንደቀረበ ያህል በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ያገኛል። ለሚሹት ሁሉ ክርስቶስ በሚፈለግበት ሰዓት የሚገኝ ይሆናል። በፈተና ቀንም የበረቱ ይሆናሉ። 8Testimonies for the Church, Vol. 4, p. 616.AHAmh 146.3

  የልምድ ብስለት ያስፈልጋል፦ አባት በፍላጎት ብቻ እንደሚንቀሳቀስ ሕፃን ልጅ መሆን የለበትም። ከቤተሰቡ ጋር በተቀደሰ ትስስር የተቆራኘ ነው። 9Testimonies for the Church, Vol. 1, p. 547.AHAmh 146.4

  አባት ለብቸኛው እውነተኛ አምላክ፣ በላከውም የሱስ ክርስቶስ ያለው ዕውቀት በቤት ውስጥ የሚኖረውን ተጽዕኖ ይወስናል። “ሕጻን በነበርሁ ጊዜ” ይላል ጳውሎስ “እንደ ሕፃን እናገር ነበርሁ፣ እንደ ሕፃን አውቅ ነበርሁ፣ እንደ ሕፃንም አስብ ነበርሁ፣ ጎልማሳ ግን በነበርሁ ጊዜ የሕፃኑን ፀባይ ተውሁ።” አባት የቤተሰብ እራስነቱን መያዝ አለበት፤ በቁመት ብቻ እንደተንቀዋለለ ሥርዓት-አልባ ልጅ ሳይሆን ፍላጎቱን የተቆጣጠረ የጎልማሳ ባህርይ ያለው ሙሉ ሰው መሆን አለበት። ትክክለኛውን የግብረ-ገብነት ትምህርት ማግኘት አለበት። የቤት ውስጥ ሕይወት ጠባዩም በንፁሁ የእግዚአብሔር ቃል መርሆዎች መሠረት አቅጣጫ የያዘና የተገደበ መሆን አለበት። እንዲህም ሲሆን በክርስቶስ ወደ ሙሉ ሰውነት ክብር ያድጋል። 10Manuscript 36, 1899.AHAmh 146.5

  ፈቃድህን ለእግዚአብሔር አስረክብ፦ አባትና ባል ለሆነው ሰው እላለሁ፡- ንፁህና ቅዱስ ሁኔታ ነፍስህን እንደከበቡት እርግጠኛ ሁን…. በየቀኑ ከክርስቶስ ተማር። የጭካኔ መንፈስ በቤት ውስጥ ፈጽሞ ዝር አይበል። ይህንን የሚያደርግ ወንድ ከሰይጣን ወኪሎች ጋር በህብረት የሚሠራ ነው። ፈቃድህን ለእግዚአብሔር ፈቃድ ለማስረከብ ፈቃደኛ ሁን። ያለህን ኃይል ሁሉ ተጠቅመህ የሚስትህን ሕይወት ውብና ደስተኛ አድርገው። የእግዚአብሔርን ቃል እንደ አማካሪህ ሰው አድርገህ ውሰደው። ቃሉ የሚያስተምረውን በቤትህ ውስጥ ተግብረው። ከዚያም በቤተ-ክርስቲያንና በመሥሪያ ቤትህ ታንፀባርቀዋለህ። የሰማይ መመሪያዎች ሁሉንም ግብይትህን በክብር ይሞላሉ። ክርስቶስን ለዓለም ትገልጽ ዘንድ መላእክት ከአንተ ጋር ይሠራሉ። 11Letter 272, 1903.AHAmh 146.6

  ቁጣው ቶሎ ለሚገነፍልበት ባል የሚገጥም ፀሎት፦ የሥራህ ብስጭቶች በትዳር ሕይወትህ ውስጥ ጽልመትን እንዲያመጡ አትፍቀድላቸው። ጥቃቅን ነገሮች ሁሉ አንተ እንደምታስባቸው ሳይሆኑ ሲቀሩ ቻይ መሆን፣ ትዕግሥት፣ ቸርነትና ፍቅር ማሳየት ካቃተህ ከእርሱ ጋር ትሆን ዘንድ ሕይወቱን ከሰጠህ፣ እጅግ ከወደደህ ከጌታ ጋር ጓደኝነት ለመመሥረት አልፈለግህም ማለት ነው። AHAmh 147.1

  በዕለት ተዕለት ሕይወትህ የሚያስደነግጡ፣ ቅር የሚያሰኙና የሚፈትኑ ሁኔታዎች ይገጥሙሃል። ቃሉ ምን ይላል? “ሰይጣንን ተቃወሙ[ተቃወመው]” በእግዚአብሔር በፍፁም በመደገፍህ ምክንያት “ከእላንትም[ከአንተም] ይሸሻል። ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ[ቅረብ] እርሱም ወደ እላንት[አንተ] ይቀርባል።” “በጉልበቴ ግን ያጸናኛል ሠላም ያደርግልኛል።” ፈቃዱን ማድረግ ታውቅ ዘንድ ወደ ጌታ ተመልከት፤ በምትሄድበት ሁሉ በማንኛውም ጊዜ በቅን ልብ ድምጽህን ሳታሰማ ፀልይ። ከዚያም ጠላት እንደ ጎርፍ ሲመጣብህ ትቃወመው ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ደረጃህን ከፍ ያደርገዋል። እጅ ለመስጠት በተቃረብህ ጊዜ፤ ትዕግሥት ስታጣ፤ እራስህን መቆጣጠር ሲሳንህ፤ መጨከንና ማውገዝ ሲፈታተኑህ፤ ጥፋት ለመፈለግና ለመኮነን ስትቃረብ፤ ይህ ጊዜ ፀሎት ወደ ሰማይ የምትልክበት ሰዓት ይሁን። እንዲህ በል፡-“መራራነትን፣ ቁጣንና የክፋት አነጋገርን ሁሉ ከልቤ ነቅዬ ማውጣት እችል ዘንድ፣ ፈተናን መቋቋም እችል ዘንድ እግዚአብሔር ሆይ እባክህን እርዳኝ። የዋህነትህን፣ ትህትናህን፣ ትዕግሥተኝነትህንና ፍቅርህን እባክህ ስጠኝ። የባለቤቴንና የልጆቼን እንዲሁም በእምነት ያገኘኋቸውን የወንደሞቼንና የእህቶቼን ሐሳብና ንግግር በስህተት እተረጉም ዘንድ፣ አዳኜንም አዋርድ ዘንድ እባክህ አትተወኝ። ቸር፣ አዛኝ፣ ሩኅሩኅና ይቅር-ባይ እንድሆን አግዘኝ። የክርስቶስን ባህርይ ለሌሎች ማሳየት እችል ዘንድ የቤቴ እውነተኛ ማገር እንድሆን እባክህ እርዳኝ።” 12Letter 105, 1893.AHAmh 147.2

  ሥልጣናችሁን በትህትና ተግብሩት፦ ባል እንደ ቤት እራስነቱ ሁልጊዜ ተኮፍሶ መኖሩ የወንድነት መገለጫው አይደለም። ሥልጣን እንደተሰጠው ከመጽሐፍ ቅዱስ ቃል እያጣቀሰ እራሱን ሲያዋድድ መሰማቱ ለእርሱ ምንም ክብር አይጨምርለትም። እቅዶቹ ሁሉ ሃኬት-የለሽ እንደሆኑ ሁሉ ባለቤቱ፣ የልጆቹ እናት ያለጥያቄ እንድትፈጽማቸው ማስገደዱ ወንድነቱን በበለጠ ሊያስመሰክርለት አይችልም። እግዚአብሔር ባልን የሚስት ራስ አድርጎ የሾመው ጠባቂዋ እንዲሆን ነው፤ ክርስቶስ የቤተ-ክርስቲያን ራስ፣ የረቂቁ ሰውነት አዳኝ እንደሆነ ባልም ቤተሰቡን አቅፎ የሚይዝ የቤት ማገር ነው። እግዚአብሔርን እወደዋለሁ የሚል ባል ሁሉ የተሰጠው ቦታ መስፈርቶች ምን እንደሆኑ በጥንቃቄ ይመርምር። የክርስቶስ ሥልጣን የሚተገበረው በበዛ ጥበብ ቸርነትና የዋህነት ነው፤ ባልም ሥልጣኑን ሲጠቀም እንደ ታላቁ የቤተ-ክርስቲያን ራስ ይሁን። 13Letter 18b, 1891.AHAmh 147.3

  Larger font
  Smaller font
  Copy
  Print
  Contents