Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የአድቬንቲስት ቤት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ሁለት—የእውነተኛ ቤት መሠረታዊ መመሪያዎች

    በዓለም በጣም ማራኪ የሆነው ሥፍራ፦ ወላጆች የልጆቻቸውን የወደፊት ደስታና ፍላጎት በጥንቃቄ በመጠበቅ ረገድ ከባድ ኃላፊነት የወደቀባቸው ቢሆንም በተቻለ መጠን ቤታቸውን ማራኪ የማድረግ ግዴታም አለባቸው። ይህ የሚያስከትለው ውጤት ርስትና ገንዘብ ከማግኘት የላቀ ነው። ቤት የፀሐይ ብርሃን ሊጎድለው አይገባም። ዞር ብለው ልጅነታቸውን ሲያስታውሱ ከሰማይ ቀጥሎ የሠላምና የደስታ ቦታ እንደነበረ እንዲያስቡ የቤት ስሜት በልጆች ልብ ውስጥ ተቀርጾ አብሯቸው ሊያድግ ይገባል። ወደ ጉልምስናም ሲመጡ በተራቸው ለወላጆቻቸው መጽናኛና በረከት ይሆኑ ዘንድ ይገባቸዋል።1Review and Herald, Feb. 2, 1886.AHAmh 7.1

    ቤት ለልጆች በዓለም እጅግ ማራኪው ቦታ ሊሆንላቸው ይገባል፤ የእናት መገኘትም ማራኪነቱን ወደር የሌለው ያደርገዋል። ልጆች በተፈጥሮአቸው አዛኝና አፍቃሪ ናቸው። በቀላሉ ይደሰታሉ፤ በቀላሉም ሊከፉ የሚችሉ ናቸው። በጨዋ ሥነ-ሥርዓት በፍቅር ቃላትና ተግባር እናቶች ልጆቻቸውን ከልባቸው ጋር ማቆራኘት ይችላሉ።2Ministry of Healing, p. 388.AHAmh 7.2

    የፀዳ፣ ንጹሕና ሥርዓትን የጠበቀ፦ ንጽህናና ጽዳት እንዲሁም ሥርዓት ለትክክለኛ የቤተሰብ አስተዳደር አስፈላጊዎች ናቸው። ነገር ግን እናት እነዚህን ተግባራት የሕይወትዋ ሁሉ አስፈላጊ መርሆዎች አድርጋ ሳትወስድ ስትቀር እንዲሁም ራስዋንም አሳልፋ በመስጠት የልጆችዋን የአካላዊ እድገት፣ የአዕምሮና የግብረ-ገብነት ሥልጠና ቸል ስትል አሳዛኝ ስህተት ትሠራለች።3Signs of the Times, Aug. 5, 1875.AHAmh 7.3

    አማኞች ሊማሩት የሚገባ ነገር ቢኖር (ምንም እንኳ ድሆች ቢሆኑም)፤ በግል ንጽህናቸው፣ በቤታቸው ጽዳትና አያያዝ እድፋምና ዝርክርክ መሆን የለባቸውም። በዚህ ረገድ የንጽህና አስፈላጊነትና ትርጉሙ ላልገባቸው እርዳታ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ከፍ ያለውን ቅዱስ እግዚአብሔርን የሚወክሉ ሁሉ ነፍሳቸውን ያልተበረዘና ንጹህ አድርገው መጠበቅ እንዳለባቸው መማር ይገባቸዋል። ይህ ንጽህናም በልብሳቸው እንዲሁም በቤታቸውውስጥ ባለ ነገር ሁሉ ላይ ሊተገበር ይገባዋል። እንዲህም ሲሆን እውነት በሕይወታችን ላይ ለውጥ እንዳመጣ፤ ነፍሳችንን እንዳነፃውና ምርጫችንን እንዳስተካከለው የሚያገለግሉን መላእክት ማስረጃ ይኖራቸዋል። እውነትን ከተቀበሉ በኋላ በንግግር ወይም በጠባይ በአለባበስ ወይም በአካባቢያቸው ለውጥ የማያሳዩ እነርሱ ለራሳቸው ይኖራሉ፤ ለክርስቶስ አይደለም። ለንጽህናና ለቅድስና በየሱስ ክርስቶስ እንደገና እንደ አዲስ አልተፈጠሩም።4Review and Herald, June 10, 1902.AHAmh 7.4

    ንጽህናን ቸል ማለት በሽታን ያመጣል። ህመም ያለ ምክንያት አይመጣም። ፍጹም ጤናማ ናቸው ተብለው በሚታመኑት መንደሮችና ከተሞች ኃይለኛ የትኩሳት ወረርሽኞች ተከስተዋል። እነዚህም የህብረተሰቡ አደረጃጀት እንዲናጋ ወይም ሰው እንዲሞት ምክንያት ሆነዋል። በብዙ አጋጣሚዎች የወረርሽኙ ተጠቂዎች የሆኑት ሰዎች ለጥፋቱ ምክንያት የሆኑትን፤ ገዳይ የሆነ መርዝ ወደ ህዋ የሚለቁትን ተህዋስያን ተሸክመው ተገኝተዋል። እነዚህ ጀርሞች የቤተሰብ አባላትና ጎረቤቶች ወደ ውስጥ በሚተነፍሱበት ጊዜ ወደ ሰውነት የሚገቡ ናቸው። በንዝህላልነትና በቸልተኛነት ምክንያት በጤና ላይ የተከሰተውን ቀውስና የተስፋፋውን ድንቁርና መመልከት ያስገርማል።5Christian Temperance and Bible Hygiene, pp. 105, 106.AHAmh 8.1

    ሥርዓት ለደስተኛ ቤት አስፈላጊ ነው፦ በማንም ላይ የሚታይ ዝርክርክነት ቸልተኛነትና ጥንቁቅ አለመሆን ጌታን አያስደስተውም። እነዚህ ጉድለቶች ከባድ ጥፋቶች ናቸው። በሥርዓት የተቀጡ ልጆችንና ጥሩ ቁጥጥር ያለውን ቤት ለሚወድ ባል የእነዚህ ነገሮች መጓደል ለሚስቱ ያለውን ፍቅር እንዲቀንስ የሚያደርጉት ናቸው። አንዲት ሚስትና እናት ሥርዓትን የማትወድ ከሆነ፤ ክብሯን የማትጠብቅ ከሆነና፤ ጥሩ አስተዳደግ ከሌላት፤ ለቤተሰቧ መስማማትንና ደስታን ልታመጣ አትችልም። በነዚህም ነጥቦች ግድፈት ያለባቸው ሁሉ ወዲያውኑ እራሳቸውን ማስተማር መጀመር አለባቸው። ጉድለታቸው ብሶ በሚታይበት ጎን የበለጠ በመሥራት ለማሻሻል መጣር ይኖርባቸዋል።6Testimonies for the Church, Vol. 2, pp.298, 299.AHAmh 8.2

    ንቃትና ትጋት ሊዋሐዱ ይገባል፦ ያልተገደበ እኛነታችንን ለጌታ አሳልፈን እንስጥ፤ ቀላሎቹና የተለመዱት የትዳር ሕይወት ሥራዎች አስፈላጊነት ቁልጭ ብሎ ይታየናል። እንደ እግዚአብሔር ፈቃድም እናከናውናቸዋለን። ንቁ ልንሆን ይገባናል። የሰውን ልጅ ተመልሶ መምጣት በመጠባበቅ ትጉህም ልንሆን ይገባል። እየሠራን ልንጠባበቀው አስፈላጊ ነው። የሁለትዮሽ ህብረት ጠቃሚ ነው። ይህም የክርስቲያንን ጠባይ ሚዛናዊ፣ በደንብ የጎለበተና የተስማማ ያደርገዋል። ሌሎች ነገሮችን ሁሉ ችላ ብለን ጊዜያችንን ሁሉ በጥልቀት ለማሰብ፤ ለጥናትና ለጸሎት ብቻ መስጠት አይኖርብንም። የግል ቅድስናን በመተው ሽርጉድ ባዮች ጥድፊያና ሥራ የበዛብንም ልንሆን አይገባም። መጠባበቃችን ጥንቃቄያችንና ሥራችን ክትትልና ውህደት ያስፈልጋቸዋል - “በሥራም አትስነፉ በመንፈሳችሁ የምትቃጠሉ ሁኑ ለእግዚአብሔርም የተገዛችሁ።” 7Review and Herald, Sept. 15, 1891.AHAmh 8.3

    ከእንግልት የሚያድኑ ነገሮችን ማሟላት፦ በብዙ ትዳር ውስጥ ባለው የሥራ ጫና ምክንያት ሚስትና እናት ለማንበብና ለራስዋ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ እንዲኖራትና የባልዋ ጓደኛ እንድትሆን የሚያደርጋት፤ የልጆችዋንም የሚጎለምስ አዕምሮ መከታተል የሚያስችላት በቂ ጊዜ የላትም። ክቡር አዳኙ ቅርብና ውድ ጓደኛዋ የአድቬንቲስት ቤት እንዲሆን ጊዜና ቦታ አታገኝም። ቀስ በቀስ ወደ ቤተሰብ ባርያነት ትሰምጣለች፤ ኃይልዋ ጊዜዋና ፍላጎትዋ ሁሉ ተገልግለንባቸው በሚያልቁ ነገሮች ይወሰዳል። ነገር ካለቀ በኋላ ስትነቃም ራስዋን በቤትዋ እንግዳ ሆና ታገኘዋለች። በአንድ ወቅት የራስዋ የነበረው የማይገኝ የከበረ እድል፤ ውድ ልጆችዋ ወደ ከፍተኛው ሕይወት እንዲመጡ ተጽዕኖ ማሳደር የምትችልበት ያ ዋጋ የማታገኝለት እድልዋን ሳታዳብረው ለዘለዓለም ባክኖ ይቀራል።AHAmh 8.4

    ቤት መሥራቾች በብልህ እቅድ የሚመሩ ይሁኑ። የመጀመሪያ ዓላማችሁ የሚያስደስት ትዳርን መፍጠር ይሁን። ጤናን የሚያሻሽሉና የሥራን ሸክም የሚያቃልሉ ሁኔታዎችን ለማቅረብ ቁርጠኞች ሁኑ።8Ministry of Healing, pp. 368, 369.AHAmh 9.1

    ተራ የሚመስሉ ተግባራት እንኳ የእግዚአብሔር ሥራዎች ናቸው፦ ልንሠራው የሚያስፈልገን ማንኛውም ሥራ ማለትም እንደ ድስት ማጠብ፣ ጠረጴዛ ማስተካከል፣ የታመመን መርዳት፣ ማብሰል ወይም እንደ ልብስ ማጠብ ያሉ ጥቃቅን ተግባራት ሁሉ የግብረ-ገብነት አስፈላጊነት አላቸው። እነዚህ በፊታችን የምናያቸው ጥቃቅን ሥራዎች ግዴታ መከናወን ያለባቸው ናቸው። የሚተገብሯቸው ሰዎችም ጠቃሚና የከበሩ ሥራዎችን እያከናወኑ እንደሆነ ሊሰማቸው ይገባል። ተልዕኮአቸው ምንም እንኳ ዝቅተኛ ቢመስል፣ ልክ መልአኩ ገብርኤል ወደ ነቢያት ሲላክ የሚሠራውን ያክል፣ በእርግጥም የእግዚአብሔርን ሥራ እየሠሩ ናቸው። ሁሉም በተሰለፉበትና በተመደቡበት ሙያ እያገለገሉ ናቸው። ሴቶች በቤታቸው ቀላል፣ ነገር ግን ሊሠሩ የሚያስፈልጉን ተግባራት ሲያከናውኑ መላእክት በሞያቸው እንደሚያደርጉት ሁሉ ታማኝነትን፣ መታዘዝንና ፍቅርን ሊያሳዩ ይገባቸዋል። ሊሠራ የሚገባው ማንኛውምሥራ ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር የሚጣጣም ከሆነ እርሱ የከበረ ሥራ ነው።9Testimonies for the Church, Vol. 3, pp. 79, 80.AHAmh 9.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents