Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የአድቬንቲስት ቤት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ክፍል ፬—የውጤታማነት ወይም የውድቀት ምክንያቶች

    ምዕራፍ አሥራ አንድ—ችኩል፤ በቂ ጊዜ ያልተወሰደበት ጋብቻ

    የልጅነት ቁርኝት አደጋዎች፦ የልጅነት ጋብቻን ልናበረታታ አይገባም። እንደ ጋብቻ ያለ እጅግ አስፈላጊ ውጤቱም ሰፊ የሆነ ግንኙነት፣ በበቂ ሁኔታ ሳይታሰብበት፤ የአዕምሮ ብስለትና የአካል እድገት በበቂ ሁኔታ ሳይደረጅ በችኮላ ሊፈፀም አይገባም።1Ministry of Healing, p. 358.AHAmh 47.1

    በለጋ ዕድሜ ያሉ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወደ ጋብቻ የሚገቡት ፍቅራቸው ሳይበስል፤ አመለካከታቸው ሳይጎለብት፤ ያለ ጥልቅና ጨዋ ስሜት ሲሆን የጋብቻንም ቃል-ኪዳን የሚያጠልቁት በልጅነት በሚሰማቸው ጠንካራ ፍላጎት ብቻ ተመርተው ነው….AHAmh 47.2

    ገና በልጅነት የተመሠረቱ ጥምረቶች ውጤታቸው ብዙ ጊዜ ሰቆቃ የተሞላበት ትዳር ወይም በሚያዋርድ ሁኔታ በፍች የተበተኑ ናቸው። የወጣትነት ግንኙነቶች ያለ እናት አባት ፈቃድ የተመሠረቱ ከሆነ ደስተኛ የመሆናቸው እድል በጣም የጠበበ ነው። ወደ አስፈላጊው የዕድሜ ክልል እስከሚደርሱ በቂ ልምድ አካብተው ጋብቻን በከበረ ሁኔታ ሊፈጽሙ እስከሚችሉበት ጊዜ ድረስ የወጣቶች ፍላጎት ሊገታ ይገባዋል። ጥብቅ ቁጥጥር የማይደረግባቸው ሁሉ ደስታ የሌለው ኑሮ የመኖርAHAmh 47.3

    አደጋ ተጋርጦባቸዋል። አንድ በአሥራ ቤት ውስጥ ያለ ወጣት በእርሱ ዕድሜ ክልል ያለችን ወጣት የቀሪ ሕይወቱ አጋር የመሆን ብቃት እንዳላት የመመዘን ችሎታው ዝቅተኛ ነው። ከተጋቡ በኋላ የማመዛዘን ችሎታቸው እየጎለበተ ሲሄድ አብረው የመኖራቸው ጉዳይ ዕጣ ፈንታቸው [የአርባ ቀን ዕድላቸው] እንደሆነ በመቁጠር በስሜት ግፊት የተቆራኙ እንጂ ምን አልባትም ለእርስ በእርሳቸው ደስታ ለመፍጠር የተገናኙ እንዳልሆኑ አድርገው ያስባሉ። ዕድላቸውን በፀጋ ተቀብለው ሊሻሻሉ የሚችሉትን ነገሮች ለመለወጥ ከመሞከር ይልቅ መወነጃጀል ይጀምራሉ፤ ልዩነት እየሰፋ ሄዶ ለእርስ በእርሳቸው የሚያሳዩት ቸልተኝነትና ግድ-የለሽነት የተለመደ ክስተት ይሆናል። ለእነርሱ “ትዳር” በሚለው ቃል ውስጥ ምንም የተቀደሰ ነገር የለም። ትስስራቸው በጥላቻ ንግግር የተመረዘና በመሪር ወቀሳ የተሞላ ይሆናል።2Messages to Young People,, p. 452.AHAmh 47.4

    ዛሬ እንደዚህ በዝቶ የምናየው ክፋት ያልበሰሉ ጋብቻዎች ውጤት ነው። ገና በልጅነት በተፈጸመ ጋብቻ የአካል ጤንነትም ሆነ የአዕምሮ ጥንካሬ አይሻሻልም። በዚህ ጉዳይ ላይ አሳማኝ ያልሆነ ምክንያት ይቀርባል። ብዙ ወጣቶች በስሜት ተነሥስተው ነው ይህንን ተግባር የሚፈጽሙት። ይህን ለመልካም ወይም ለክፉ የሚዳርጋቸውን፤ ለዕድሜ-ልካቸው በረከት ወይም እርግማን የሚሆንባቸውን ጋብቻ በችኮላና በስሜት ተገፋፍተው ያደርጉታል። ብዙዎቹ ከክርስትና አንጻር የሚነገራቸውን መመሪያ ወይም ምክንያት አይሰሙም።3Id., p. 453.AHAmh 47.5

    ልምድ የሌላቸው ወጣቶች ወደ ጋብቻ ህብረት በጥድፊያ እንዲገቡ በማድረግ ሰይጣን በሥራ ተጠምዷል። በአሁኑ ጊዜ እየተፈጸሙ ያሉትን ጋብቻዎች ባናሞጋግሳቸው ይሻለናል።4Testimonies for the Church, Vol. 2, 252.AHAmh 48.1

    በጥድፊያ በሚፈፀሙ ጋብቻዎች ምክንያት በእግዚአብሔር ሰዎች መካከል እንኳ መለያየት፣ መፋታትና በቤተ-ክርስቲያንም ከፍተኛ ድንግርግር እየተከሰተ ነው።5Review and Herald, Sept. 25, 1888.AHAmh 48.2

    ይስሐቅ በተከተለው መንገድና የዚህ ዘመን ወጣቶች፣ ጠንካራ ክርስቲያኖች ጭምር፣ በሚመርጡት መንገድ መካከል ምን ያህል ልዩነት አለ! አብዛኛውን ጊዜ ወጣቶች የጋብቻ ፍላጎታቸው እራሳቸው ብቻ የሚወስኑት እንጂ ወላጆቻቸው ወይም እግዚአብሔር በምንም ዓይነት ሊቆጣጠራቸው እንደማይገባ ያስባሉ። ለአካለ-መጠን ሳይደርሱ ያለ ወላጆቻቸው እርዳታ የራሳቸውን ምርጫ ለማካሄድ ብቁ እንደሆኑ ይሰማቸዋል። ስህተታቸውን ለማየት የጥቂት ዓመታት የጋብቻ ቆይታቸው በቂ ነው፤ ክፉ መዘዙን ለማስቀረት ግን የማይችሉት ይሆናሉ። ችኩል የጋብቻ ውሳኔ እንዲያደርጉ ያስገደዳቸው የጥበብና እራስን የመግዛት እጦት፣ ቀጣዩ ህይወታቸውም ክፋትን እንዲያባብስ ፈቅደውለት በመጫረሻም ትዳራቸው የሚያዋርድ ቀንበር ይሆንባቸዋል። በዚህም ምክንያት ብዙዎቹ በዚህ ሕይወት ያላቸውን ደስታና ለሚመጣው ሕይወታቸው ያላቸውን ተስፋ አጨልመዋል።6Patriarchs and Prophets, p. 175.AHAmh 48.3

    ለእግዚአብሔር ሠራተኞች ሊሆኑ ይችሉ የነበሩ ይተበተባሉ፦ እውነትን የተቀበሉ፤ በአንድ ወቅትም በመንገዱ የተራመዱ ወጣቶች አሉ። ነገር ግን ሰይጣን ማስተዋል በጎደለው ቁርኝትና ችግር በበዛበት የጋብቻ መረብ ተብትቦ ያስቀራቸዋል። በዚህ አካሄዱ ከምንም በላይ ውጤታማ እንደሚሆንና በማታለል ከቅድስና መንገድ ሊያስወጣቸው እንደሚችል አረጋግጧል።7Testimonies for the Church, Vol. 5, pp. 114, 115.AHAmh 48.4

    የዚህ ዘመን ወጣቶች የተጋረጠባቸውን ከባድ አደጋ በቅጡ እንደማያውቁት አየሁ። እግዚአብሔር በተለያየ የሥራ መስክ ሊያሰማራቸው የሚቀበላቸውን ሠራተኞች ሰይጣን ጣልቃ ይገባና በክፉ ተብትቦ ያደነባብራቸውና ከአምላክ ይለያቸዋል። ሊሠሩለት ለተጠሩትም ሥራ መቅናቸው የፈሰሰ ይሆናል። ሰይጣን እጅግ ብልህ፣ ኧህ የማይልና የማይሰለች ሠራተኛ ነው። ያልጠረጠሩትን እንዴት ማጥመድ እንደሚችል ጠንቅቆ ያውቃል፤ የሚያሳስበው ደግሞ ከዚህ ብልሃቱ የሚያመልጡት በጣም ጥቂቶች መሆናቸው ነው። አደጋ አይታያቸውም፤ ከወጥመዶቹም አይጠነቀቁም። የእግዚአብሔርን ወይም እንዲያስጠነቅቁ፣ እንዲገስጹና እንዲመክሩ የላካቸውን ጥበብ በመሻት ፈንታ ለእርስ በእርስ ያላቸውን ፍቅር እንዲጠብቁ ያደርጋቸዋል። በራስ መተማመናቸው አይሎ ለተግሳጽ ፈጽሞ አይንበረከኩም።8Id., p. 105, 106.AHAmh 48.5

    ምክር በአሥራ የዕድሜ ክልል ውስጥ ላሉ ወጣቶች፦ ለልጃገረዶች ያላችሁ የፍቅር አስተሳሰብ በሌሎች ዘንድ ብልህ አያስመስላችሁም፤ አዕምሮአችሁ በዚህ አቅጣጫ እንዲሮጥ መፍቀዳችሁ ለጥናት ያላችሁን ፍላጎት ይቀንስባችኋል። የተበላሸ ህብረት እንድትመሠርቱ ይመራችኋል፤ የእናንተም ሆነ የሌሎችን አካሄድ ያበላሻል። እንዲህ ሆኖ ነው የታየኝ። የራሳችሁን መንገድ ለመከተል አሻፈረኝ እስካላችሁ ድረስ ሊመራችሁ፤ ተጽዕኖ ሊያሳድርባችሁና ሊከለክላችሁ የሚፈልገውን ሰው ሁሉ በቆራጥ ውሳኔ ልትቃወሙት ትነሳላችሁ፤ ምክንያቱ ደግሞ ልባችሁ ከእውነትና ከጽድቅ ጋር ስምምነት ስለሌለው ነው።9Manuscript 15a, 1896.AHAmh 49.1

    የዕድሜ አለመመጣጠን፦ ጓደኛሞቹ ዓለማዊ ሀብት አይኖራቸው ይሆናል፣ የጤናማነት በረከት ግን በእጅጉ ያስፈልጋቸዋል። በአብዛኛው በዕድሜ የሰፋ ልዩነት ሊኖር አይገባም። ይህንን ሕግ ችላ ማለት በዕድሜ የሚያንሰው ወገን ላይ ከባድ የጤና ጉዳት ሊያስከትል ይችላል፤ በመሆኑም ብዙ ጊዜ የሚወለዱት ልጆች የአካልና የአዕምሮ ጥንካሬ ይነፈጋሉ። የወጣትነት ሕይወታቸው የሚጠይቀውን እንክብካቤና ጓደኝነት ያህል በዕድሜ ከገፋ/ች/ ወላጃቸው ማግኘት አይችሉም። የወላጅ ፍቅርና ምሪት በሕይወታቸው በጣም በሚያስፈልግበት ዕድሜ ክልል እያሉም እናታቸውን ወይም አባታቸውን በሞት ሊነጠቁ ይችላሉ።10Ministry of Healing, p. 358.AHAmh 49.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents