Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የአድቬንቲስት ቤት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ ሠላሳ አምስት—ሸክምን መጋራት

    የአባት ኃላፊነት ሊተላለፍ አይችልም፦ አባት ለልጆቹ ያለበት ኃላፊነት ወደ እናት ሊተላለፍ አይችልም። እርስዋ መወጣት ያለባት የራስዋ በቂ ሸክም አላት። እግዚአብሔር በእጃቸው የተወውን ሥራ መፈፀም የሚችሉት ባልና ሚስት አንድ ሲሆኑ ብቻ ነው። 1Fundamental Beliefs of Christian Education, p. 69AHAmh 149.1

    አባት ልጆችን ለሕይወትና ለዘለዓለማዊነት ለማስተማር ከአለበት የኃላፊነት ድርሻ ራሱን ማግለል የለበትም። ኃላፊነትን መጋራት የግድ ያስፈልገዋል። ለእናትም ለአባትም ለሁለቱም ግዴታ አለባቸው። እነዚህ ባህርያት በልጆቻቸው እንዲጎለምሱ ከፈለጉ፣ በአባትና በእናት መካከል ያለው ፍቅርና መከባበር ሊገለጥ ይገባዋል። እናት ለምታከናውነው ልጆቻቸውን የመንከባከብ ሥራ፣ ባል ደስተኛ ፊት በማሳየትና በመልካም ንግግር ሚስቱን ያበረታታት፤ ያጽናት። 3Signs of the Times, Sept. 13, 1877.AHAmh 149.2

    በፊትዋ ላለው ተጋድሎ ባለቤትህን እርዳት፤ ለንግግርህ ተጠንቀቅ፤ የነጠረ ጠባይ፣ ደግነትና ጨዋነት አጎልብት፤ እንዲህ በማድረግህ ካሣ ይከፈልሃል። 4Testimonies for the Church, Vol. 2, p. 84AHAmh 149.3

    ደግ አገልግሎት የእናትን ሸክም ያቃልልላታል፦ ሥራው ምንም ዓይነት ይሁን፣ ምን ያህልም ግራ የሚያጋባ ይሁን፣ አባት ቀኑን ሁሉ ጎብኝዎችንና እንግዶችን ሲያናግርበት የዋለውን ፈገግታ የተሞላ ፊትና ለዛ ያለው የድምፅ ቃና ይዞ ወደ ቤቱ ይግባ። በተትረፈረፈው የባልዋ ፍቅር ሚስት መደገፍ እንደምትችል በምታልፍባቸው ችግሮችና ልፋቶችዋ ውስጥ ሁሉ ክንዱ እንደሚያበረታት፤ ተጽዕኖው እንደሚያድሳት፤ ሸክምዋ በግማሽ እንደሚቀንስ ሊሰማት ይገባል። እነዚህ ልጆች የእርስዋ እንደሆኑ ሁሉ የእርሱስ አይደሉምን? 5Christian Temperance and Bible Hygiene, p. 70.AHAmh 149.4

    የባልዋን ፈንታ ጭምር ለመሸከም ከምትሞክር፣ ሌሎች ኃላፊነቶችን ብትወጣ ሚስት የተሻለ ልትሠራ ትችላለች፤ ለባልም እንዲሁ ነው። ጨዋ የሆኑ አገልግሎቶች ዋጋ ያላቸው ናቸው። ባል ብዙ ጊዜ እንደፈለገ ከቤት የመውጣት፣ ተመልሶ ሲመጣም እንደ ቤተሰቡ ክበብ መሪ ሳይሆን እንደተሳፋሪ ዘው ብሎ በነፃነት ወደ ቤቱ የመግባት ዝንባሌ ይንፀባረቅበታል። 6Manuscript 80, 1898.AHAmh 149.5

    የቤት ውስጥ ሥራዎች አስፈላጊና የተቀደሱ ናቸው። ብዙውን ጊዜ ግን የሚሠራው አንድ የዛለ ሰው ብቻ ነው። ምንም ዓይነት ለውጥ ከሌለ፤ ባል ሁልጊዜ የሚያገኘውን ደስታ የተሞላበት መዝናኛ፣ ሚስት ማግኘት ካልቻለች፤ ማድረግ ያለበትን እየቻለ ሳይፈጽመው ከቀረ ወይም አስፈላጊ መሆኑ ካልተሰማው ስፍር ቁጥር የሌላቸው ችግሮችና ግራ የሚያጋቡ ነገሮች ተፈጥረው የሚያበሳጩ እየሆኑ ይመጣሉ። የተሸከመችውን ኃላፊነት አስቸጋሪነት ተረድቶ እርዳታ ካላደረገላት በስተቀር በየዋህነት የምትመራው ሕይወት የማያቋርጥ መስዋዕትነት የሚያስከፍላትና እጅግ እየከበደባት የሚ መጣ ይሆናል። 7Signs of the Times, Dec. 6, 1877.AHAmh 149.6

    ለደካማ ሚስትህ አስብላት፦ ባል ለቤተሰቡ ያለውን የላቀ ስሜት መግለጽ ይኖርበታል። ደካማ ለሆነች ሚስቱ ደግሞ የበለጠ ቢጠነቀቅላት የብዙ በሽታን በር ሊዘጋ ይችላል። ቸር፣ ደስታ የሞላባቸውና የሚያበረታቱ ቃላት በመፈወስ ችሎታቸው አንቱ ከተባሉ መድኃኒቶች በተሻለ ውጤታማ ናቸው። ይህ ለተከፋና ተስፋ ለቆረጠ ልብ መጽናናትን ያመጣል። በመልካም ተግባርና በሚያበረታቱ ቃላት ምክንያት ወደ ቤተሰቡ የመጣው ደስታና ብርሃን የድካሙን አሥር እጥፍ ይከፍላል። የልጆቻቸውን አዕምሮ የመቅረጽና የማሠልጠን አብዛኛው ሸክም በእናት ላይ የወደቀ መሆኑን ባል ማስተዋል ይገባዋል። ይህ ደግሞ ሊያራራው፣ ሊንከባከባትና ሸክምዋን ለማቅለል ሊያነሳሳው ይገባል። በፍቅሩ እንድትደገፍ ሊያበረታታት ይገባል። ለደከሙት ብርታትና ሠላም፤ ለዛሉት ዘለዓለማዊ ዕረፍት፤ ወደሚገኝበት ወደ ሰማይ ሊመራት ይገባዋል። የጠቆረ ፊት ይዞ ወደ ቤቱ መግባት የለበትም። የእርሱ መገኘት ለቤተሰቡ የፀሐይ ጮራ፣ ለሚስቱ ደግሞ እግዚአብሔርን እንድትፈልገውና እንድታምነው ብርታት ሊሆን ይገባዋል። እግዚአብሔር ቃል የገባውን እንዲፈጽምና የተትረፈረፈ በረከቱም ወደ ቤተሰባቸው እንዲመጣ በአንድነት መጋበዝ አለባቸው። 8Testimonies for the Church, Vol. 1, pp. 306, 307.AHAmh 150.1

    በእርጋታ ምሩ፦ ብዙ ባሎችና አባቶች ጥንቁቅና ታማኝ ከነበረው በግ ጠባቂ ጠቃሚ የሆነ ትምህርት ሊማሩ ይችላሉ። ፈጣንና አስቸጋሪ ጉዞ እንዲያደርግ በተገፋፋበት ጊዜ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ መለሰ፡- [አንተ ታውቃለህ ጌታ ሆይ] “ሕፃናት ጨቅላ ልጆች እንደሆኑ በጎችም ላሞችም ያጠባሉ። ሰዎች በመንገድ አስቸኩለው የነዷቸው እንደሆን በአንድ ቀን እንሰሶች ሁሉ ይሞታሉ።” “እያዘገምሁ እከተላለሁ እንደ እንሰሶችም ሕፃናትም እርምጃ መጠን።”AHAmh 150.2

    የጉዞ አጋሩ እንደምትችለው መጠን በዚህ አድካሚ ሕይወት ባልና አባት “እያዘገመ ይምራ።” ለሀብትና ለሥልጣን በሚሮጥበት በዚህ ዓለም ዝግ ብሎ መራመድን፤ ከጎኑ ትቆም ዘንድ ለተጠራችው ምችቶትና አጋዥ መሆንን ይማር….AHAmh 150.3

    ባል በርኅራኄውና በማይሞት ፍቅሩ ሚስቱን ያግዝ። ትኩስና ደስተኛ፣ በቤት ውስጥም እንደ ፀሐይ ብርሃን ሆና እንድትቆይ ምኞቱ ከሆነ ሸክምዋን መሸከም እንድትችል ይርዳት። ቸርነቱና አፍቃሪ ርኅራኄው ወደር የማይገኝለት ብርታት ይሆናታል፤ የሚያካፍላት ደስታም በአፀፋው ለልቡ ሐሴትንና ሠላምን ያመጣል….AHAmh 150.4

    እናት ልታገኘው የሚገባት እንክብካቤና ምቾት ከተነፈገች፤ በሥራ ብዛት ወይም በጭንቀትና በትካዜ እንድትዝለፈለፍ ከተተወች፤ ልጆችዋ መውረስ የሚገባቸውን፣ ለመኖር ያላቸውን ፍላጎት የሚፈጥረውን የአዕምሮ መነቃቃት ኃይል እንዲሁም የደስተኝነት መንፈስ ሳያገኙ ያድጋሉ። የእናትየዋን ሕይወት ብሩህና ደስተኛ በማድረግ፤ ከእጦት፣ ከአድካሚ ሥራና ከአስጨናቂ ችግሮች በመከለል፤ ልጆች መልካም የመተዳደሪያ ደንቦችን ወርሰው የራሳቸውን የሕይወት ጦርነት በኃይልና በታታሪነት እንዲዋጉ ማድረግ እጅግ የተሻለ ነው። 9Ministry of Healing, p. 374AHAmh 151.1

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents