Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
የአድቬንቲስት ቤት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ አርባ—የእናትን ሥራ በትክክል አለመረዳት

    ሥራዋ ጠቃሚ እንዳልሆነ ስሜትዋ ይፈታተናታል፦ ለእናት ብዙ ጊዜ ሥራዋ እርባና-ቢስ አገልግሎት ነው። እምብዛም የማይመሠገን ሥራ ነው። የርስዋን ችግሮችና ሸክሞች ሌሎች አያውቁላትም። ቀኖችዋ በሚደጋገሙ በጥቃቅን ሥራዎች የተሞሉ ናቸው። እነዚህ ሥራዎች ትዕግሥት አስጨራሽ ትጋትን፣ ራስን መግዛትን፣ ጥበብንና ራስን በመስዋዕትነት የሚያቀርብ ፍቅርን የሚጠይቁ ናቸው። ሆኖም ልትኮራበት የምትችለው ታላቅ ስኬት የላትም። ያደረገችው በቤት ውስጥ ያሉ ነገሮች በተሳካ ሁኔታ እንዲቀጥሉ ነው። በድካምና ግራ በመጋባት ውስጥም ሆና ልጆችዋን በደግነት ልታነጋግራቸው ትሞክራለች። በሥራ ልትጠምዳቸውና ደስተኛ ልታደርጋቸው ትጥራለች፤ እግራቸው በትክክለኛው መንገድ እንዲራመድ ትለፋለች፤ ሆኖም ምንም እንዳላከናወነች ይሰማታል። ነገር ግን እንደዚህ አይደለም። ሰማያዊ መላእክት በየዕለቱ የምትሸከመውን ሸክም እያስተዋሉ በችግር ያለቀችውን እናት ይመለከቷታል። ስሟ በዓለም ተሰምቶ አያውቅ ይሆናል፤ በበጉ የሕይወት መጽሐፍ ግን ተጽፏል። 1Counsels to Teachers, Parents and Students, p. 144.AHAmh 170.1

    እውነተኛዋ ሚስትና እናት…. ሥራዋን በኩራትና በደስታ ታከናውናለች፤ ሥርዓት ባለው ቤተሰብ ውስጥ የሚያስፈልገውን ሁሉ በራስዋ እጅ ማከናወንዋ የሚያዋርድ ሆኖ አታገኘውም። 2Signs of the times, Sept. 9, 1886.AHAmh 170.2

    ከሚሲዮናዊ አገልግሎት ያላነሰ ሥራ፦ እናትነት እንዴት አስፈላጊ ሥራ ነው! ሆኖም እናቶች ለሚሲዮናዊ አገልግሎት ሲያፏሽጉ ይታያሉ! ወደ አንድ እንግዳ አገር ወጥተው ቢያዩት ምን ያህል ዋጋ ያለው ሥራ እየሠሩ እንደነበር ይረዳሉ። ለዕለት ተዕለት የትዳር ኑሮ የሚያስፈልጉትን ሥራዎች መሥራት ግን አድካሚ ና ምሥጋና-የለሽ ነው ይላሉ። 3Review and Herald, July 9, 1901.AHAmh 170.3

    የመስክ ሚሲዮናዊ አገልግሎት ለመስጠት የሚያቃስቱ እናቶች ሁሉ ያን መስክ በቤታቸው ክበብ ውስጥ ያገኙታል….የማያምኑትንና መስክራ ልታድናቸው የምትፈልገውን ሰዎች ያህል ለልጆችዋ ነፍስ ዋጋ አትሰጠውም? በምን ዓይነት ገራምነትና እንክብካቤ ነው የሚያድገውን አዕምሮአቸውንና ሐሳባቸውን ከእግዚአብሔር ጋር የምታቆራኘው! እንደ አፍቃሪና እግዚአብሔርን ፈሪ እናት ይህንን ሥራ ማን ሊሠራ ይችላል? 4Manuscript 43, 1900.AHAmh 170.4

    በቀጥታ በኃይማኖታዊ ሥራ ላይ ካልተሳተፉ በስተቀር የእግዚአብሔርን ፈቃድ እያደረጉ እንዳልሆነ የሚሰማቸው አሉ፤ ይህ ስህተት ነው። እያንዳንዱ ለጌታ የሚሠራው ሥራ አለው፤ ቤትም አስደሳች መሆን ያለበትን ያህል ማራኪ ማድረግ ግሩም ምግባር ነው። ዝቅተኞቹ ተሰጥኦዎች እንኳ የተቀባዩ ልብ ለእግዚአብሔር የተሰጠ ከሆነ የትዳር ሕይወትን አምላክ እንደሚፈልገው ማድረግ ይችላሉ። በሙሉ ልብ ለእግዚአብሔር ከሚደረግ አገልግሎት የብርሃን ነፀብራቅ ወደ ፊት ያበራል። በሰሙት ነገር ልባዊ ትኩረትና ማስጠንቀቂያ ጭምር በመስጠት ልጆቻቸው እግዚአብሔርንAHAmh 170.5

    ከማስከፋት እንዲታቀቡ በማድረግ ሴቶችና ወንዶች መድረክ ላይ ወጥቶ የሚሰብከውን አገልጋይ ያህል እግዚአብሔርን ማገልገል ይችላሉ። 5Manuscript 72, 1899.AHAmh 171.1

    እጃቸው ያገኘውን ሁሉ በሙሉ ፈቃደኝነት ለመሥራት የሚተጉ፣ ባሎቻቸው ኃላፊነታቸውን እንዲሸከሙ የሚያግዙና ልጆቻቸውን ለእግዚአብሔር የሚያሠለጥኑ ሴቶች ናቸው በአገልግሎት ዘርፍ ከፍተኛውን ደረጃ የሚይዙት። 6Testimonies for the Church, Vol. 2, p. 466.AHAmh 171.2

    ኃይማኖታዊ ተግባራት የቤተሰቡን እንቅስቃሴ መተካት የለባቸውም፦ የእናትነትና የሚስትነት ኃላፊነትሽን ቸል ብለሽ፣ እጅሽን ዘርግተሽ፣ እግዚአብሔር ሌላ ዓይነት ሥራ እንዲሰጥሽ የምትጠብቂ እናት፣ ጌታ ራሱን እንደማይቃረን እርግጠኛ ሁኚ። በቤት ውስጥ ያለውን ኃላፊነት እንድትወጪ አዞሻል። ከተሰጠሽ ሥራ ውጪ የተሻለና የተቀደሰ ኃላፊነት እንደታቀደልሽ የምታስቢ ከሆነ እየተታለልሽ ነው። በራስሽ ቤት ውስጥ ታማኝ በመሆን በቅርበት ላሉት ነፍሳት በመሥራት በሰፊ መስክ ክርስቶስን ለማገልገል የሚያስችልሽን ብቃት ታዳብሪያለሽ። ነገር ግን እርግጠኛ እንድትሆኚ የሚያስፈልገው ነገር በቤት ክበብ ያለውን ኃላፊነታቸውን የሚዘነጉ ሁሉ ለሌሎች ነፍሳት ሊተጉ የተዘጋጁ አለመሆናቸውን ነው። 7Review and Herald, Sept. 15, 1891.AHAmh 171.3

    እግዚአብሔር ቤትሽን ባልሽንና ልጆችሽን እንድትተይ አልጠራሽም፤ እንደዚህ አድርጎ አያውቅም፤ ወደ ፊትም ፈጽሞ አያደርገውም…. ከትንሽዋ መንጋችሁ ሊለያይሽ ግዴታ የሆነበት ሥራ እግዚአብሔር ሰጥቶኛል ብለሽ ፈጽሞ ለአፍታ እንኳን እንዳታስቢ። ልጆችሽ አላስፈላጊ ጉድኝቶችን በመመሥረት ግብረ-ገብነታቸው የተሰበረና ልባቸው ለእናታቸው የደነደነ እንዲሆን አትተያቸው። AHAmh 171.4

    እንዲህ ብታደርጊ ብርሃንሽ በተሳሳተ አቅጣጫ እንዲበራ ታደርጊያለሽ፤ እግዚአብሔር እንደሚፈልግባቸው ለመሆን በመጨረሻም ሰማይን ለመውረስ የሚያደርጉትን ጥረት የበለጠ አስቸጋሪ እያደረግሽባቸው ነው። ጌታ ይጠነቀቅላቸዋል፤ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ካልሽ አንችም ተንከባከቢያቸው። 8Letter 28, 1890AHAmh 171.5

    በዕድሜአቸው የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ነው መሥራት፤ መከታተል፤ መፀለይና እያንዳንዱን መልካም ዝንባሌ ማበረታታት። ይህ ሥራ ሳይቋረጥ መቀጠል አለበት። ሚሲዮናዊ ሥራ ለመሥራት ሲባል የእናቶች ስብሰባና የስፌት ክበብ ውስጥ እንድትሳተፊ ትበረታቺ ይሆናል፤ ነገር ግን ታማኝና አስተዋይ ተቆጣጣሪ ከልጆችሽ ጋር ልትተይው የምትችይው ሰው ካላገኘሽ በስተቀር፣ ቸል ልትይው የማትችይው የቤት ውስጥ አደራ ስለአለብሽ እግዚአብሔር ለሌላ ሥራ እንዳስቀመጠሽ የመናገር ግዴታም አለብሽ። እግዚአብሔር እንደሚፈልጋቸው ይሆኑ ዘንድ ልጆችን እንድታሠለጥኚ የተሰጠሽ ሥራ የሚጠይቀውን ብቃት እንዳስጠበቅሽ በተጨማሪ ሥራ ከሚገባው በላይ ልትለፊ አይቻልሽም። በሌላ አነጋገር ተጨማሪ የምትሠሪው አድካሚ ሥራ ካለ ልጆችሽን ለመንከባከብ የሚያስፈልግሽን ብቃት ይቀንሰዋል። እንደ የክርስቶስ አጋር ሠራተኝነትሽ ልጆችሽ ሰልጥነውና ሥርዓት ይዘው ወደ እርሱ ልታመጫቸው ይገባሻል። 9Manuscript 32, 1899.AHAmh 171.6

    በተገቢው መንገድ ያልሠለጠነና ያቀራረጽ ግድፈት የሚያሳይ ልጅ ባህርይ መንስኤው በአብዛኛው እናት ናት። እናት የሚያጨናንቃትን የቤተ-ክርስቲያንን ሥራ በመሸከም ልጆችዋን ልትተው አይገባም። እናት ልትጠመድበት የተገባት ወደር የሌለው ሥራ በልጆቹ ሥልጠና ረገድ ምንም ቀዳዳ ሳይደፈን እንዳይቀር ማረጋገጥ ነው። ለትምህርትዋና ሥልጠናዋ ጥገኛ ለሆኑት ልጆችዋ ጊዜዋን በመጠቀም ቤተክርስቲያንዋን የምትረዳውን ያህል በሌላ በምንም ነገር ልትረዳ አትችልም። 10Manuscript 75, 1901.AHAmh 172.1

    ሰፋ ያለ የመሥክ አገልግሎት መመኘት ከንቱ ነው፦ ቀላል የሆኑትን በመንገዳቸው የተዝለከለኩትን ኃላፊነቶች ቸል ብለው ሳለ፣ አንዳንድ እናቶች በወንጌል አገልግሎት ሥራ ውስጥ መሳተፍ ይመኛሉ። ልጆች ቸል ይባላሉ፤ ቤት ለቤተሰቡ ደስታ የሞላበትና የሚማርክ አይደረግም፤ ስድብና ምሬት የዘወትር ትዕይንት ናቸው፤ ልጆች ቤታቸው የመጨረሻ አስጠሊታው ቦታ እንደሆነ እየተሰማቸው ያድጋሉ። በመሆኑም ቤታቸውን ጥለው የሚወጡበትን ጊዜ ይናፍቃሉ። የቤት ውስጥ ሕይወት ልስላሴ ጥሩ መካር ሳይሆንላቸው፤ የቤት ተጽዕኖ ሳይገድባቸው በሙሉ ፈቃደኝነት ታላቁን ዓለም ይቀላቀሉታል።AHAmh 172.2

    የልጆቻቸውን ልብ ከራሳቸው ጋር ማቆራኘትና በትክክለኛው መንገድ መምራት የነበረባቸው ወላጆች በእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ዕድል ያባክናሉ፤ ለታላቁ የሕይወታቸው ኃላፊነት እውር ይሆናሉ፤ በሰፊው የወንጌል አገልግሎት መስክ ለመሥራት በከንቱ ያልማሉ። 11Health Reformer, Oct. 1876.AHAmh 172.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents