Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 24—በእጅ ሙያ መሰልጠን

    በፍጥረት ሳምንት፣ ሥራ፤ እንደ በረከት የተመረጠ ነበር፡፡ እድገት፤ ኃይል፤ ደስታ ማለት ነበር፡፡ በኃጢአት ሥራ ምክንያት የዓለም ሁኔታ ሲለወጥ የሥራ ሁኔታም እንዲለወጥ አድርጐታል፡፡ ምንም እንኳን አሁን በጭንቀት፤ በድካምና በስቃይ የሚፈጸም የሚከናወን ቢሆንም አሁንም የደስታና የእድገት ምንጭ ነው፡፡ ለፈተናም ጥሩ መከላከያ ነው፡፡ ሥራ የሚኖረው የራሱ ሥነ ሥርዓት በግል መጥፎ አዝማሚያ ላይ ይቆጣጠራል ታታሪ ሠራተኛነትን የልብ ንጽህናንና ጥብቅነትን ያጠነክራል፡፡ ስለዚህም ከውድቀታችን እንድናንሠራራ የታሰበልን የታላቁ የአምላክ እቅድ አካልም ይሆናል፡፡EDA 239.1

    ወጣቱ የሥራን ክቡርነት እውነታ ማየት እንዲችል ሆኖ መመራት አለበት፡፡ እግዚአብሔር ያለማቋረጥ የሚሠራ መሆኑን አሳዩአቸው፡፡ በተፈጥሮ ውስጥ ያሉ ነገሮች ሁሉ የተመደበላቸውን ሥራ ያከናውናሉ፡፡ የሥራ እንቅስቃሴ ተፈጥሮን ሁሉ ይገልፃል፡፡ እኛም ተልዕኮአችንን ለማሟላት ንቁ ሠራተኛ መሆን አለብን፡፡EDA 239.2

    በሥራችን ሁልጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር መሆን አለብን፡፡ መሬትንና በውስጧ ያሉ መዝገቦቿን ሁሉ ሰጠን፡፡ ነገር ግን ለራሳችን ጥቅምና መቾት እንደሚውሉ ማድረግ አለብን፡፡ ዛፎችን እንዲያድጉ አደረገ፡፡ እኛም ጣውላ አዘጋጅተን ቤት እንሠራለን፡፡ በመሬትም ውስጥ ወርቅን ብርን ብረትንና ከሰልን ቀብሮ አስቀመጠ፡፡ እናም ልናገኛቸው የምንችለው በሥራ ብቻ ነው፡፡EDA 239.3

    እግዚአብሔር ፈጥሮ እስከአሁንም ሁሉን ነገሮች ባለማቋረጥ በመቆጣጠር ላይ ያለ ሲሆን ለእኛ የእርሱን ዓይነት ኃይል ከፍሎ ሰጥቶናል፡፡ በተፈጥሮ ባህሪያት ላይ በተወሰነ መጠን እንድትቆጣጠር ኃይል ሰጥቶናል፡፡ እግዚአብሔር ከዚያ ሁሉ ምስቅልቅል ውስጥ አውጥቶ ምድርን ከነውበቷ እንደፈጠረ ሁሉ እኛም ትርምስ በሞላበት ሁኔታ ውስጥ ሥርዓትና ውበትን መፍጠር እንችላለን፡፡ ምንም እንኳን አሁን ሁሉም ነገሮች በኃጢአት ምክንያት የተበላሹ ቢሆንም በፈፀምነው ሥራ የእርሱ ዓይነት ደስታ ይሰማናል፡፡ እርሱ ምድርን ሠርቶ ከጨረሰ በኋላ «መልካም ሆነ» በማለት ተናገረ፡፡EDA 239.4

    እንደ አንድ ሕግ ለወጣቱ እጅግ ጠቃሚ የሆነውን ነገር የሚያገኘው ከሥራ ነው፡፡ ትንሽ ልጅ ሐሳቡን የሚያሳርፍበትና እድገትም የሚያገኘው በጨዋታ ነው፡፡ የሚሠራው የአካል ማጐልመሻ እስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሁሉ አካሉን ብቻ ሣይሆን አአምሮውንና መንፈሳዊ እድገቱን የሚያፋጥን መሆን አለበት፡፡ ብርታትና ብልሃት እያገኘ በሄደ ቁጥር በአንድ ዓይነት ጠቃሚ የሥራ መሥመር የሚደሰት ይሆናል፡፡ እጆቹ ለሥራ የተሟሉ እንዲሆኑ አድርጐ የሚያሰለጥንና የሕይወትንም ሸክም በድርሻቸው እንዲወጡ ለማድረግ ወጣቶችን የሚያስተምር የአእምሮንና የባህሪይን እድገት ያፋጥናል፡፡EDA 240.1

    ወጣቶች ሕይወት ማለት ከልብ መሥራት፤ ኃላፊነት ፤ ለሌሎች ጥንቃቄ መውሰድ ማለት መሆኑን ይማሩ፡፡ የሥራ ወይም የተግባር ሰው የሚያደርጋቸውን ሙያ መማርና በድነገት የሚፈጠሩ ሁኔታዎችን ሁሉ መጋፈጥ የሚችሉ ሰዎች እንዲሆኑ አድርጐ ማሰልጠን ያስፈልጋል፡፡ ሥነ ሥርዓትና ያሠራር ስልት ያለው፤ በቅደም ተከተል በሚገባ የተደራጀ ሥራ ለአንዳንድ የሕይወት ውጣ ውረድ መሰናክል መከላከያ ብቻ ሣይሆን በአጠቃላይ ሁለገብ ለሆነ እድገት የሚረዳ መሆኑን መማር አለባቸው፡፡EDA 240.2

    የሥራን ክቡርነት በሚመለከት የተባለውንና የተፃፈውን ሁሉ ካለመረዳት የተነሳ የእጅ ሥራ ግምት እንደሚያሰጥ ወይም እንደሚያስንቅ አድርጐ የመገመት ስሜት አለ፡፡ ወጣቶች መምህራን፣ ፀሐፊዎች፣ ነጋዴዎች፣ ሀኪሞች፣ ኃላፊ ባለሥልጣኖ፣ ጠበቆች ሆነው ወይም ሌላ ጉልበት የማይጠይቅ ሥራ ላይ ለመሠማራት ይመኛሉ፡፡ ወጣት ሴቶችም ከቤት ሥራ ሸሽተው በሌላ ሥራ ላይ ለመሠማራት ትምህርት ይፈልጋሉ፡፡ ማንም ሰው ወይም የትኛዋም ሴት ብትሆን በቀና ልብ የሚሠሩት ማንኛውም የእጅ ሥራ ሁሉ አያስንቃቸው፡፡ ዝቅተኛ ግምት የሚያሰጥ ወይም የሚያዋርድ ሥራፈት ቦዘኔ መሆንና ራስን ብቻ መውደድ ነው፡፡ ቦዘኔነት ክፉ ማሰብን ያመጣል፡፡ ውጤቱም ሕይወትን ባዶ መድረባዳ ማናቸውም ክፉ ተክል ሁሉ የሚበቅልበት ሜዳ ማድረግ ነው፡፡ «ብዙ ጊዜ በርሷ ላይ የሚወርደውን ዝናብ የምትጠጣ መሬት ለሚያርሱትም ደግሞ የምትጠቅም አትክልት የምታበቅል ከእግዚአብሔር በረት ታገኛለችና ኩርንችትን ግን ብታመጣ የተጣለች ናት ለመረገምም ትቀርባለች መጨረሻዋም መቃጠል ነው፡፡» እብራ፣ 6፡7-8EDA 241.1

    የተማሪውን ጊዜ በአብዛኛው ከሚወስዱበት የጥናት ዘርፎች አብዛኛዎቹ ለጠቃሚነትና ደስተኛነት የሚያገለግሉ አይደሉም፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ወጣት ራሱን ከሁሉም የቀን ተቀን ተግባራት ጋር ማስተዋወቅ ይበልጥ ይጠቅመዋል፡፡ ቢያስፈልግ አንድ ወጣት ሴት ፈረንሳይኛ ወይም አልጀብራ ማወቋ እጅግ ወሳኝና ጠቃሚ ሊሆንላት ይችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሕብስት የሆነ ዳቦ መጋገር፤ ቆንጆ የልብስ ቅድና ስፌት እንዲሁም ሌሎች ለቤት አያያዝ የሚያስፈልጉ ተግባራት ሁሉ ለሕይወት እጅግ አስፈላጊ ናቸው፡፡EDA 241.2

    ለመላው ቤተሰብ ጤንነትና ደስታ የሚሆን ምግብ የማዘጋጀት ኃላፊነት ያለባት ሴት ከባለሙያነትና ከብልህነት የበለጠ ሌላ ነገር አይኖርም፡፡ እንደ ነገሩ ተደርጐ የተዘጋጀ ያልተሟላ ምግብ የጐልማሳውን አለኝታነትና የልጁንም ዕድገት ያሰናክለዋል፡፡ ከነጭራሹም ሊያጠፋውም ይችላል፡፡ ጠቀሜታው ለአካል ብቻ የሆነ ምግብ በማቅረብ የምትጋብዝ በመጥፎ ጐኑ ማበላሸት እንደምትችል ሁሉ በዚያው ችሎታ በጐውንም መፈፀም ትችላለች፡፡ ስለዚህ የሕይወት ደስታ በታማኝነት ከሚፈፀመው ከተለመዱ ተግባራት ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው፡፡EDA 242.1

    በቤት አያያዝ ውስጥ ወንዱም ሴቷም የየራሳቸው ድርሻ ያላቸው ሲሆን ወንድና ሴት ልጆችም የቤት ውስጥ ተግባራት ዕውቀት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ አልጋ ማንጠፍ፤ ቤቱን በሥርዓት ማዘጋጀት፣ ሳህኖችን ማጠብ፣ ምግብ ማቀራረብ መቻል፣ የራሱን ልበሶች አጥቦ ተኩሶ አጣጥፎ ማዘጋጀት፣ አንድን ልጅ እንደ አንድ አዋቂ ሙሉ ሰው የሚያደርገው ሥልጠና ነው፡፡ በጣም ደስተኛና ጠቃሚ ሰው እንዲሆን ያደርገዋል፡፡ ሴቶች ልጆችም በበኩላቸው ለፈረስ ልጓም ማስገባት መጋዝና መዶሻ መጠቀም መቻል መጫሪያና ዶማ መያዝ ቢችሉ በሕይወት ለሚያጋጥሟቸው ድንገተኛ ችግሮች ሁሉ በጥሩ ሁኔታ መጋፈጥ የሚችሉ ይሆናሉ፡፡EDA 242.2

    ልጆችና ወጣቶች እግዚአብሔር በየቀኑ የሚታገለውን ታታሪ ሠራተኛ እንዴት እንደሚያከብረው ከመጽሐፍ ቅዱስ ይማሩ፡፡ ስለ «ነቢያት ልጆች» (1ኛ ነገሥ 6፡1-7) ያንብቡ፡፡ በትምህርት ቤት ውስጥ በነበሩ ጊዜ ራሳቸው ስለገነቡት ቤት ያንብቡ፡፡ በተውሶ የመጣውን መጥረቢያ ከመጥፋት ያዳነው ተዓምር ስለተገለጠላቸው ተማሪዎች፡፡ ስለአናፂው የሱስ ያንብቡ፡፡ ድንኳን ሠሪ ስለነበረው ጳውሎስ ከአድካሚው የእጅ ሥራው ጋር እጅግ ከፍተኛ ሰብዓዊና መለኮታዊ አገልግሎትን ስለ አጣመረው ጳውሎስ ያንብቡ፡፡ አምስት እንጀራዎች ይዞ ስለነበረውና በመድኅን አስገራሚ ተዓምር የተሰበሰበውን ሕዝብ ስለመገበበት ሁኔታ ያንብቡ፡፡ ዶርካስ ስለ ተባለችውና ከሞት በኋላ እንደገና ተመልሳ ለድሆች ልበስ እንድትሰፋላቸው ስለተጠራችው መበልት ያንብቡ፡፡ በምሣሌዎች ስለተጠቀሰችው ሴት «የበግ ጠጉርና የተልባ እግር ትፈልጋለች በእጆቿም ደስ ብሏት ትሠራለች» «ገና ሌሊት ሳለ ትነሳለች ለቤቷም ሰዎች ምግባቸውን ለገረድዎቿም ተግባራቸውን» ስለምትሰጠው ሴት «ከእጅዋም ፍሬ ወይን» ስለምትተክለዋ ሴት ያንብቡ «ወገቡዋን በኃይል» ስለምትታጠቀው «እጅዋን ወደድህ» ስለምትዘረጋው «እጅዋን ወደችግረኛም ስለምትሰድደው» «የቤቷን ሰዎች አካሄድ በደህና ትመለከታለች፡፡ የሃኬትንም እንጀራ አትበላም» ስለተባለላት ሴት ያንብቡ፡፡ (ምሳ 31፡13፣15፣ 16፣17፣20፣27) ፡፡EDA 242.3

    ስለእንደዚህ ዓይነቷ ሴት እግዚአብሔር እንደዚህ ይላል «እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርሷ ትመሰገናለች ከእጅዋ ፍሬ ስጧት ሥራዎችዋም በሸንጐ ያመሰግኗት» ምሳ 30፡31EDA 243.1

    ለእያንዳንዱ ልጅ የመጀመሪያው የኢንዱስትሪ ት/ቤት የወላጆቹ ቤት መሆን አለበት፡፡ በተቻለ መጠንም በየትምህርት ቤቱ ውስጥ የእጅ ሥራ የሙያ መሣሪያዎች በተጓዳኝ መቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲህ ዓይነት ሥልጠና በአመዛኙ እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታው በተጨማሪ ከሚኖረው ሥነ ሥርዓት ጋር የጅምናስቲክ መሣሪያዎችን ቦታ መተካት አለበት፡፡EDA 243.2

    የእጅ ሙያ ስልጠና እስከ አሁን ከተሰጠው በላይ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ ከከፍተኛ የአእምሮና የሞራል ትምህርት በተጨማ ለአካል መዳበርና ኢንዱስትሪያዊ ስልጠና የሚጠቅሙ ትምህርት ቤቶች መገንባት አለባቸው፡፡ በርሻ ሥራዎች፣ በእጅ ሥራ ውጤቶች በተቻለ መጠን እጅግ ጠቃሚ በሆኑ መስኮች መሸፈን ያለባቸው ሥራዎች የቤት ውስጥ ኢኮኖሚያዊ አስተዳደር ፣ ለጤና የሚበጅ ምግብ በማዘጋጀት፣ በልብስ ስፌት፣ አጠቃላይ ንጽህናና የልብስ አዘገጃጀት፣ በሽተኛን የማስታመም፤ ሕፃናትን ተንከባክቦ በማስተማር ረገድ ትምህርት መስጠት ያስፈልገዋል፡፡ የአትክልት ቦታዎች፤ አነስተኛ የሙያ ወርክ ሾፖች፤ የማስተናገጃ ክፍሎችም መዘጋጀት አለባቸው፡፡ እያንዳንዱ የሥራ መስመርም በምርጥ ባለሙያዎች መመራት አለበት፡፡EDA 243.3

    ሥራው አንድ የተወሰነ ዓላማ ሊኖረው ይገባል፡፡ ዝርዝርና ግልጽ መሆንም አለበት፡፡ እያንዳንዱ ሰው በተለያዩ የእጅ ሙያዎች ላይ ሰልጥኖ ዕውቀት እንዲኖረው ይፈልግ ይሆናል እናም ቢያንስ በአንደኛው ባለሙያ መሆኑ አይቀርም፡፡ እያንዳንዱ ወጣት ትምህርት ቤቱን ሲለቅ አንድ በሕይወቱ ወይም በኑሮው መተዳደሪያ እንዲሆነው የሚያስችለው እውቀት የእጅ ሙያ ተምሮ መውጣት አለበት፡፡EDA 244.1

    በትምህርት ቤቶች ውስጥ በኢንዱስትሪዎች ዘርፍ ሥልጠና ላይ የሚኖረው ተቃውሞ በሚጠይቀው ወጪ ስፋትና ብዛት ላይ ነው፡፡ ነገር ግን የመጨረሻ ግቡ ወጪውን ይክሳል፡፡ ወጣትን እንደ ማሰልጠን ሌላ ከባድ ኃላፊነት አልተጣለብንም፡፡ እናም በትክክል ይፈጸም ዘንድ የሚጠይቀው አንዳንዱ ወጪ በአግባቡ ሥራ ላይ መዋል አለበት ማለት ነው፡፡EDA 244.2

    ከሚያስገኛቸው ገቢዎች ውጤቶች አንፃር እንኳ ለእጅ ሥራ ሙያ ስልጠና የሚጠይቀው ወጪ የትክክለኛውን መዋዕለ ንዋይ ሁኔታ ያመለክታል፡፡ ልጆቻችን ቢሰባሰቡም ከምስጢሩ ቦታና ከጭንቀቱ ውጭ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ለአትክልት ቦታ የሚያስፈልገው ወጪ ለወርክ ሾፖችና ለገላ መታጠቢያዎች የሚወጣው ወጪ፣ ከሆስፒታሎችና ማገገሚያዎች ከሚገኝ ገቢ በላይ ነው፡፡ ወጣቶችም ራሳቸው ለኢንዱስትሪ ሥር ባህል ሲሰለጥኑ ጠቃሚና ምርታማ በሆነ የሥራ መሥመር ባለሙያ ሲሆኑ ለሕብረተሰቡና ለሕዝብ የሚኖራቸውን ጠቃሚነት ማን ሊገምተው ይችላል?EDA 244.3

    በጥናት መካከል ላይ መዝናናት ካስፈለገ ክፍት በሆነ ንፁህ አየር በሚገኝበትና ጠቅላላ የሆነ የሰውነት እንቅስቃሴ ሊደረግበት የሚያመች ቦታ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ በእርሻ ሥራ ሙያ እንደ መሠልጠን ያለ ሌላ ጠቃሚ መስመር የለም፡፡ በእርሻው መልክ ፍላጐት እንዲያድርባቸው ሐሳቡን በልባቸው ለመፍጠርና ለማበረታታት በጣም ትልቅ ጥረት መደረግ አለበት፡፡ መምህሩ መጽሐፍት ቅዱስ ስለ እርሻ ሥራዎች የሚናገረውን በሚገባ ትኩረት ይሰጥበት፡፡ ሰው መሬትን እያረሰ ያለማ ዘንድ የእግዚአብሔር ሐሳብ እንደሆነ ያ የመጀመያው ሰው የዓለም ሁሉ ገዢ የነበረው ሰው ይንከባከብና ያለማው ዘንድ የአትክልት ቦታ ተሰጥቶት እንደነበረ፣ እንዲሁም በዓለም ላይ የነበሩ ታላላቅ ሰዎች ሥራው ክቡር በመሆኑ አራሽ ገበሬዎች እንደነበሩ በመገንዘብ ትኩረት ይሰጥበት፡፡ በእንዲህ ዓይነት ሕይወት ውስጥ የሚኖሩ አድሎችን አሳዩ፡፡ ጠቢቡ ሰው እንዲህ ይላል፡፡ «…. እርሻን የሚወድ ንጉሥ ቢኖር መልካም ነው፡፡» መክብብ 5፡9 መሬትን የሚያለማ ሰው ይላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ «ይህንንም ብልሃት አምላኩ ያስታውቀዋል፣ ያስተምረዋልም» ኢሳ 27፡18 ኑሮውን በእርሻ ላይ ያደረገ ሰው ከብዙ ፈተናዎች ያመልጣል፡፡ ሥራቸው በከተማ ውስጥ የሆኑ ሰዎች የማያገኙትን ደስታና ቁጥር የሌለው ጥቅምና በረከትም ያገኛል፡፡EDA 245.1

    እጅግ በጣም ብዙ ሐብት የማፍሰስና የሥራ እሽቅድድም በጦፈበት በዛሬው ዘመን በእርሻ ሥራ የተሰማራው ሰው የሚያገኘውን ያክል በሌላ ዘርፍ የተሰማራው ሰው በሙሉ ነፃነት በእርግጠኝነት በራስ መተማመን የድካሙን ያክል በምላሹ የሚያረካ ነገር አያገኝም፡፡EDA 245.2

    በእርሻ ሥራ ውስጥ ተማሪዎች ንድፈ ሐሳብ ብቻ ሣይሆን የተግባር ትምህርትም ይሰጣቸው፡፡ ስለ ተፈጥሮ፣ መሬትን አለስልሶ ስለ ማዘጋጀት፣ ስለ ተለያዩ አዝርዕት መዝራት ጠቀሜታ፣ ጥሩ ምርት ስለሚገኝበት ዘዴ ሳይንስ የሚሰጠውን ትምህርት በሚያጠኑበት ጊዜ ዕውቀታቸውን ጥቅም ላይ ያውሉት፡፡ መምህራንም በሥራው ውስጥ ከተማሪዎች ጋር ይካፈሉ፡፡ እናም በእውቀት በሚሠራው ጊዜ ምን እንደሚመስለ የጥሩ ሙያን ጥቅም ያሳዩአቸው፡፡ ሥራውን በተቻለ መጠን በጥሩ ሁኔታ የማከናወን ዓላማና ምኞት የፀሐይ ብርሃንና ንፁህ አየር እያገኙ ከሚኖረው መንፈስ የሚያድስ የሰውነት እንቅስቃሴ ጋር ተዳምሮ ለእርሻ ሥራ ፍቅር እንዲያድርባቸውና ብዙ ወጣቶች የወደፊት ዘላቂ ሥራቸው እንዲሆን ይወስኑ ዘንድ ይረዳቸዋል፡፡ ስለሆነም አሁን ወደታላላቅ ከተሞች ውስጥ የመጉረፍን ማዕከል እስከመከላከል የሚደርሱ በእግር የሚተኩ ይሆናሉ፡፡EDA 246.1

    እንደዚሁም ደግሞ ትምህርት ቤቶቻችን የሥራ አጥን ብዛት ለመቀነስ የሚረዱ ወይም አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ይሆናሉ፡፡ በሽህ የሚቆጠሩ፣ ረዳት የሌላቸው ረሀብተኞች ቁጥራቸው በየቀኑ እየጨመረ የወንጀለኞችን ብዛት ከፍ እያደረገው በመሄድ ላይ የሚገኙትን ልዩ ሙያ በሚጠይቅ፣ ትጋት በሚያስፈልገው የእርሻ ሥራ እንዲሠማሩ አመራር ቢያገኙ ደስተኛ ጤናማና ነፃ በሆነ ሕይወት ራሳቸውን እስከመቻል በደረሱ ነበር፡፡EDA 246.2

    የእጅ ሙያ ሥልጠና ጠቀሜታ የተራቀቀ ችሎታ ባላቸው ባለሙያዎች ዘንድም ይፈልጋለ፡፡ አንድ ሰው ብሩህ አእምሮ ሊኖረው ይችላል፡፡ ሐሳቦችን ቶሎ የማግኘትና የመጨበጥ ችሎታ ይኖረው ይሆናል፡፡ የዚህ ሰው እውቀትና ብቃት ለተመረጠበት ጥሪ ብቁ ሊያደርጉትና ተቀባይነትን እንዲያገኙ ሊያደርጉት ይችላሉ፡፡ ይሁንና ችሎታው ለሥራው የሚመጥን ለመሆን የማያበቃ ገና ብዙ የሚቀረው ሊሆን ይችላል፡፡ ከመጽሐፍት ብቻ የተወሰደ ትምህርት የሚጠቅመው ነገር ቢኖር ላይ ላዩን ብዠ ወደመጋለብ ማሰብን ያበረታታል፡፡ በትክክል ከተከናወነ ወይም ከተሠራበት በለምድ ብልህነት እያልን የምንጠራውን የተግባር ጥበብ ወደማዳበር ያዘነብላል፡፡ እቅድ የማውጣትና የማስፈፀም ችሎታን ያዳብራል፡፡ ድፍረትንና ጥንቁቅነትን ያበረታታል፡፡ ዘዴና ብልሃትን ያመጣል፡፡EDA 246.3

    አንድ ዘላቂ ሙያ ለሆነ ዕውቀቱ መሠረት የጣለ ሀኪም በሽተኛው ባለበት ክፍል ውስጥ ገብቶ በሚሰጠው ተግባራዊ ግልጋሎት አጠቃላይ የሆነ እውቀት በድንገተኛ በሽተኞች ላይ የሚፈልገውን አገልግሎት ለመስጠት ችሎታ ያለው፤ ሌሎችንም ሙያው የሚጠይቀውን ክህሎቶች ሁሉ ማሟላት እንደሚያስፈልገው ጠለቅ ብሎ ለማየት ፍጥነት ይኖረዋል፡፡ እነዚህን ሁሉ ግን አሚልቶ የሚሰጠው የተግባር ሥልጠና ብቻ ነው፡፡EDA 247.1

    አገልጋዩ፤ የወንጌል መልዕክተኛው፤ መምህሩ ሁሉ ለየቀኑ ሕይወት የሚያስፈልግ ዕለታዊ ተግባራት የሚጠቅም ዕውቀታቸውና ሙያ መያዛቸው ሲገለጽ በሕዝብ ዘንድ ተፈላጊነታቸው እየጨመረ ይሄዳል፡፡ የወንጌል መልዕክተኛው ስኬታማነት፣ ምናልባትም ሕይወቱ ጭምር ተግባራዊ ስለሚሆኑ ነገሮች በሚኖረው ዕውቀት ላይ የሚመሠረት ይሆናል፡፡ ምግብ የማዘጋጀት ችሎታ ድንገተኛ አደጋዎችንና በሽተኞችን የማከም ችሎታ፤ ቤት ወይም ቤተ ክርስቲያን መገንባት ቢያስፈልግ፣ እነዚህ ነገሮች ሁሉ በሕይወት ሥራ ውስጥ በመሳካት ወይም በውድቀት ልዩነት ያሳያሉ፡፡EDA 247.2

    አንድን ትምህርት በመማር ረገድ ብዙ ተማሪዎች ራሳቸውን በራሳቸው ቢረዱ የበለጠ ዕውቀት ያካብታሉ፡፡ ዕዳ ውስጥ ከመግባት ወይም በወላጆቻቸው ላይ ተማምነው ራሳቸውን ከመካድ ወጣት ወንዶችና ሴቶች በራሳቸው ላይ የሚተማመኑ ይሁኑ፡፡ የገንዘብ፣ የጊዜን፣ የጉልበትን ፣ የሚኖሩ ጥሩ አጋጣሚዎችን ፋይዳ ይማራሉና መቦዘን ከሚያስከትለው ፈተናም በጣም ይርቃሉ፡፡ የተራረፈውን በማጥፋት ልማድም ይድናሉ፡፡ የቁጠባ ንብረት አያያዝ ፣ የኢንዱስትሪ፣ ራስን የመካድ፣ ተግባራዊ የሆነ የሥራ አመራርና በዓላማ የመጽናት ትምህርቶች መካን በሕይወት ለሚኖረው ጦርነት ዋነኛዎቹ መሣሪያዎች የሆኑላቸዋል፡፡ የተማሪው ራስን በራስ በመርዳት መማር ብዙ ትምህርት ቤቶች ከወደቀባቸው የእዳ ሸክም ትግል ያድናል፡፡ የእነኝህን ተቋሞች ጠቃሚነት ስንካላ ከማድረግም ብዙ ይረዳል፡፡EDA 247.3

    ወጣቶች መማር ማለት የሕይወትን አስቸጋሪ ግዳጆችና ከባድ ሸክሞች ለማምለጥ የሚችሉበትን መንገድ ማስተማር ማለት ብቻ አለመሆኑን ይገለጽላቸው፡፡ ዓላማው የተሻሉ ዘዴዎችንና ከፍተኛ ዓላማዎችን በማስተማር ሥራው ብሩህ እንዲሆንላቸው ማድረግ ነው፡፡ የሕይወት እውነተኛ ዓላማ የሚችሉትን ያክል ለራሳቸው ትልቁን ድርሻ ማጋበስ አይደለም፡፡ በድርሻቸው የዓለምን ሥራ እየሠሩ ፈጣሪአቸውን እንዲያከብሩ ነው እንጂ፡፡EDA 248.1

    የጉልበት ሥራ ዝቅ ተደርጐ የሚታይበት ዋነኛው ትልቁ ምክንያት ብዙ ጊዜ በግዴለሽነትና ባለማሰብ የሚፈጸም በመሆኑ ነው፡፡ አስፈላጊነቱ ግዴታ ሲሆን በትክክል የሚፈጸም እንጅ በምርጫ የሚሠራ አይደለም፡፡ ሠራተኛው ከሙሉ ልቡ አይሠራውም፡፡ እሱም ሥራውን አያከብረውም ሌሎችም እንዲያከብሩት አያደርግም፡፡ ይኸንን ስህተት የሕሊና ትምህርት ሊያርመው ይገባል፡፡ ትክክለኛነትና በሚገባ በዝርዝር የመፈጸም ልምድ መዳበር አለበት፡፡ ተማሪዎቹ ዘዴና ሥርዓትን መማር አለባቸው፡፡ ጊዜን በቁጠባ መጠቀምና እያንዳንዷ እንቅስቃሴ ዋጋ እንዲኖራት ማድረግ አለባቸው፡፡ መማር ያለባቸው እጅግ ምርጥ የሆኑትን ዘዴዎች ብቻ ሣይሆን ያለማቋረጥ ለማሻሻል በሚገፋፋ ምኞት መንፈስ መነቃቃት አለባቸው፡፡ ሥራቸውን ሁሉ የሰው ልጆች አእምሮና እጆች ሊሠሩ የሚችሉትን ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ላይ ለማድረስ ዓላማ ይኑራቸው፡፡EDA 248.2

    እንዲህ ዓይነት ስልጠና የሥራ ጌቶች እንጅ ባሪያዎች እንዲሆኑ አያደርጋቸውም፡፡ ለብርቱ ሠራተኛ ዕጣ ብርሃን ያበራለታል፡፡ የተቀደሰ ሥራ እንደሆንለትም ያደርገዋል፡፡ ሥራዬ ለሰዎች ደስ የማያሰኝ ነው ብሎ የሚያስብ ሰው በዚያውም ላይ ብቻ ለራሱ በመርካት፣ በማይምነት አንዳችም የማሻሻል ሙከራ ሳያደርግ ለሚቀመጥ ሰው በርግጥ ሸክም ይሆንበታል፡፡ ነገር ግን ሣይንስና በትሕተና ሥራ አማካይነት የሚገነዘቡ ቅድስናና ውበትን ይመለከታሉ፡፡ በታማኝነትና በብቃት በማከናወንም በሥራው ደስታን ያገኛሉ፡፡EDA 249.1

    በእንዲህ ዓይነት የሰለጠነ ወጣት በሕይወቱ የተጠራበት መስመር ምንም ዓይነት ቢሆን ቀና እስከሆነ ድረስ የሥራ ደረጃውን ጠቃሚና የሚከበር ያደርጋል፡፡EDA 249.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents