Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ዳንኤል በምድር የሰማይ አምበሳደር

    ዳንኤልና ጓደኞቹ በወጣትነታቸው ዘመን በባቢሎን ውስጥ ሳሉ በዚያ ዓይት የወጣትነት እድሜ ዮሴፍ በግብጽ ምድር ከደረሰበት ችግር በተሻለ ዕድል ላይ ነበሩ ማለት ቢቻልም ከእሱ ትንሽ አነስ በሚል አገለግሎት ላይ እያሉ የባህሪይ ፈተና ውስጥ ወድቀው ነበር፡፡ በይሁዳ ከነበረው ትንሽ ቤታቸው አንፃር እነኘህ የነገሥታት ዘር የሆኑ ወጣቶች እጅግ ድንቅ ወደሆኑ ከተሞች ተወስደው ነበር፡፡ በዚያም ታላቅ ወደነበረው ንጉሥ ችሎት ለንጉሡ ልዩ አገልግሎት እንደሰጡ ለብቻ ተለይተው ተቀመጡ፡፡ በዚያ በቅሌት በተበከለ አደባባይ የድሎትና የምኞት ሆነው ሳለ የባቢሎን ምርኮኞች መሆናቸው የእግዚአብሔር ቤት የአገልግሎት ዕቃዎች የባቢሎን የጣኦት ቤቶች ውስጥ እንዲቀመጡ መደረጋቸው፣ የእስራኤል ንጉሥ ራሱ በባቢሎናዊያን እጅ ወድቆ እሥረኛ መሆኑ አሸናፊዎቹ ወገኖች ሃይማኖትና ልማዳቸው ከእብራዊያን ሃይማኖትና ልማድ እንደሚበልጥ አድርገው በጉራ ለመናገር በቁ፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ እሥራኤላዊያን ከእርሱ ትዕዛዝ ውጭ በመሄዳቸው ምክንያት በመጣባቸው ሐፍረት አማካይነት እግዚአብሔር የሁሉም የበላይ መሆኑን ያስቀመጣቸው መመዘኛዎችም ቅዱስ መሆናቸውንና የመታዘዝን መልካም ውጤቶች እርግጠኛነት ይረዱ ዘንድ እግዚአብሔር በባቢሎን አስመሰከረ፡፡EDA 56.2

    ዳንኤልና ለጓደኞቹ ከወደፊት እድላቸው ገና መጀመሪያው ላይ ወሳኝ የሆነ ፈተና ገጠማቸው፡፡ ምግባቸው ከቤተ መንግሥት ገበታ እየመጣ እንደሰጣቸው መታዘዙ ንጉሡ እንደወደዳቸውና ለደህንነታቸውም ስለአሰበ ለብቻ እንዲቀመጡ ማድረጉ መጠንቀቁን ያመለክታል፡፡ ይሁንና ግማሹ ምግብ ለጣኦቶቹ ይሰጥ ስለነበር ይህ ከንጉሡ ቤተመንግሥት የሚመጣው ምግብ ለጣኦቶቹ የተዘጋጀ ነበር ማለት ነው፡፡ ከዚህ ዓይነት መሥተንግዶ መሳተፍ ማለት ደግሞ ንጉሡ ለሀሰተኛ አማልክት ከሚያደርገው ነገር ጋር መተባበር ማለት ነበር፡፡ ለአብ የነበራቸው ታማኝነት ከመሳተፍ አገዳቸው፡፡ በመጥፎ ልማድ የተበላሸ አካል ሕሊናና መንፈሳዊ እድገት ከምቾትና ድሎት የተነሳ የሚመጣውን ከስረት ዘልቀው ሊገቡበት ፈልፈለጉም፡፡EDA 57.1

    ዳንኤልና ጓደኞቹ የእግዚአብሔርን ቃል መሠረታዊ ሐሳቦች በታማኝነት ተምረው ነበር፡፡ እጅግ ከፍተኛውን መልካም ነገር ለማግኘት እንዲቻል ለመንፈሳዊው ጉዳይ ምደራዊ ነገሮችን መስዋዕት ማድረግ እንደሚደስፈልግ ተምረው ነበር፡፡ ውጤቱንም አገኙ፡፡ በመግብና በመጠጥ ላይ የነበራቸው ርጋታና አስተዋይነት የተሞላበት ለማድ የእግዚአብሔር ወኪል እንደመሆናቸው ያሳዩት የኃላፊነት ስሜት፣ የአካል የአእምሮና የነፍስን የተቀደሰ ዕድገት የሚጋበዝ ነበር፡፡ ሥልጠናቸውን ሲጨርሱ በንጉሡ ፊት ክብር ሽልማት ለማግኘት ከሌሎች ተወዳደሪዎች ጋር በተሰጣቸው ፈተና «...እንደ ዳንኤል፣ ሀናንያ እና እንደሚካኤልና እንደአዛርያ ያለ አልተገኘም፡፡» ዳን 1፡19EDA 57.2

    በባቢሎን አደባባይ ከየሀገሩ የተወከሉ ሁሉ በተገኙበት ምርጥ ከህሎት ያላቸው ሰዎች እጅግ ከፍተኛ የተፈጥሮ ስጦታ ያላቸው ሰዎችና ይህች ዓለም ልትሰጥ የምተችለውን ከፍተኛ ትምህት ያገኙ ሰዎችና መሰሎቻቸው በተሰበሰቡበት መካከል እብሪዊያኑ ምርኮኞች ጓደኛ አልተገኘላቸውም፡፡ በአካላዊ ጥንካሬና በውበት፣ በአእምሮ ችሎታና በስነጽሁፍ ውጤት ሊወዳደራቸው የሚችል አለተገኘም፡፡ «ንጉሡም በጠየቃቸው በጥበብና በማስተዋል ሁሉ በግዛቱ ሁሉ ከሚኖሩ የሕልም ተርጓሚዎችና አስተማሪዎች ሁሉ ከእነሱ አሥር እጅ የበለጡ ሆነው አገኛቸው፡፡» ዳን1፡20EDA 58.1

    ያለማወላወል ከእገዚአብሔር ጋር ተባበረ፡፡ ከእርሱ ክብር ጐን ሳያዘነብል ዳንኤል ቅዱስ ከብሩን የጠበቀና ለየት ያለ ተህትና ማሳየት ገና በወጣትነቱ በከሳሹ እጅ እያለ ነገር ግን የንጉሡን «መውደድና ፍቅር አስገኘለት፡፡» ይህ ባህሪይውም በሕይወቱ አደገበት፡፡ እናም እጅግ በፍጥነት በግዛቲቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ለመሆን በቃ፡፡ ተከታታይ ነገሥታት በነገሡበት ዘመን ሁሉ የሕዝብ ውድቀትና መነሳት በተከታተሉና ተቃዋሚ መንግሥት በተመሠረተ ቁጥር የእርሱ ጥበብና ታላቅ ሰውነት ያው ነበሩ፡፡ ከልብ የነበረው ፍፁም ደግነቱ ለመሠረታዊ ሐሳቦች ካለው ታማኝነት ጋር ተዋህዶ ጠላቶቹም እንኳ እውነቷን እስከመናገር ደረሱ፡፡«ነገር ግን የታመነ ነበረና በደልና ስህተት አልተገኘበትም፡፡» ዳን.6፡4EDA 58.2

    ዳንኤል በማይወላውል እምነት ወደ እግዚአብሔር በቀረበ ጊዜ ለነቢያት የሚሆን ኃይል በእርሱ ላይ አረፈ፡፡ የችሎት ኃላፊነትና የመንግሥትን ሚስጥሮች ይዞ በሕዝብ ከበሬታ ባገኘ ጊዜ በእግዚአብሔር ዘንድም እንደ አንድ አምባሳደር ሆኖ ሞገስ አገኘ፡፡ የመጪዎቹን ዓመታት ሚስጥሮችንም ማንበብ ተማረ፡፡ አረመኔ ነገስታት የሰማይ ወኪል ከሆነው ሰው ጋር በመተባበራቸው የዳንኤልን አምላክ ለማወቅ ተገደው ነበር፡፡ ናቡከደነጾር ዳንኤልን እንዲህ አለው፡፡ «በእውነት አምላካችሁ የአማልከት አምላክ የነገሥታት ጌታና ሚስጥርነ ገላጭ ነውና» ዳሪዎስም በአወጣው አዋጅ ላይ «በምድር ሁሉ ላይ ወደሚኖሩ ወገኖችና አህዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋ ወደሚናገሩ ሁሉ፡፡» «ዘለዓለም የሚኖር ነውና መንግሥቱም የማይጠፋ.... ያድናል ይታደጋል በሰማይና በምድር ታምራትና ድንቅን ይሠራል፡፡ ዳንኤልንም ከአናብስት አፍ አድኖታልና፡፡» ዳን.2፡47 ምዕ 6፡25-27EDA 58.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents