Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የመዝሙር ኃይል፡፡

    የመጽሐፍ ቅዱስ መዝሙሮች ታሪክ የሙዚቃንና የመዝሙርን ጥቅምና ስለ አጠቃቀማቸውም በሚገልፁ ሐሳቦች የተሞላ ነው፡፡ ሙዚቃ ዘወትር ለክፉ ሐሳብ ዓላማ እንዲያገለግል ሆኖ በተሳሳተ መንገድ ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ወደ ፈተና እንድንገባ ክፉኛ ከሚስቡን ነገሮችም ዋነኛው እሱ ነው፡፡ ነገር ግን በትክክል ሥራ ላይ ከዋለ የእግዚአብሔር ክቡር ድንቅ ስጦታ ነው፡፡ ሐሳባችን ወደ ተቀደሰ ክቡር ዓላማ እንዲያነሳሳ ታስቦ የተቀየሰ ነው፡፡ ነፍስንም የሚያነቃቃና ከፍ የሚያደርግ ነው፡፡EDA 185.2

    የእስራኤል ልጆች በበረሃ ሱጓዙ በተቀደሰ መዝሙር እልልታ እያስተጋቡ ይሄዱ ነበር፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ዛሬ እግዚአብሔር ልጆቹ የመናኝ ጉዞ በሚመስለው ሕይወታቸው እንዲደሰቱ አድርጐ ሰጥቶአቸዋል፡፡ በመዝሙር ውስጥ ከመደጋገም ይልቅ የእርሱ ቃላት በአእምሮ ውሰጥ ሰርፀው ሊፀኑ የሚችሉባቸው ጥቂት መንገዶች አሉ፡፡ እንዲህ ዓይነት መዝሙር ደግሞ አስደናቂ ኃይል አለው፡፡ ባለጌ የሆነንና ያልታረመ ባሕሪይን ለመግራት፣ ሐሳብን ለማቀላጠፍና ርህራሔን ለማንቃቃት የተግባርን ውህደት ለማራመድ ድፍረትን የሚያጠፋውንና ጥረትን የሚያዳክመውን ጭጋግና የጭንቅ ምልክትን ሁሉ አስወጥቶ ወዲያ የሚጥል ነው፡፡EDA 185.3

    ልብን በመንፈሳዊ እውነት ለመሳብ ከሚያስችሉት መንገዶች ዋነኛው ነው፡፡ በጭንቀት ለተጐዳና ተስፋ ሊቆርጥ ለተቃረበ ነፍስ ተረስቶ የቆየ የልጅነ መዝሙር የእግዚአብሔር ቃላት ያሉበት ትዝታ ሲታወስ ፈተናዎች ሁሉ ኃይል የሌላቸው ይሆናል፡፡ ሕይወትም አዲስ ዓላማ ተይዛለች፡፡ ለሌሎች ነፍሶችም ብርታትንና ደስታን ማካፈል ይቻላል፡፡EDA 185.4

    እንደ አንድ የትምህርት ዘዴነቱ መዝሙር ያለው ጠቀሜታ ሳይታይ ሊታለፍ የሚገባው አይደለም፡፡ በቤታችሁ ውስጥ እንዲዘመር አድርጉ፡፡ መዝሙሮቹም ጣፋጭና የነጠረ ዜማ ይኑራቸው፡፡ በመዝሙሩ ውስጥ ከሚኖሩት ቃላት ጥቂቶቹ የውግዘት አብዛኛዎቹ ግን የደስታና የተስፋ የእልልታ ይሁኑ፡፡ በትምህርት ቤት ውስጥም መዝሙር ይኑር፡፡ ምክንያቱም ተማሪዎቹ ወደ እግዚአብሔር ወደ መምህሮቻቸውና ወደ ጓደኞቻቸውም እርስ በእርስ ይበልጥ እንዲቀራረቡ ያደርጋቸዋልና፡፡EDA 186.1

    እንደ አንድ የሃይማኖት አገልግሎት ፀሎት የሚያበረክተውን ያክል መዝሙርም አንድ ትልቅ የተግባር ክንውን ነው፡፡ አንደ እውነቱ መዝሙርም ፀሎት ነው፡፡ ልጅ ይኸንን እንዲገነዘብ አድርገው ካስተማሩት በመዝሙሩ ውስጥ ያሉትን ቃላት ትርጉም ያስባል፡፡ እነሱ ወደሚሰጡት ኃይልም የበለጠ ይሳባል፡፡EDA 186.2

    ታዳጊ መድህናችን ወሰን ወደሌለበት ዓለም መግቢያ በር ሲያመለክተን፣ ሥጋችንም የእግዚአብሔርን ክብር ሲለብስ በእርሱ ዙፋን ዙሪያ የሚኖሩት የሰማይ መዘምራን እግዚአብሔርን ከሚያሞግሱበትና ከሚያመሰግኑበት መዝሙር አንዳንድ አንጓዎችን እንይዛለን፡፡ የመላዕክት መዝሙር በሚያስተጋባበት ጊዜ በምድራዊ ቤታችን ውስጥ መነቃቃትን ይፈጥራል ልባችንም ወደ ሰማይ መዘምራን ይሳባል፡፡ የሰማይ ግንኙነት በምድር ይጀምራል፡ አምላክን የማሞገስን ቁልፎችን እንማራለን፡፡EDA 186.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents