Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    የአገልግሎት ሕግ

    በሰማይና በምድር ያሉ ነገሮች ሁሉ በሕይወት ውስጥ ያለው ታላቅ ሕግ ያገልግሎት ሕግ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ ወሰን የሌለው አባት ሕያው ለሆኑ ነገሮች ሕይወት አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ክርስቶስ ወደዚህ ምድር «እንደ አንድ አገልጋይ» ሆኖ መጣ ሉቃ 22፡27 መላዕክት «ሁሉ መዳንን ይወዱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?» እብ 1፡14 ያው የአገልግሎተ ሕግ በሁሉም የተፈጥሮ ነገሮች ላይ ተጽፏል፡፡ በአየር ላይ ያሉ ወፎች፣ የሜዳ አውሬዎች፣ የጫካው ዛፎች፣ ቅጠሎች፣ ሣሩና አበባዎች በሰማዮች ላይ ያለች ፀሐይና የሚያበሩ ኮከቦች ሁሉም አገልግሎት አላቸው፡፡ በሀይቅና ውቅያኖስ ወንዝና የምንጭ ኃይል እያንዳንዳቸው የሚወስዱት ለመስጠት ነው፡፡EDA 111.3

    ስለዚህም በፍጥረት ውስጥ እያንዳንዱ ነገር ለዓለማዊ ሕይወት አገልግሎት በሰጠ መጠን የራሱም ይጠበቅበታል፡፡ «ስጡ ይሰጣችኋል፡፡» (ሉቃ 6፡38) ይህ ትምህርት በቅዱስ መጽሐፍት ገጾች ላይ ከተፃፈው ባላነሰ ሁኔታ በተፈጥሮ ላይም ተጽፎአል፡፡EDA 112.1

    ኮረብቶችን መስኮት ከተራራ ወደባህር ለሚወርደው ውሃ መንገድ እንደሚከፍቱ ሁሉ የሚሰጡት ነገር በፍጥነት በመቶ እጥፍ ይመለሳል፡፡ የሚወርደው ምንጭ ወደታች በሄደ ቁጥር በስተኋላው የውበትና የፍሬአማነት ስጦታ ጥሎ ያልፋል፡፡EDA 112.2

    በመሃል የመኸር ወራት ሜዳዎች ደረቅ ቡናማ መልክ የሚታይባቸው ሆነው ሣለ ወንዝ በሚሄድበት መንገድ ጨሌ ሣርና ለምለም ዛፍ ይታያል፡፡ እያንዳንዱ የዛፎቹ ቀምበጥ እያንዳንዱ የአበባው እምቡጥ ለዓለም ማስተላለፊያ መስመሮች ለሚሆኑ ሁሉ የእግዚአብሔርን የፀጋ ካሣ አዋጅ ይመሠክራሉ፡፡EDA 112.3

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents