Loading...
Larger font
Smaller font
Copy
Print
Contents
ሥነ - ትምህርት - Contents
  • Results
  • Related
  • Featured
No results found for: "".
  • Weighted Relevancy
  • Content Sequence
  • Relevancy
  • Earliest First
  • Latest First
    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents

    ምዕራፍ 11—የሕይወት ትምህርቶች

    «ለመሬት ተናገር እርሷም ታስተምራለች፡፡»EDA 110.1

    በሁሉም ፍጡር ነገሮች ውስጥ አልፎ የሚናገረውን ድምጽ ይሰሙ ዘንድ ልባቸው ገር እንዲሆንና አእምሮአቸውም ተቀባይ ይሆን ዘንድ ታላቁ መምህር አዳማጮቹን ከተፈጥሮ ጋር እንዲገናኙ አደረገ፡፡ ዐይናቸው ካረፈበት ሁሉ ለየት ብሎ ከሚያዩት ነገር ላይ የሚገኘውን መንፈሳዊ ትምህርት በማብራራት ይተረጉሙት ዘንድ ረዳቸው፡፡ የእውነትን ትምህርት ሲያስተምር ትምህርቱን ሊሰጥ ይወድ የነበረው ምሳሌዎችን በመጥቀስ ነበር፡፡ ይህም የርሱ መንፈስ ለተፈጥሮ መስህብ ምን ያክል ክፍት እንደነበረ የሚያሳይና መንፈሳዊ ትምህርቶችን ከአካባቢው የቀን ተቀን የሕይወት ገጠመኞች ላይ ማሰባሰብ ምን ያክል ያስደስተው እንደነበረ የሚያሳይ ነው፡፡EDA 110.2

    በሰማይ ላይ ያሉ ወፎች፣ በመስክ ላይ የሚታዩ አበባዎች ገበሬው በማሳው ላይ ስለዘራው ዘር፣ የበጐች እረኛና በጐቹ፣ ክርስቶስ የማይሞተውን እውነት ያስተማረው እና ያብራራው በእነኝህ ምሳሌዎች አማካይነት ነው፡፡ በሕይወት ከሚያጋጥሙ ሁኔታዎች ወስዶ አዳማጮም በለምድ በኑሮአቸው የሚያጋጥማቸውን ዓይነት ትምህርቶች በመጥቀስ ስለ እርሾ፣ ስለ ጠፋችው ሳንቲም፣ ስለ ጠፋው ልጅ፣ ስለተደበቀው መዝገብ፣ ስለ እንቁ ስለ አሣ አጥማጁ መረብ፣ በጠንካራ አለት ላይ ስለ ተሠራውና በድቡሽት ላይ ስለተሠራው ቤት አብራርቶ ገልጾአል፡፡ በትምህርቶቹ ውስጥ የእያንዳንዱ ሰው አእምሮ የሚያስደስትና ወደ እያንዳንዱ ሰው ልቦና የሚማፀን አንድ ነገር አለበት፡፡ ስለዚህም የየቀኑ ግዳጅ ከፍተኛውን አስተሳሰብ ተነጥቆ በዙር የሚመላለስ የልፋት ሥራ ብቻ ከመሆን ይልቅ በመንፈሳዊውና በማይታየው ያላሰለሰ አስተዋሽነት ሊብራራለትና ሊነቃቃም ይገባው ነበር፡፡EDA 110.3

    እኛም ስናስተምር ልክ እንደዚሁ አድርገን መሆን አለበት፡፡ ልጆች የእግዚአብሔርን ፍቅርና ጥበብ በተፈጥሮ ውስጥ ማየትን ይማሩ፡፡ ስለ እርሱ ያለው አስተሳሰብም ከወፎች ከአበባዎች ከዛፍ ጋር የተያያዙ ይሁኑ፡፡ የሚታዩ ነገሮች ሁሉ ለእነሱ የማይታየውን የሚገልጽላቸው እንዲሆኑና በሕይወት ውስጥ የሚከናወኑ ሁኔታዎች ሁሉ የመለኮታዊን ትምህርት ለማግኘት ምክንያት ይሁንላቸው፡፡EDA 111.1

    እንግዲህ በሁሉም የተፈጥሮ ነገሮች ውስጥ ያለውን ትምህርትና በሕይወት የሚያጋጥሙ ነገሮችን ሁሉ ማጥናትን በሚማሩበት ጊዜ የተፈጥሮን ነገሮች ሁሉና በሕይወት ውስጥ የሚከሰቱ ሁኔታዎችን የሚገዙ ሕጐች እኛን ለመቆጣጠር የተደረጉ መሆናቸውንና ለእኛ ደህንነት ሲባልም ስለሆነ ደስታና ስኬታማነትን ለማግኘት በመታዘዝ ብቻ መሆኑን ያሳያል፡፡EDA 111.2

    Larger font
    Smaller font
    Copy
    Print
    Contents